Monday, August 5, 2013

***በሰላማዊ ለውጥ ላይ በር የዘጉ፣ አመፃን በራሳቸው ላይ ይጠራሉ፡፡***

በመላው ኢትዮጵያ፣ በእስልምና እምነት ተከታይ የሃገሪቱ ዜጎች ላይ በስፋት የግድያ እርምጃ አምባገነኑ ስርዓት እየወሰደ ነው አሳፋሪ፣አዛዛኝ ተግባር ነው። ክቡር ህይወታቸውን በግፈኛው ወያኔ/ኢህአዴግ የአፈና ሃይል ያጡት ወገኖች ቁጥር በርካታ ሆኗል ዝምታው ደግሞ ዕልፍ አዕላፍ ያደርገዋል። ክፉኛ የቆሰሉት ወገኖቻችን ቁጥር ከተገደሉት እጅጉን የገዘፈ ነው። ፍጹም አረመኔያዊነት በተሞላው መንገድ በወያኔ ቅልብ ጦር የተቀጠቀጡትና እንደከብት ተሰብሰብው በየእስር ቤቱ የታጎሩት ወገኖቻችን ቁጥር በሽዎች የሚቆጠር ሆኗል። እጅግ ሰላማዊና ስልጡን በሆነ መንገድ ፍትሃዊ ጥያቄ ባነሱ ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እልቂት ሊያንገበግበን ይገባል። የደረሰባቸውን መከራና እንግልት እያንዳችን የራሳችን መከራና እንግልት አድርገ መውሰድ አለብን
ዕሊና ቢስ ብቻ ነው የሰውን ስቃይና እንግልት የሚያስደስተው።
ማንም ነፃ እንዲያወጣን መጠበቅ የለብንም እራሳችን ነን ነፃነትን ለማምጣት መፋለም ያለብን!!
ወያኔን አያወግዝም ወይም ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመውን ግፍ በገንዘብና በስልጠና በዲፕሎማሲ ድጋፍ የሚያበረታቱን የምእራብና ሌሎች የወጭ መንግስታት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማድረግ አይፈልጉም እነሱም በናሽናል ኢንተረስት ጥቅም ተሳስረዋል።
ባለፉት 22 አመታት ውግዘትና መማጸን የትም እንዳላደረሱን በሚገባ እናውቃለንና። ተደጋግሞ ግልጽ እንደሚነገረው የኢትዮጵያ ህዝብ መከራ የሚያበቃው ህዝብ የወያኔን በእብሪት የተሞላ ግፈኛ ማንነት የሚመጥንና የሚስማማ የትግል ስልት መርጦ አምሮ ወያኔን ታግሎ በመደምሰስ ብቻ ነው። ሙስሊሙም ሆነ የሌሎች እምነት ተከታዮች መረዳት የሚገባን ወያኔ ስላማዊና ስልጡን ከሆነው የእኛ አለምና መርህ ጋር የማይተዋወቅ ዘረኛ ገዳይ ሃይል መሆኑን ነው።
ይህ በእብሪትና በድንቁርና የታጀለ የወያኔ/ኢህአዴግ ሃይል የኢትዮጵያን ህዝብ ትእግስት ከፍርሃት፣ አርቆ አሳቢነታችሁን ከሞኝነት ጋር አስተሳስሮ የሚያይ ነው።

ታጋይን በማሰርና በመግደል ትግሉን ማሰር አይቻልም !
የሚመቸውን ህግ በማውጣት ሰውን በፀረ ሽብርተኛ በመክሰስ በማሰርና በመግደል ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ ለሱ የሚመቹትን እና ለሱ የሚሰግዱትን በማገልገል ሌላውን ሕዝብ ከሌላ አገር የመጣ ይመስል እያሰቃየው በሚገኝበት ወቅት ላይ መሆኑን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም ! 
‹‹
ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትም›› የሚል ፅኑ መፈክር በማሰማት በበርካታ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ከፍለው ባቆዩት አገር ወደስልጣን የወጣው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት መፈክሩን በመዘንጋትታሪክ ራሱን ይደግማልእንደሚባለው ያለፉትን ገዥዎች ታሪክ እየደገመ ይገኛል፡፡

በአደባባይ መግደልና በሚስጥር መግደል ሁለቱም የወንጀል ልዩነት የላቸውም፡፡ የዜጎችን ነፃነት ቀምቶ፣ ሃሳባቸውን በነፃነት እንዳይገልፁ እያሸማቀቁ ተቃዋሚዎችንም የተለያየ ስም እየለጠፉና 

ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከት የገዥው መንንግስት ለራሱእያሰሩ መኖር ጊዜውን ጠብቆ በወንጀለኝነት እንደሚያስጠይቅ ካለፉት ታሪኮቻችን አይተናል። 

የፀጥታና የደህንነት ሃይሎች ተግባር ሃገር መጠበቅ እንጂ በሃሳብ የተለዩ ዜጎችን ማሳደድ አይደለም!!!

የምንገድልለት አላማ ባይኖረን የምንሞትለት አላማ አለን

የሚለውን ድንቅና ክቡር እመነታችሁን ወያኔ የሚያየው ህዝባችን በመግደል ፍትሃዊ ጥያቂያችሁን ማዳፈን ይቻላል በሚል ትርጓሜ ነው።ወያኔ ይህን የተቀደሰ የነፃነት ጥያቄ፣ እምነታችሁንና እንዲሁም ቅንነትና ትእግስታችሁን ለእናንተ የሚመጥን ስልጡን ምላሽ ማፈላለጊያ አድርጎ አያየውም። አላየውም።
ምላሹ ደግሞ በሰላማዊ ለውጥ ላይ በር የዘጉ፣ አመፃን በራሳቸው ላይ ይጠራሉ፣ውድቀታቸውም ስለሚናፍቃቸው ማሳየት ተገቢ ነው።ያለበለዚያ የመቶ አመት የቤት ስራ በላያችን ላይ መፍጠር ነው።

ለነፃነት ታግሎ ነፃነት ማግኘት ከተጠያቂነት መዳን ነው።

ድል ነፃነቱን ላጣው ኢትዮጵያዊው ወገኔ !!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment