አንድ ወዳጄ ይኼንን የአቅጣጫ ሰላምታ እንደማይወደው አጫውቻችሁ አውቃለሁ? ለምንድን ነው ስለው ‹‹የሰው ልጅ እንደ ንፋስ በአቅጣጫ ላይ ተመሥርቶ ሰላምታ ሲለዋወጥ እበሽቃለሁ፤›› አይለኝ መሰላችሁ? የዘንድሮን ሰው የሚያበሽቀውን ነገር ብዛት ቆጥረን መጨረስ አቃተን! ግን ግን ንፋስን ለምንከተል የዘመኑ ሰዎች ይህ ሰላምታ ካልተሰጠ ለማን ይሰጥ? ለራስ ብቻ የሚሮጥበት ዘመን መሆኑን ካየን ዘንዳ ከዚህ ሌላ ምን ይባላል? አንዳችን ያለ ሌላችን መኖር እንደማንችል እያወቅነው ‘እኔ’ን ብቻ ላማከለ ነፍስ መሮጣችን ይገርመኛል። የሚገርማችሁ ደግሞ አባባልን እንኳ መርጠን አለመጠቀማችን ነው።
ለምሳሌ ‹‹ዘመኑ የውድድር ነው›› የሚለውን አባባል ለተቀደሰ ይሁን ለረከሰ ተግባር እንደምንጠቀምበት ሳንለይ ለሁለቱም እንዳሻን እንገለገልበታለን። አሁንማ ሙሰኛውም በሰሞነኛ ተቆጣጣሪዎች ሲያላግጥ ‘ዘመኑ የውድድር ነው’ ማለት ጀምሯል አሉ። ‹‹ውድድሩ ጤናማ ዕድገት ለማስመዝገብ ነው? ወይስ እንደተለመደው ጠልፎ ለመጣል ነው?››
ሌባ ቀጪ አጥቶ ለሕዝብ አገልግሎት በሚውል ገንዘብ ደልቦ ሲንጎማለል ይውላል(ህውሃት/ወያኔ)። ተጠቂው ሰፊው ሕዝብ አቧራ ለብሶ ለዕለት ጉርሱ ይማስናል(የኢትዮጵያ ህዝብ)። ለምሳሌ ‹‹ዘመኑ የውድድር ነው›› የሚለውን አባባል ለተቀደሰ ይሁን ለረከሰ ተግባር እንደምንጠቀምበት ሳንለይ ለሁለቱም እንዳሻን እንገለገልበታለን። አሁንማ ሙሰኛውም በሰሞነኛ ተቆጣጣሪዎች ሲያላግጥ ‘ዘመኑ የውድድር ነው’ ማለት ጀምሯል አሉ። ‹‹ውድድሩ ጤናማ ዕድገት ለማስመዝገብ ነው? ወይስ እንደተለመደው ጠልፎ ለመጣል ነው?››
ፍትሕ የናፈቃት ዓለም።
በየጥጋጥጉ ዲስኩር ብቻ ተለጥፎ ይነበባል! ይነበነባል! ‹‹አሁንማ የሰለቸኝ መፈክር ማንበብ ነው፤›› ፡፡ ‹‹ለምን? ትሉኝ ይሆናል›› ‹‹በመፈክር ውስጥ የተሸጎጡ በርካታ ውሸቶች አሉ፤››
አሁንማ ውሸት ጆሮዬን አደነቆረው፡፡
ባለፈው ሰሞን አንድ የመንደራችን ጎበዝ ተማሪ ‹‹እኔ ከእንግዲህ ወዲያ ትምህርት የሚባል በቃኝ አቅለሸለሸኝ፤›› ብሎ አቆመው ተብሎ ሲወጣ ሲገባ የሠፈሩ መጠቋቆሚያ መሆኑን ሰማሁ። አንድ ቀን ከጓደኛዬ ጋር ሆነን ልጁ ከሩቅ ሲመጣ አየነውና ጨዋታ ጀመርን። ‹‹ይኼ ልጅ በቃ ትምህርቱን ተወው?›› አልኩት ጓደኛዬን። ሽምግልና የተላከው እሱ ስለሆነ ሚስጥሩን ማወቁ አይቀርም በሚል። በነገራችን ላይ ምሁሩ ጓደኛዬ ለመሰለው ነገር የሠፈሩ ቀንደኛ ተመራጭ መካሪና አግባቢ ነው። አሳክቶ መናገሩን ይችልበታል። አሳክቶ መናገሩን እየቻሉበት ስንቱን ከገደል አፋፍ መመለስ የሚችሉ እያሉ በዝምታቸው ምክንያት ስንት ትውልድ ጠፋ ይሆን?
‹‹አይ አንቺ አገር! ይብላኝልሽ ወልደሽ የወላድ መካን እንደሆንሽ ሁሉ ልጆችሽ እያሳመሙሽ ስትኖሪ። ስንቱ በላዩ ላይ በሩን ዘግቶ ተኝቷል መሰለህ ? የጋን መብራቱን አትቁጠሩት››
ኢትዮጵያ በምሁር ልጆችዋና በተፈጥሮ ሀብት ክምችቷ ምንም አልተጠቀመችም ከማለት ቦዝነን አናውቅም ። እውነታችንን አይደል ታዲያ? አውቃለሁ ባይ እንጂ እስቲ እንሰማማ የሚል የለም። ቆርጦ ቀጥል ተሰብስቦ ዕውቀት አሳፋሪ መስሏል። በአስተሳሰብ ድህነት ስንጠወልግ ግድ የሚለው መጥፋት ነበረበት? ኧረ ወዴት ነው እየተጨካከንን የምንጓዘው? አንድ የማውቀው ሰው፣
‹‹ ነዳጅ ላይ ተቀምጠን የምንራበው እኮ አገሪቱ ላቧን ጠብ አድረጋ ያስተማረችው ስለተኛ ነው፤›› ያለኝን አልረሳውም፡፡
እናም ጓደኛዬ እንዲህ አለኝ። ‹‹የትምህርት ቤት ዲስኩር ሰልችቶኛል። ተግባር ላይ የማይውል ቢቀር ምን ይጎዳል? ህሊናዬን እየኮሰኮሰኝ ለአገር ዕድገት የማይጠቅም ትምህርት ከምማር ድንጋይ መፍለጥ ይሻለኛል ብሎ አመፀ፤›› ሲለኝ ገረመኝ።
ጎበዝ! እንዲህ ያሉ ጠያቂ ታዳጊዎችን እንዴት እያስተናገድናቸው ይሆን? ነገሮችን አብራርተን በማስረዳት ወይስ ‘ለራስህ ስትል ተማር’ እያልን? ጓደኛዬ እንደሚያጫውተኝ ከሆነ ይኼን መሰል ጥያቄ የሚያነሱ ንቃተ ህሊናቸው ከፍ ያለ ተማሪዎች በአግባቡ ከተያዙ ዛሬ አለ የሚሉትን ችግር ነገ አድገው መቀየራቸው እንደማይቀር ነው። ለውጥን በአንድ ጀንበር ካላደረግን ብለው ሲያደናብሩን ስንቶች ወደ ኋላ ጎተቱን መሰላችሁ?
ትውልድ ቀርፆ በትውልድ ውስጥ የነገዋን እናት አገር ሰፋ አድርጎ ተመልካቹ ጠፋ።
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment