Sunday, August 25, 2013

ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ በቃሊቲ እስር ቤት ሕይወቱ አለፈ

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው የሰብአዊ መብት ታጋይና መንግስትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል ሕይወቱን በሙሉ በእስር ቤት እንዲያሳልፍ የተፈረደበት ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ በቃሊቲ እስር ቤት ሕይወቱ ማለፉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገቡ።
እንደዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ኢንጂነር ተስፋሁን ሕይወቱ ያለፈው ትናንት ሲሆን ለሕይወቱ ማለፍ የተገለጸ ምክንያታዊ በሽታም ሆነ ሌላ ነገር አልቀረበም።
በኬንያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስደተኛ አድርጎ ወረቀት የሰጠው ቢሆንም የኢሕአዴግ መንግስት ከኬንያ ድረስ ስደተኛውን ኢንጂነር ተስፋሁን ወደ ሃገር ቤት አምጥቶ ያሰረው ሲሆን ሕይወቱን ሙሉ በ እስር ቤት እንዲያሳልፍ ተፈርዶበት ላለፉት 6 ዓመታት በ እስር ቤት መቆየቱ ታውቋል።
በዚህ ዜና ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ይዘን እንቀርባለን።

No comments:

Post a Comment