Wednesday, August 28, 2013

ማን ይናገር የነበረ..... የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ!

(በሰልሞን ተሰማ ጂ.) http://semnaworeq.blogspot.com
Email: solomontessemag@gmail.com
ዕዴሌ አጋጣሚ፣ ሇሰው ሌጅ ስትመጣ፣
መሌካምና ክፉ፣ አሊት ሁሇት ጣጣ !!!
(ከበዯ ሚካኤሌ፣ “የዕውቀት ብሌጭታ”፤)
የታኅሣሥ 1953ቱን (ዒ.ም) “ሥዑረ-መንግሥት” ዋዜማ፣ መባቻና ማግስት
ያካተተ መጽሏፍ ታትሟሌ፡፡ የመጽሏፉ ዯራሲ፣ አቶ ብርሃኑ አስረስ ሲሆኑ፣
አሳታሚው ዯግሞ የአዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ነው፡፡ የመጽሏፉ ርዕስ፣
“ማን ይናገር የነበረ.....፣ የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ” የሚሰኝ ሲሆን፣
በ2005 ዒ.ም ሇመጀመሪያ ጊዜ አዱስ አበባ ሊይ ታትሟሌ፡፡ ይኼንን
የሚያህሌ ቁምነገረኛ መጽሏፍ በ144.00 (አንዴ መቶ አርባ አራት) ብር
ገዝቶ ቁምነገር መዝረፍ ያጓጓሌ፡፡ ገጽ በገጽ ሲገሌጡት ከ እሰከም ስሇላሇው
ነፍስን በሃሴት ያጭራሌ፡፡ አንዴ ጊዜ ብቻ አንበውት የማያሌቅ ሃተታ የያዘ
ዴንቅ ዴርሳን (Masterpiece) ነው፡፡ ዴርሳኑን ዯጋግሞ ማንበብ እውነትን
የበሇጠ ማወቅ ነው፡፡ “ዴንቅ የሆነ ዴርሳን” ነው ያሌኩት ሇማጋነን
አይዯሇም፡፡ በእርግጥም፣ ውብ ነው! እጹብ ዴንቅ ነው!....
 ይኼው ሌንገመግመው የመረጥነው መጽሏፍ እጅግ ከፍ ያሇ የዋጋ
የሚሰጠው፤ የነገረ-መረጃ (Intelegenece)፣ የወታዯራዊ፣ የፖሇቲካ፣
የሕግ፣ የታሪክ፣ የንግዴ፣ የማህበራዊ ሳይንስና የግብረ-ሠናይ ይዘት ያሇው
ሥራ ነው፡፡ እንዯሚታወቀው፣ በሀገራችን የነገረ-መረጃ (የስሇሊ-ነክነት) 
ያሊቸው መጽሏፍት ቁጥር እጅግ በጣም አናሳ ነው፡፡ ያለትም ትቂት
መጽሏፍት ቢሆኑ የትርጉም ሥራዎች ናቸው፡፡ ሇዚያውም ዯግሞ የአቶ ማሞ
ውዴነህ ጥረቶች ናቸው፡፡ ይህም የሆነው በሁሇት ምክንያቶች ነው፡፡
አንዯኛ፣ የዯኅንነት (የመረጃ) መሥሪያ ቤቱ ኃሊፊዎቹ በተከታታይ ሕይወታቸው በምስጢራዊ አኳኋን በማሇፉና
የሚያውቁትን ምስጢራዊ መረጃ ሉዘግቡት ባሇመቻሊቸው ነው፡፡ በጃንሆይ ዘመን የነበሩት የዯኅንነት መሥሪያ ቤት ሃሊፊዎች
