Tuesday, August 27, 2013

ኢሕአዴግ ሆይ፤ በህግ አምላክ! ሕግ ይግዛክ!!

ቀጥሎ የሚታዩዋቸው ግለሰብ የመ/አ መሰቦ ማዳልቾ ይባላሉ፡፡ በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ ዞን ከቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ማለትም ከፍትህ/ከመልካም አስተዳደር፤ ከማንነት/ከብሔር እና ከልማት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ዛሬ በአርባ ምንጭ ወህኒ ቤት ይገኛሉ፡፡
1185279_556267574441149_1239414489_n
እርሳቸውን በሚያውቁት ዘንድ ተወዳጅ፤ ከማያውቁት ዘንድ ቶሎ ተግባቢ፤ በአጠቃላይ በአቀራረባቸው ትሁቱ፤ በባሕርያቸው መካሪና አስታራቂ፤ እንዲሁም ደግና ለተቸገሩት ደራሽ ባለ ሀብት እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ በተለይ መለያቸውም ይህ ነው፡፡ ባለሀብቱ የቁጫዎችን ጥያቄ በሚመለከት ከአሜሪካ ሬዲዮ (VOA)፤ ከጀርመን ሬዲዮ (DW)፤ እና ከሌሎች የፕሬስ የሚዲያዎች ጋር ቃለ-ምልልስ አድርገሃል፤ በዚህም “ሕዝብን ለአመጽ አነሳስተሃል”፤ በሚሉና በተያያዥ ክሶቸ የጋሞ ጎፋ ዞን ፖሊስ በቁጥጥር ሥሩ የዋሉት ባለፈው ቅዳሜ ነሐሴ 11ቀን 2005 ዓ.ም  ማለዳ ላይ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ እንደሰማሁት ከሆነ፤ ፖሊሶች ግለሰቡን ለማሠር የፈለጉበት ምክንያት ምንም ይሁን ምን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተከተሉት መንገድ የሕግ አግባብነትን የተከተለ ነበር የሚል ድምዳሜ አለኝና ለሠራዊቱ አባላት ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች እስረኞች ጋር ማለትም የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው በፍ/ቤት ተወሰኖላቸው ግን ማረሚያ ቤቱ ከሌሎች ተቋማትና ከተቋማቱ ሥራ ኃላፊዎች ጋር በማበር አልፈታም በማለት እስከ ዛሬዋ ቀን ማለትም ነሐሴ 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ያልሆነበትን ሁኔታ የተለያዩ ሚዲያዎች በተደጋጋሚ ዘግበውበታል፡፡ የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና የፖለቲካ ድርጅቶች በቁጫ እየተፈፀመ የለውን ህገወጥ ድርጊት ያወገዙት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 13-እስረኞችን=ለ27-ቀናት፤ እንዲሁም 25-እስረኞችን ደግሞ=ለ19ቀናት አስሮ ካስቀመጣቸው እና ገና ዕጣ ፋንታቸው ካልታወቀላቸው ስመ ጥር የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በአንድ ላይ አርባምንጭ ወህኒ ቤት ይገኛሉ፡፡  ባለሀብቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ወላይታ ሶዶ ከተማ ነበር፡፡ ወደ ሶዶ ከተማ የመጡትም ለሆቴላቸው፣ ለፋርማሲያቸው፣ ለእርሻዎቻቸው እና ለሌሎች ንግድ ተቋማቶቻቸው የሚሆኑ ቁሳቁሶችንና ለመግዛትና ሠራተኛ ለማፈላልግ እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የመ/አ መሰቦ ማዳልቾን ፖሊሶች ሲይዙዋቸው፣  ወላይታ ሶዶ ከሰላምበር ከ62-65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኝ ከተማ ሆኗን በማስታወስ፡- “ይህንን ያህል ኪ.ሜ ተጎዞ መምጣትንና ነዳጅ ማቃጠልን፤ ጎማንና የመኪና ውስጥ አካላትን (spare parts) መጉዳት ለምን አስፈለገ? እኔምኮ ቁርስ እንደበላሁ ወደ ሰላምበር ልመለስ ነበረኮ ለምን ይህንን ያህል ሽፍታ ለመያዝ እንደተሠማራ ኃይል ሌሊቱን በብርድና በውርጭ እንቅልፍ አጥታችሁ ለፋችሁብኝ” በማለት ለፖሊሶቹ ያለቸውን ርኅራኄ ገልጾላቸው የነበረበትን ሁኔታ ያጫወተኝ ሰው ለራሱ ከመሳቁም ባሻገር እኔንም ፈገግ አድርጎኝ ነበር፡፡

No comments:

Post a Comment