**ኢህአዴግን(ራዕይና ሌጋሲውን)የሚያውቀው የለም።ኢትዮጵያም አውሮፕላን እንዳላት ደሪምላነርም ገዝተን ለምነን እንደምንበላ ‘ደሮነርም’የሚሠራ አትራፊ የመከላከያ ኅይል እንዳለን የሚመሠክረውና የሚያውቀው ያው ፓርላማ፣ የኤምባሲ ካድሬና ቤተሰቦች ተሰብስበው ቡና በማፍላትና በመጨፈር ነው። ስለዚህ ፖለቲካን ከእስፖርት ጋር እናደባልቀው…
(አብዮታዊ ዴሞክራሲያውዊና ኦሎምፒካዊት ኢትዮጵያ!በለው!)
(አብዮታዊ ዴሞክራሲያውዊና ኦሎምፒካዊት ኢትዮጵያ!በለው!)
ኅይሌ ገብረስላሴ ስንት ታላላቅ ሰዎችን ጨብጧል ሲሸነፍ የሚስቅ ተብሏል፡ በሀገር ውስጥም በሠራው ተጨብጧል!። ምን ቢሆን ከ፻ ዓለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በምን ያንሳል? ዶ/ር ነው። ሻለቃ ነው። ቢያንስ ደብዳቤ ተቀብሎ ደብዳቤ ላይ ፈርሞ፣ ተነስቶ ጨብጦ ተቀምጦ ስቆ በፈገግታው ሀገራችንን ማንነት ከፍ ያደርግልናል።ኢትዮጵያ አውሮፕላን አላትን? ሲሉ ለመሆኑ ሀይሌገብረስላሴ ለሩጫ ይህንን ሁሉ ሀገር የሄደው እየሮጠ ነው ወይንስ በበቅሎ ነበር ብለው ነው?
እኛስ የተጠቀለሉ መሪ አፍሪካን የወከሉት በባዶ እግራቸው ሄደው ነበር? ወይ ንቀት ብታምኑም ባታምኑም ኢህአዴግ ተደፍሯል! ተንቋል!ተዋርዷል!በዓለም ኢህአዴግ ለመኖሩና ሥልጣን ለሠፊው ሆዳም ህዝብ እንደሚሰጥ ከመድብለ ፓርቲ የተዳበለ ወንበር በ፪ጠ/ሚኒ በ፩ ምጠ/ሚ በ፪ም/ጠ ሚኒ መሳይ (በደቦ)የምትመራ ፓርቲ ለፈገግታ እንግደህ ኅይሌ ትጨምርና ሠው ይሙት ፈርም ሲሉት ከፈረመ ይህ ሰው ይፈታ ሲሉት ሮጦ ይጠፋል። ግን በአበባ ተከቦ በተቀመጠ ቁጥር መናፈሻው(እሪዞርትቱ) ያለ መስሎት በቁምጣ እንዳይቀመጥና እንግዳ እንዳይመጣ!እንዳያሳጠን በለው! ፻ አለቃም እንዲሁ የሹመት ደብዳቤ ለአመጣው ሁሉ “እስቲ ትኩስ የማር ጠጅ ይላሉ አሉ።”
***ምን አባቱ የተናቀ ሠፈር በዲያስፖራ ይከበባል አሉ! መቼም በስታዲየም መሮጥና በፖለቲካ መሮጥ አንድ ነው። ቢያንስ ፓርላማ ገብቶ ሥቆ ማሳቅ ያቅተዋል? ። ለነገሩ በእንግሊዘኛ ከአቶ መለስ አያንስም!ለነገሩ ልጆቹም አማርኛ አይችሉም በእንግሊዘኛ ይረዱታል መውለድ ጉዱ!? በፈገግታ ከአቶ ኅይለመልስ አይተናነስም!።ግን ይህ ቦታ ኅይለመልስን ይመጥን ነበር። ኢሳያስ ኣፈዋርቄ አሸባሪ! የቀጠናው አተራማሽ! ወንበዴ! ብለው እቤቱ ሄጄ ጸሎት አድረጌ እግሩ ላይ ወድቄም ቢሆን እደራደራለሁ አሉ። እሪ በይ ወያኔ አለ የእኛ ሀገረ ሰብ …
ኅይሌ ገብረስላሴ በገንዘብ ከሼክ አላሙዲን አይተናነስም! እንዲያውም “እኛ ኢንቨስተሮች ሥራ ሥለምንከፍት ስንሳሳትም ዝም በሉን ብታዩንም እንዳላያችሁ ሁኑ አደለም ያሉት በአንድ ደምፅ!!”ሌላው ከሩጫ በኋላ ባንዲራ ይዞ ይሮጣል ፕሬዘዳንት ሲሆኑ ሁልጊዜ በመኪና ላይ ያውለበልባል ለነገሩ ትርጉሙን ቢያውቁት ባትሉኝ እንጂ!..
ኅይሌ ገብረስላሴ በገንዘብ ከሼክ አላሙዲን አይተናነስም! እንዲያውም “እኛ ኢንቨስተሮች ሥራ ሥለምንከፍት ስንሳሳትም ዝም በሉን ብታዩንም እንዳላያችሁ ሁኑ አደለም ያሉት በአንድ ደምፅ!!”ሌላው ከሩጫ በኋላ ባንዲራ ይዞ ይሮጣል ፕሬዘዳንት ሲሆኑ ሁልጊዜ በመኪና ላይ ያውለበልባል ለነገሩ ትርጉሙን ቢያውቁት ባትሉኝ እንጂ!..
እንግዲያውስ መለስ ከቻይና(የቡድን)ቤተሰባዊ አመራር ፣ ኅይለማርያም ከህንድ(የኀብርት)(የደቦ)ከፊት ያላችሁ ሁሉ መሪ ናችሁ ፣ ኅያሌ ገ/ስላሴ ከኦሎምፒክ( በይቻላል)(በይሆናል) እየመከረ ወይ ከመካከለኛ ወይ ከመጨረሻ አጥር ግቢ እንሠለፋለን ! እግዝኦ…የቡድን የኅብረትና ኦሎምፒክ አመራር ያለህ…ኅይለመንግስቱመለሰማርያምገብረስላሴ…..በለው!!በቸር ይግጠመን ከሀገረ ከናዳ
No comments:
Post a Comment