በሙለ በሰው እጅ አሌፈዋሌ፡፡ አቶ መኮንን ሀብተ ወሌዴ ዋናው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ላ/ኮሇኔሌ ወርቅነህ ገበየሁም ቢሆን
ተታኩሶ ነው የሞተው፡፡ ኮ/ሌ ዲንኤሌ ዯግሞ በሻሇቃ ዮሏንስ አራት ኪል ቤተ-መንግሥት ውስጥ (ከነሰናይ ሌኬ ጋር አንዴ
ቀን ነው) የተገዯሇው፡፡ የዯርግ ዘመን፣ ሇረጅም ጊዜያት የዯኅንነትና የሀገር ውስጥ ጉዲይ ሚኒስትር የነበረው ኮ/ሌ ተስፋዬ
ወሌዯ ሥሊሴም ቢሆን፣ ከ21 ዒመታት እስር በኋሊ ሉሇቀቅ ቀናት ሲቀሩት መሞቱ ተሰማ፡፡ ከርሱም ቀጥል ኃሊፊነቱን
የተቆናጠጠው “ተጋዲሊይ” ክንፈ ገ/መዴኅን በግንቦት 4/1993 ዒ.ም በጎሌፍ ክሇብ ተገዯሇ፡፡ እነዚህ ሁለ ክስተቶች
ተዯማምረው፣ የኢትዮጵያን የዯህንነት መሥሪያ ቤት የሚመሇከቱ መረጃዎች ከኃሊፊዎቹ ጋር ተቀበሩ፡፡ የኃሊፊዎቹንም ፍጻሜ
ያዩት የመረጃ መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች “ጎመን በጤና” ብሇው እንዱታቀቡ ጥሊውን አጠሊባቸው፡፡
ሁሇተኛውም ምክንያት ከባህሊችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ በብዙዎቹ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰቦች አኗኗር ውስጥ
“አይተኻሌን?-አሊየኹም!” ሰምተኻሌን?-አሌሰማኹም!” በሌ የሚሌ የመረጃና የዯኅንነት መግቻ ጥብቅ ሕገ-ዴንብ አሇ፡፡ ይህ
ሕገ-ዯንብ ከማንም በሊይ የሚጠብቀው የተጠያቂውን ግሇሰብ ዯኅንነት ነው፡፡ “ሰውን ማመን ቀብሮ ነው!” ያሇችውን ቀበሮ
ኢትዮጵያዊት ሳትሆን አትቀርም፡፡ “...ሌቡ ዘጠኝ፣ ሰምንቱን ሸሽጎ አንደን አጫወተኝ!” የተባሇው ተረት ሇሁለምኢትዮጵያዊ ሳይሠራ አይቀርም፡፡ ያም ባይሆን፣ ብዙዎቹ “ምስጢር፣ የባቄሊ ወፍጮ አይዯሇም” ብሇውም የሚያምኑ
በመሆናቸው፣ “አይተው-ሊሇማየትና ሰምተውም-ሊሇመስማት” ከፍተኛ ጥንቃቄ ያዯርጋለ፡፡ በዚህም የተነሣ፣ ኢትዮጵያ
ውስጥ ሇበርካታ ዘመናት ያህሌ፣ ምስጢር-ጠባቂነት የግሇሰቦች ባህሪ ከመሆንም አሌፎ የወሌ ባህሌም ሇመሆን ችሎሌ፡፡
ወዯዋናው ትኩረታችን እንመሌስ፡፡....“ማን ይናገር የነበረ.....የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ”፣ የተሰኘው መጽሏፍ ዯራሲ
