የኢትዮጵያ ሚሊታሪ አቪየሽንና የኢትዮጵያ ኤየር ሀይል ከሁለት ሳምነት በፊት ድሬዳዋና ሞቃዲሾ የወደቁትን ሁለት አውሮፕላን አደጋዎችን እየመረመሩ እንደሆነ ለሪፖርተር የውስጥ አዋቂወች አስታዎቁ፡፡ ከኢትዮጵያ ሚሊታሪ አቪየሽንና ከኢትዮጵያ አየር ሀይል የተመረጡ የአደጋው ምክንያት አጣሪዎች አደጋው ወደተከሰተበት ቦታ መላካቸውም ተጠቅሷል፡፡
የመጃመሪያው አደጋ ኦገስት 6 ሲ130(ኤል100) የተባለ የጦር አውርፕላን ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር መንገድ ላይ ሲከሰት ሁለቱ ተሳፋሪዎችም ቀላል አደጋ አጋጥሟቸዋል፡፡ የአውሮፕላኑ ፓይለት የነበሩትም ኮሎኔል ሰለሞን ሲሆኑ የተጎዱት ሁለቱ ተሳፋሪዎች አዲስ አበባ በሚገኘው ጦር ሁይሎች ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ሁለተኛው አንቶኖቭ 12 አውሮፕላን ደግሞ ኦገስት 9 በሶማሊያ ሞቃዲሾ አየር መረፊያ ላይ ተከስክሶ በእሳት ሲቀጣጠል ከስድስቱ ተሳፋሪዎች ውስጥ አራቱ ሞተው ተገኝተዋል፡፡ ሁለቱ የተረፉት ተሳፋሪዎች ደግሞ ወደ ሞቃዲሾ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ይህ አውሮፕላን የሙስሊም ታጣቂዋች ጋር ለሚዋጉት የአለም አቀፍ ሀይሎች መሳሪያ ጭኖ ነበር፡፡
የሄው የጦር እቃ ጫኝ አንቶኖቭ 12 አውሮፕላን ኦገስት 9 ከጠዋቱ 12፡00 ሰአት ከድሬዳዋ ተነስቶ ከሁለት ሳታት በኋላ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ላይ ጠዋት 2፡00 ተከስክሷል፡፡
ለሪፖረተር የታመኑ የዜና ምንጮች አንደዘገቡት የኢትዮጵያ ሚሊታሪ አቪየሽንና የኢትዮጵያ ኤየር ሀይል ኤክስፐርቶች በሶስት ቀን ልዩነት የተከሰቱትን የአውሮፕላን አደጋዎች ምርመራ እያካሄዱ ነው፡፡ የአደጋዎቹ መንስኤ ገና እንዳልታወቀና መረጃዎች እየተሰበሰቡ እንደሆነ ምንጮቹ ጠቅሰዋል፡፡ ምነጮች ጨምረው እንደተናገሩት ‘‘ ሁለት አደጋዎች ባአንድ ሳምንት ማለት ብዙ ነው፡፡ አደጋው የተከሰተው ባጋጣሚ ወይም ታቅዶበት ሊሆን ይችላል፡፡’’ ብለዋል፡፡
የበረራ ኤክስፐርቶች እንዳሉት አንቶኖቭ አውሮፕላን ደካማ አደጋን የመከላከል ብቃትና የደህንነት መጠበቂያዎች እንዳሉት መዝገቦቹ ያረጋግጣሉ ብለዋል፡፡ ብዙ ያረጁ አንቶኖቭ አውሮፕላን አደጋዎች በአፍሪካና በተለያዮ የአለማች ክፍሎች ተከስተዋል፡፡ እንደ ኤክስፐርቶቹ ገለጻ ሲ130 አውሮፕላኖች በአንጻራዊ ሁኔታ የተሸሉ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ኤክስፐርቶች እነዳሉት ማንኛውም አውሮፕላን በደካማ ሁኔታ ከተጠገነ የመከስከስ አደጋ ሊያጋጥመው ይችላል ፣ ነገር ግን ያረጁ አውሮፕላኖች የመከስከስ አደጋ ከየትኛውም አውሮፕላኖች በተለየ ሁኔታ ይጨምራል፡፡
No comments:
Post a Comment