ሟች ሃይቅ ውስጥ በመዋኘት ላይ እያለ አጠገቡ የነበረች አንድ ጉማሬ ግራ እግሩን በመንከስ እና አንስታ በመወርወር ህይዎቱ እንዲያልፍ አድርጋዋለች።
ከሃይቁ ውጭ ሆነው ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ጓደኞቹ ለፖሊስ በመናገራቸው ፖሊስ ደርሶ ጉዳዩን እንዲመለከት አድርገዋል።
በሀይቁ ላይ ጉማሬ መሰል አደጋ ሲያደርስ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የጠቀሱት ኢንስፔክተር ሳሙኤል ፥ ጉማሬዎቹ በሃዋሳ ሃይቅ ላይ ብቅ የሚሉበት የራሳቸው የሆነ ጊዜ እንዳላቸው እና በተለይ ጤዛ የመላስ ባህሪ ስላላቸው እና ቁስለት ሲኖርባቸውም ውጭ ስለሚያገግሙ ሰዎች ባይቀርቧቸው የተሻለ ነው በማለት መክረዋል ።
No comments:
Post a Comment