ዋናው የትምህርት ጥናታቸው ኤኮኖሚክስ ነው፡፡ በ1951 ዒ.ም በአዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮላጅ የኤኮኖሚክስ ዱግሪያቸውን
በኦክስቴንሽን እያጠኑ ሳሇ ከሻሇቃ ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተዋወቁ፡፡ ሁኔታውን እንዱህ ያስታውሱታሌ፣ “በወቅቱ የምሰራው
በአሜሪካን የማስታወቂያ ክፍሌ (USIS) ነበር፡፡ ዯቡብ የመን ዯርሶ የመጣውን ጓዯኛዬን አዱስ መጽሏፍ ገዝቶ አምጥቶሌኝ
ነበር፡፡ በሥራ ቦታዬ ሊይ ፋታ ሳገኝ ሇማንበብ ከጽሕፈት ጠረንጴዛዬ ሊይ አስቀምጠው ነበር፡፡....የመሥሪያ ቤቱ
ዲይሬክተር... በአንባቢነቴ ይዯነቅ ነበርና ጠጋ ብል አርእስቱን ቢመሇከት “ዲስ ካፒታሌ” የሚሌ ሆኖ ያገኘዋሌ፡፡” በዚህም
ሳቢያ አቶ ብርሃኑ በኮሚኒስትነት ተጠርጥረው ወዯሕዝብ ፀጥታ ጥበቃ መሥሪያ ቤት ይወሰዲለ፤ ሻሇቃ ወርቅነህም ዘንዴ
ይቀርባለ (ገጽ-18)፡፡ (መግቢያችን ሊይ የተጠቀምናት፣ “እዴሌ አጋጣሚ፣ ሇሰው ሌጅ ስትመጣ” የምትሇው የከበዯ ሚካኤሌ
ስንኝ በትክክሌ ዯርሶባቸዋሌ፡፡) ዯራሲው ከተጠረጠሩበትም የኮሚኒዝም ስርፀት ጣጣ ነፃ ቢወጡም ቅለ፤ ወዯUSIS 
ተመሌሰው እንዲይሠሩ ይዯረጋለ፡፡ ከዚህም ጊዜ ጀምሮ፣ ከኤኮኖሚክስ ጥናታቸው ሌቆ የነገረ-መረጃ ሥራቸው ጨምሯሌ
(ገጽ-19)፡፡
“መረጃ አይናቅም፤ አይዯነቅም!” በሚሇው መሠረታዊ የነገረ-መረጃ ንዴፈ-ሃሳብ የሚያምኑት ዯራሲ ብርሃኑ አስረስ፣ ሴራውን
(መፈንቅሇ-መንግሥቱን)ና በሀገሪቱ ውስጥ የነበሩትን የኤኮኖሚ፣ የፖሇቲካ፣ የማኅበራዊና የአስተዲዯራዊ ኩነቶች
በገሇሌተኛነት ሇመተንተን ያዯረጉት ጥረት የሚዯነቅ ነው፡፡ የስዑረ-መንግሥቱ ጠንሳሾች፣ “በህዝቡ ሊይ የመታየውን የፍርዴ
ጉዴሇት፣ የአስተዲዯር በዯሌና የኤኮኖሚ ዴቀት እያስጨነቃቸውና ሰሊም እየነሳቸው ስሇሄዯ፣ አማራጭ መፈሇግ ግዴ
እየሆነባቸው መጣ” ይሊለ(ገጽ፣ 151)፡፡ ነገር ግን፣ በኅዲር 29/1953 ዒ.ም ንጉሠ ነገሥቱ በላ/ኮልኔሌ ወርቅነህ በኩሌ
የሊኳት ቴላግራም ያሇጊዜው እሳት መጫሯን ያትታለ (ገጽ-151/2)፡፡
በገጽ 81 እና 82 ሊይ እንዯገሇጹት ሁለ፣ ሻሇቃ ወርቅነህን ሇሇውጥና ሇመሻሻሌ ያነሳሱትን አምስት ምክንያቶች ዘርዝረዋሌ፡፡
