እንዲያውም የሙያተኛውን መብት ለማስከበር ከባድ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩትን በርካታ ማህበራቶችን ማፈራረስና ማዳከም ነው ቀዳሚ ስራው ያደረገው፡፡
ዛሬ ላይ ቆመን 22 አመት ሙሉ ለሙያ ነፃነት ፣ ለባለ ሙያተኛው መብት እና ግዴታ የሚታግሉ ነፃ እና ገለልተኛ ማህበራት/ተቋም አለመፈጠሩንና መፈራረስን ወደኋላ ስንመመለከት የኢህአዴግ ጠንካራ ማህበራትን እና የህዝብ ተቋማትን ማፍረስ ትልቁ አጀንዳው ለምን ሆነ ለሚል ጥያቄ እናነሳለን፡፡
የሰራተኛ ማህበር ፣የመምህራን ማህበር፣ የነፃ ጋዜጠኞች ማህበር ፣የኢትዩጲያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ … የቱ ተነስቶ የቱ ይቀራል ብዙ መጥቀስ ይቻላል፡፡
በኢትዮጲያ ነፃ ሙያ ማህበራት በሌሉበት ወቅት የሙያ ነፃነቴን አላስነካም በማለት ለእስር የተዳረጉ በርካታ ንፁህ ኢትዮጲያውያን አሉ፡፡ ተደጋግሞ እንደሚገለጸው ከነዚህ ውስጥ ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በጋራ የሚታገልላቻው ተቋማ/ማህበር ሳይኖር በግላቸው መከራን እየተቀበሉ ባለበት ኢህአዴግ ስልጣን ከያዝ በኋላ የታየ ጠንካራ የሙያ ማህበር የለም፡፡ሰአት ቸል መባላቸው አሳስቦኛል፡፡

በሃገር ውስጥ በእስር እና በእንግልት ላይ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የጋዜጠኞች የሚያስከብር ተቋም ባለመኖሩ ምክንያት ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ብቸኛ ወኪል እና ተቆርቋሪ ሆነዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት ኢህዴግ የሚፈጽመውን ሀሳብን በነፃነት መግለፅና የሙያ ነፃነት ረገጣ ደጋግመው ሲቃውሙ ይሰማሉ፡፡
ነገ ግን በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት የተቃወሙትን ድርጊት ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ የሚመስለው African Media Initiative (AMI) በኢትዮጲያ ጥቅምት ላይ የአፍሪካ የመገናኛ ብዙሃን መሪዎችን ለመሰብሰብ ወስኖአል፡፡
በእኔ አቋም African
Media Initiative ይህንን የአፍሪካ የመገናኛ ብዙሃን መሪዎች 6ኛ አመታዊ ስበሰባ በአዲስ አበባ ማካሄድ የለበትም፡፡ ምክንያቱም ስብሰባውን በአዲስ አበባ ካደረገ ኢህአዴግ የሚያደርገውን ሀሳብን በነፃነት መብት አፈናና ሰብአዊ መብት ረገጣ ያበረታታል ፣ ለነፃነት መሰዋትነት እየከፈሉ ያሉትን ሰዎች ሞራል ይነካል እንዲሁም የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ይከፋፍላል፡፡ ነገ ግን በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት የተቃወሙትን ድርጊት ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ የሚመስለው African Media Initiative (AMI) በኢትዮጲያ ጥቅምት ላይ የአፍሪካ የመገናኛ ብዙሃን መሪዎችን ለመሰብሰብ ወስኖአል፡፡
በሀገሪቱ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ እና የሙያ ነፃነት ተነፍጎአል፡፡ ለነዚህ የህዝብ መብቶች የሚከራከር ገለልተኛ ተቋም በኢትዮጲያ በሌለበት ወቅት የአፍሪካ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ ይህንን ድርግት ከሌላው ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን ማውገዝ እየተገባው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመመካከር ይህንን ስብሰባ በአዲስ አበባ ለማካሄድ ማቀዱ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡
ስለሆነም ይህንን ስብሰባ በአዲስ አበባ እንዳይደረግ የተቃውሞ ጥሪየን እንድትደግፉ እና እንድትተባበሩ ለመላው ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ደጋፊዎች በሙሉ አቀርባለሁ፡፡
No comments:
Post a Comment