ዳዊት መላኩ፣ ጀርመን
ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ባለፈው አንድ ወራት ፈጣሪያቸውን በጾም በፀሎት ተወስነው ሲማጸኑ የቆዩ የእስልምና እምነት ተከታዮች የኢድአል ፈጥርን በአል ለማክበር ሀገር አለን እምነት አለን ብለው በተለመደው መልኩ ሀይማኖታዊ በአላቸውን ለማክበር ወጥተው የቀሩተን፤አሁንም በእስራት ላይ የሚገኙትን እና በአደባባይ ሰውንም ፈጣሪንም በማይፈሩ አረመኔያዊ ፍጡራን የተቀጠቀጡ እናቶች፤ እህቶች፤ ወንድሞች ፤ህፃናት እና አረጋውያን የደረሰባቸውን ስቃይ ለመጋራት ነው፡፡
ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ እያሸበረ አሸባሪ ሲል ፤እየገደለ ገዳዩን ሳይሆን ወገኑ የተገደለበትን ንጹሃን ዜጎችን ሲያስር እንደሚቀጥል ምስክር መጥራት ሳያስፈልግ በየቀኑ የምናው ያደባባይ ሚስጥር ነው፡፡
ዛሬ ያልታሰረ ነገ ሰበብ ተፈልጎለት እንደማይታሰር፤ ዛሬ ድብደባና እንግልት ያልደረሰበት ነገ እነደማይደበደብ፤ዛሬ ያልተገደሉ ነገ እንደማይገደሉ፤ዛሬ ያልተፈናቀሉ ዜጎች ነገ እንደማይፈናቀሉ ፤ዛሬ ንብረቱ ያልተዘረፈበት ነገ መጥተው እንደማይዘርፉት፤ ዛሬ ከስራው ያልተፈናቀለ ነገ እንደማያፈናቀሉት ፤ዛሬ ከወያኔ ጉያ ተወሽቀው ህዝቡን እያሰቃ ያሉ ሆድ አምላኪዎች የፖለቲካ ታማኝነታቸው ጥያቄ ምልክት ውስጥ ሲገባ እንደማይታሰሩ ምንም ዋስትና የላቸውም፡፡
ባሳለፍናቸው 22 የጨለማ ዓመታት የወያኔን አረመኔያዊ ተግባራት ከኛ በላይ መናገር የሚችል ካላ ለቀባሪ ማርዳት ነው የሚሆነው፡፡እንግዲህ ባጭሩ የወያኔ ዘረኛ አንባገነን መንግስት በስልጣን እስላከ ድረስ እስራት፣ ግድያ ፣ስደት ፣እንግልት ፣ዘረፋ እና መሰል ተግባራት ከኢትዮጵያውያን ጀርባ ላይ ይወርዳሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ወያኔ ሁሉንም ነገር ከስልጣን ለይቶ ለማየት ስላልታደለ በስላጣኑ ዙሪያ ስጋት ነው ብሎ ያሰበውን ሁሉ እያስወገደ ይቀጥላል፡፡ለማንኛውም ሀገር እና ወገን ወዳድ ዜጋ ሁሉ ሁለት አመዘራጮች ከፊቱ ይጠብቁታል፡፡ አንድም ሁሉንም ሰባዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በዘረኞች አሰነጥቆ በባርነት እንደጭቃ ሲረገጡ መኖር ወይም የተነጠቅነውን ነፃነታችንን በጋራ ትግላችን ማስመለስ፡፡ነፃነት ደግሞ ያለ መራራ ትግል እና መስዋዕትነት ሊገኝ ስለማይችል ዛሬ ግድያ ፣እስራት፣ እንግልት ያለደረሰባችሁ ወገኖች የእናንተም የነገእጣ ፈንታ ተመሳሳይ በመሆኑ “ጎለቤት ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ “እንደተባለው በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን ግፍና በደል በጋራ በማውገዝ ይህ አስከፊ ስርዓት እንዲወገድ ካላደረግን በየተራ ሞተን ማለቃችን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር!
ሞት ረግጠው ሊገዙን ለሚፈልጉ እንባገነኞች!
ሞት ረግጠው ሊገዙን ለሚፈልጉ እንባገነኞች!
No comments:
Post a Comment