እነርሱም በኮሪያ ዘመቻና በቶኪዮና ሴኡሌ የህክምና ጉብኝቱ እንዱሁም በሲዊዴን ቆይታው ወቅት በገሃዴ ያያቸው
መሆናቸውን ያብራራለ፡፡ ከግርማዊነታቸውም ጋር በተሇያዩ አገሮች ሲሄዴ ባወቃቸው ኩነቶች ተገፋፍቶ እንዯሆነም ያወሳለ፡
፡ የኢትዮጵያንና የሕዝቧንም እዴገትና ብሌጽግና ያጫጨው “የመሬት ስሪት/ፖሉሲው” ጉዲይ መሆኑን ላ/ኮልኔሌ ወርቅነህን
ዋቢ አዴርገው ያትታለ (ገጽ-91/2)፡፡ ኮ/ሌ ወርቅነህ ባቀረበው የመሬት ስሪት/ፖሉሲው ጥናታዊ ማስታወሻ እንዯጠቀሰው፣
“የመሬት ይዞታው ጉዲይ አንዯጋንግሪን እየገዘፈ መጥቶ መንግሥትን የሚያናውጥ ሕዝብንም የሚያፋጅ ቀውስ
እንዯሚያመጣ” ማስረዲቱን ያስታውሳለ፡፡ በአሁኑም ጊዜ፣ “በዒሇም ሊይ ርስት የሇሽ ሕዝብ ያሇባት ብቸኛ አገር (ከኮሚኒስት
አገሮች በቀር) ኢትዮጵያ ሳትሆን አትቀርም፤” ይሊለ(ገጽ-92)፡፡ አያይዘውም፣ “ሰው በሰውነቱ እኩሌ ሆኖ የተፈጠረ ስሇሆነ፣
የአገሩ የተፈጥሮ ሀብት ከሆነው መሬት ዴርሻ ሉኖራ ይገባሌ፤....” የሚሌ አቋም የነበራቸውን አፄ ኢያሱ አዴያምሰገዴን
የመሬት ስሪት ዯንብ ያቀርባለ (ገጽ-121)፡፡ አፄ ምሉሌክም አዱስ አበባን ሲቆረቁሩ ይዘውት የነበረውን ፍትሀዊ የመሬት
ስሪት ዯንብ ያወሱና፣ የምኒሌክ ሹማምንት ግን “ከሕዝብ ተሇይተው መሬት ሇነርሱ ብቻ እንዯተፈጠረ ወዯ ማዴረጉ አዘነበለና
ራሳቸውን ብቻ በማበሌፀግ የማኅበራዊና የኤኮኖሚያዊ ኑሮውን ዯረጃ ሌዩነት አሰፉት፤” ሲለ ይወቅሳለ (ገጽ-125):: 
በመጨረሻም፣ ከበዴ ያሇና ጥንቃቄን የሚሻ ትንታኔ ሇአንባቢያኑ ያቀርባለ፡፡ “የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት ዴሌዴሌ እንዲጠና
ላ/ኮልኔሌ ወርቅነህና አቶ ገርማሜ ንዋይ አዘዙኝ” ይሊለ (ገጽ-119)፡፡ ገርማሜ የኢትዮጵያን የመሬት ወረራ ያመሳሰሇው
ሇመጀመሪያ ዱግሪው መመረቂያ ጽሐፉ ሲያዘጋጅ ካጠናው ከኬንያው የ“ማው ማው” ንቅናቄ ጋር ነበር፡፡ ሆኖም፣ ከሊይ
የተገሇጹትን የአፄ ኢያሱንና የአፄ ምኒሌክን የመሬት ስሪት ዴሌዴሌ ሲረዲ፣ “ዴሮ ከነበረው ስሜቱ መሇስ” ብል እንዯነበር
ያስታውሳለ፡፡ ሆኖም፣ “ገርማሜ ነዋይ፣ እነዚህ ከመሬት ባገኙት ኤኮኖሚ ተጠቃሚ የሆኑ ጥቂቶች፣ የፖሇቲካ ስሌጣኑንም
በመጨበጣቸው በሕዝቡ ሊይ ይዯርስ ሇነበረው የአስተዲዯር በዯሌና የፍትሕ መጓዯሌ በዋናነት ተጠያቂ አዴርጎ ያቀርባቸው”
እንዯነበርም አትተዋሌ (ገጽ-126ና 139)፡፡ በተመሳሳይ ኹኔታም፣ በገርማሜ ታሊቅ ወንዴም በብ/ጄኔራሌ መንግሥቱ ነዋይ
ይመራ የነበረውንም የክብር ዘበኛ አምርሮ ይጠሊው እንዯነበር በገጽ-266 ሊይ ዘግበዋሌ፡፡ ገርማሜ እንዱህ አሇ፤ “የክብር
ዘበኛ... በመፍረሱ ዯስ ብልኛሌ፡፡.... ያ ሠራዊት ጀግና ነው፡፡ የታወቀ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሊይ የፈሇገውን ነገር ማዴረግም
ይችሌ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ በንጉሠ ነገሥቱ ሊይ ያሇው ታማኝነት ከፍ ያሇ ስሇሆነ ሳይዋጋ ቀረ፡፡.... ሠራዊቱ አንዴ የተቃውሞእንቅስቃሴ ተነሳ ሲባሌ ሄድ ያፍናሌ፡፡ ስሇዚህ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሆኑ ማንኛውም ሰው (ዴርጅት) 
በተቃውሞ መንቀሳቀስ ወይም የሌቡን ተናግሮ ሀሳቡን መግሇጽ ስሊሌቻሇ፣ ይህ ሠራዊት ከተበተነ በኋሊ ሇተቃውሞ
እንቅስቃሴ ይነሣሣሌ፡፡ ዒሊማውም ውጤት እንዱያገኝ ይረዲሌ....፡፡” ከአራት ዒመታትም በኋሊ ገርማሜ ነዋይም
እንዯተነበየው ሆነ፡፡ በ1957 ዒ.ም ጀምሮ የተማሪዎች አመጽ እየበረታ ሄዯ፡፡
አቶ ብርሃኑ፣ ሇመጽሏፋቸው ዋና መነሻ የሆኗቸውን ሃሳቦች ያገኙት በዴርጊቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆናቸው ነው፡፡ ዯራሲው፣
እዚህም-እዚያም ተሰባጥረው የሚገኙትን የ1953ቱን ስዑረ-መንግሥት መነሻና መዴረሻ “ማን ይናገር?...የነበረ!” እና
“የታኅሣሡ ግርግር” ባለት ሃይሇ-ሃሳብ አዯሊዲይነት በፈርጅ-በፈርጁ ሉዯሇዴለት ጥረዋሌ፡፡ ሙከራቸውም ፈሩን ያሇቀቀ
ነበር፡፡.... በአስተሳሰባቸውና በአቀራረባቸውም የገሇሌተኛነት ስፍራን ሇመውሰዴ ተግተዋሌ፡፡ በመፈንቅሇ-መንግሥቱ ሴራ
ተሳትፏቸው የተነሣ ሇአምስት ዒመታት ያህሌ ቢታሰሩም፣ የእሌህና የስሜታዊነት ጥገኛ ሇመሆን አሌፈሇጉም፡፡ ከዚህም
ከዚያም ብሇው ጠቃሚ የሆኑትን ሃሳቦችና ነጥቦች ተፈሊሌገው በማጠናቀር የዏይን እማኞችን ሃቲት ሇማካተት ተግተዋሌ፡፡
ይሁንና፣ ምንም የገሇሌተኛነት መንገዴን ሇመውሰዴ ቢሞከሩ እንኳን፣ በአሇቃቸው/በወዲጃቸው በላ/ኮልኔሌ ወርቅነህ
ገበየሁ ተጽእኖ ስር ከመውዯቅ አሊመሇጡም፡፡ “የመፈንቅሇ መንግሥቱ መሪዎች” የሚሇው ምዕራፍ ሥር “ወርቅነህ ገበየሁ
(?-1953)” የሚሇው ንዐስ-ርዕስ የዯራሲውን የሃሳብ አካሄዴና የአስተሳሰብ ፈሇግ በይበሌጥ የሚመሰክር ነው፡፡ ዯራሲው
ንጉሠ ነገሥቱንና ላልችንም ሰዎች የሚያዩት በእነርሱ ዏይን ነው፡፡ ሇአብነትም ያህሌ ገጽ-85፣ ገጽ-92፣ ገጽ-102፣ ገጽ-
111/2፣ ይጠቀሳለ፡፡ በገጽ-145ና ገጽ-342 ያለትን አተያዮች ዯግሞ በብ/ጄኔራሌ መኮንን ዯነቀና በመቶ አ/ በቀሇ አናሲሞስ
በኩሌ ነው ያስተሊሇፉት፡፡ ይኼንንም ያዯረጉት ይሆነኝ ብሇው ነው፤ ከስሜታዊነት ሇመራቅ፡፡
በተጨማሪም፣ ዯራሲው በመፈንቅሇ መንግሥቱ ተሳታፊ የነበሩትን ዋና ዋና ተዋንያን እስር ቤት ሳለና ከወህኒ ቤትም ከወጡ
በኋሊ ተከታትሇው በማናገር የተበታተኑትን ምስጢራዊ መረጃዎች አጠናቅረውና አስፋፍተው በመፃፍ አንዴ ጉሌህ-ፈር
ቀዯዋሌ፡፡ ከእንግዱህ ወዱያም፣ የተሇያዩ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ የፖሇቲካ ሳይንስ አጥኚዎች፣ የሥነ-ጽሐፍና የትውን ጥበባት
ቀማሪዎች ስሇጉዲዩ በየፊናቸው ሇመተርጎም የሚያስችሊቸውን ግብዒት አግኝተዋሌ፡፡ ከዚህም ላሊ፣ ምስጢራዊ ሰነድችና
መረጃዎችም እንዯምን ሉገኙ እንዯሚችለ መሊና ዘዳውን ገሌጠዋሌ፡፡ ሇውጥ እንዳት ያሇነውጥ ሉመጣ እንዯሚችሌ
ተሞክሯቸውንም አካተዋሌ፡፡ በምዕራፍ 1ና በምዕራፍ 9 ስርም ያለት ሁሇቱ ሃተታዎች ይኼንን የዯራሲውን የሕይወት
ተሞክሮና ዕጣ-ፈንታ ይተርካለ፡፡ የሚዯንቀው ነገር፣ ዯራሲው “እኔ-በዚህ ወጥቼ፣ እኔ በዚህ ወርጄ!” ከሚሇው የንፉግ ትችት
የራቁ መሆናቸው ነው፡፡
በታኅሣሥ 1953 ዒ.ም የተዯረገውን የመፈንቅሇ መንግሥት ሙከራ ተከትልም፣ በስዴስት ኪል ገነተ-ሌዐሌ ቤተ-መንግሥት
አረንጓዳው ሳልን ስሇተገዯለት አስራ አምስት(15) ባሇሥሌጣናት አሟሟት ሌከኛውን መረጃ ይሠጣለ፡፡ ግዴያውን የመራው
ገርማሜ ነዋይ እንዯነበረና ዋነኛው ነፍሰ-በሊም እጩ መኮንን ነጋሽ ዴንበሩ መሆኑን ይገሌፃለ (ገጽ-258 እና 266 ይመሌከቱ፡
፡) ብ/ጄነራሌ መንግሥቱ ነዋይ፣ “ኧረ ሇመሆኑ ሚኒስትሮቹ እንዳት ሆኑ? ፈታችኋቸው? ሌዐሌ ጌታዬስ? (አሌጋ ወራሹስ) 
ማሇታቸው ነው፤” ብሇው ሲጠይቁ፣ ገርማሜ “እሳቸው እዛው ናቸው፡፡ ሇሚኒስትሮቹ ግን የሞት ቅጣት ሰጥተናሌ፤” እንዲሇ
ይተርካለ፡፡ የመጽሏፉም አንኳር ነጥብ ያሇው እዚሁ ሊይ ነው፡፡ በኮሚኒዝም ስርፀት ከሁሇተኛው የእጩ መኮንንነት ኮርስ
የተቀነሰው መርሻ ዴንበሩና በኮሚኒስትነት ከወሊይታ አውራጃ ገዢነቱ የተነሳው ገርማሜ ነዋይ፣ ዜጎችን ያሇፍርዴ በመግዯሌ
ሇነሻሇቃ መንግሥቱ ኃይሇ ማርያም አርዒያ ሆኑ፡፡ ሇላልችም “በዱሞክራሲ ካባ ስር፣ የማርክሲዝምና ላኒኒዝምን ጃኬት” 
ሇሇበሱ ነፍሰ ገዲዮች አጽዴቆት ሰጡ፡፡
ማጠቃሇያ፤
“ማን ይናገር የነበረ.....የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ”፣ የተሰኘው መጽሏፍ እጅግ የሚዯነቅ የቋንቋ
አጠቃቀምና የቃሊት አሰካክን የተከተሇ ነው፡፡ አሌፎ-አሌፎ የቀበሌኛ ቃሊትን ቢጠቀምም እንኳ፣ በግርጌ ማስታወሻ አማካይነት
“ፍቻቸው” ተቀምጧሌ፡፡ በዚህ መጽሏፍ ውስጥ ያሇው ጉዴሇት በዋናነት አንዴ ነው፡፡ እርሱም፣ በአረንጓዲ ሳልን ውስጥ
በነገርሜ የተገዯለባቸው የራስ አበበ አረጋይ፣ የራስ ስዩም፣ የሜ/ጄኔራሌ ሙለጌታ ቡሉ፣ የአቶ መኮንን ሀብተ ወሌዴና
የላልችንም ባሇሥሌጣመናት ቤተሰቦች አሇማናገራቸው ነው፡፡ ከዒመታት በኋሊ፣ እነዚህ የሟቾቹ ቤተሰቦች ስሇመፈንቅሇ
መንግሥቱ ያሊቸውን ስሜትና እውቀት ሉያካትቱት ቢችለ ምንኛ ዕጹብ-ዴንቅ ይሆን ነበር፡፡ ከአቶ ብርሃኑ አስረስ
አሌገፉበትም እንጂ፣ ትሌቅ ሙከራ አዴርገው እንዯነበር አያጠራጥርም፡፡ በ1953 ዒ.ም የፍትሕ ሚ/ር የነበሩትን ዯጃ/ችዘውዳ ገ/ሥሊሴንና ብ/ጄኔራሌ መኮንን ዯነቀን ሇማነጋገር ያዯረጉት ጥረት መሌካም ነው፡፡ እጅግም የሚዯነቅ ነው፡፡ በሰማኒያ
ሦስት ዒመታቸው የተሇያዩ ጫናዎችን ተቋቁመው ይኼንን የመሰሇ ዴርሳን ስሊቀረቡሌን ሇአቶ ብርሃኑ አስረስ ያሇኝን ምስጋናና
ሌባዊ አክብሮት በአንባቢያን ስም ይዴረሳቸው እሊሇሁ፡፡ አንባቢያንም፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋሊ ዋጋው ተፋፍቆ በእጥፍ
ከምትገዙት፣ ዛሬውኑ መጽሏፉን በትክክሇኛው ዋጋ “የግሊችሁ አዴርጉት!” በማሇት ወንዴማዊ ምክሬን አስተሊሌፋሇሁ፡፡
ሇአቶ ብርሃኑም መሌካም ጤንነትና ሰሊምን እመኛሇሁ፡፡ (በተረፈ፣ በቸር እንሰንብት!)
በሳምናታዊው የአዱስጉዲይ መጽሔት ቅጽ 7፣ ቁ. 178 ሊይ፣ በነሏሴ 18 ቀን 2005 ዒ.ም የወጣ ነው:

No comments:

Post a Comment