Wednesday, August 7, 2013

ስደት ድህነት ነው ድህነት የብልሹ ፖለቲካ ስርዓት ውጤት ነው

በግሩም ተ/ሀይማኖት
በጨለማ ውስጥ የምትዳክረው የየመኗ ዋና ከተማ ሰነዓ ሆኜ ስንቱን ጉድ አየሁ፡፡ ስንቱ ስደተኛ ላይ የደረሰውን እያየሁ አለቀስኩ፡፡ ኡኡኡ….ድረሱ አልኩ፡፡ኢትዮጵያን እንወዳለን የምትሉ ሰዎች ህዝቡን ሳይሆን ባዶ መሬቱን ድንጋይ አፈሩን ነው እንዴ የምትወዱት ወገን አለቀ ድረሱ…ብያለሁ፡፡ ተመስገን ዛሬ ከስንት ሺዎች እልቂት በኋላ የሚደርስ ባይሆንም ሰሚ መገኘቱ ደስ ይላል፡፡ ለወሬም ቢሆን ተሰምተናል፡፡ ባይሆን ፕሮግራሙን ያየ እንኳን ሊማርበት ይችላል እና ብራቮ ኢቲቪ….ተመስገን ስለተረፍኩ ዛሬ ለስንቱ እልቂት ምስክር ሆኛለሁ፡፡ ሰነዓ መብራት ችግር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ኩራዝ ለኩሳ በጀኔሬተር ጩኸት (ባንድ) የምትታጀብ ጭል..ጭል በሚል ደብዛዛ ብርሃን ያላት ሰፊ ናይት ክለብ ትመስላለች፡፡ ብቅ ጥልቅ የምትለው መብራት ተራዋ ለእኛ ሆነና እውነት ባይኖር እንኳን ዘፈን አይጠፋም፡፡ አንዳንዴም ምን ዋሹ የሚለውን ለማየት ኢቲቪ ከፈትኩ፡፡ ከዜና በኋላ ስለስደት ለየት ያለዝግጅት እንደሚያቀርቡ ማስታወቂያውን ሰምቼ ጠበኩ፡፡ ዘ-ይገርም ነው፡፡ ግን ሁሌ ከቀብር በኋላ ማሸርገዳችን..ልታይ ልታይ ማለታችን እስከመቼ ይሆን የሚቀጥለው?

ፕሮግራሙ ሲጀምር ግን ይሄ ሁሉ ተቆርቋሪ መስሎ መታየት ፈላጊ እስከዛሬ የት ነበር? ብያለሁ፡፡
ሌሎችንም የት ነበሩ አስብሏል፡፡ እውነት ለህዝብ ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት ካልሆነ በስተቀር ከዚህ በፊት ኧረ!...የወገን ያለህ ይህን ያህል ዜጋ አለቀ ስንል ምነው ምላሽ የሚሰጠን ጠፋ? አንድ በሉ፡፡ ይህን ያህል ዜጋ ታፍኗል፣ 14 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ሀረጥ የሚባለው ካምፕ ውስጥ ታጉረው ወደሀገር የሚመልሰን ጠፋ ሀገራችን መልሱን ብለው ሰላማዊ ሰልፍ እስኪወጡ ድረስ በርሃብ ሲቆሉ…ሲረግፉ መልስ መቼ ሰጡ? ሁለት በሉ፡፡ በስንት ሺህዎች በየጎዳናው እስኪረግፉ ቀባሪ አጥተው በየመንገዱ ወደቁ ኧረ የሰሚህ ያለህ ስንል ዝምታው ለምን ነበር?

አሁንም ይሄ ሁሉ አታሞ ድሰቃ እውነት ለስደተኛው ሊሰራ ታስቦ ከሆነ አልረፈደም፡፡ ግን ከልብ አለመለቀሱ እነሱ ውይይት ብለው በተቀመጡበት ቀን እዚህ የመን ውስጥ ስንቶች በአፋኞች መከራቸውን እየበሉ ነው? ስንቶች ተደብድበው አካላቸውን አጥተዋል? እውነት ድንበሩ ከተዘጋ በዚህ ሳምንት ብቻ ወደ የመን የተሻገረው ህዝብ ብዛት በሺህዎች መሆኑ እና የIOM (ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት) ሰራተኞች ከቁጥጥራቸው ውጭ መሆኑን ማሳወቃቸው ምን ያሳያል፡፡ ዛሬም እየተዋሸ ፖለቲካዊ ድስኮራ መሆኑን አያሳይም? ተሰብስቦ ከማውራት ወደ ተግባር መሸጋገር ነው የሚያስፈልገው፡፡

በዚሁ ውይይት ላይ ጭርስ አንዳንዶች ዛሬም የሚያወሩትን የሚያውቁ ሆነው አልታዩም፡፡ ስለቻይና እድገት ባልተያያዘ መልኩ የከተማልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ ብዙ አወሩ፡፡ ባለ ሁለት ዲጂት ተከታታይ እድገት አስመዘገበች በተባለው ኢትዮጵያ ድህነት የለም ለማለት ሞከሩ፡፡ በድህነት አይደለም የሚሰደዱት አሉንም፡፡ እግዚአብሄር ይስጣቸው አንባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሆዳቸው ብለው የአይጥ ምስክር…ያስባሉንን እውነቱን ነገሯቸው፡፡ ሁለቱን ነጣጥለን አንመልከት ድህነት አይደለም ያሰደዳቸው ማለት ስህተት ነው አሉም፡፡ የውይይት አቅጣጫውን ግንዛቤ በማነስ ስደት እንደሚወጣ ለማድረግ የሞከሩ ሰዎች በዝተው መታየታቸውና እንዲያውም በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ መሆናቸው መናገራቸው ደግሞ ድራማውን አስቂኝ ያደርገዋል፡፡ ጥናት ቢያደርጉ እውነት ይሄን ነበር የሚናገሩት? ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ቢያገላብጡ የውጭ መገናኛ ብዙሀንን ቢከታተሉ እንኳን ችግሩ ገብቷቸው ይናገሩ ነበር፡፡ ግን ባልሰሩት፣ ባላዩት ጥናት አቅራቢ ሆነው ለተከራከሩት ሰዎች አንድ እውነት አስረግጬ ልነግራቸው ወደድኩ፡፡

እህቷ ሞታ በተሰጣቸው ገንዘብ ሌላኛዋ እህቷ ሄደችበት ብሎ ግንዛቤ ማጣት ነው ያለው ጥናት አቅራቢ በምን አስቦት ነው፡፡ ሲዋሽስ በልክ ቢኮን ምን አለበት ከአረብ ሀገር ሞተው ሬሳ ሲገባ ወይም መቀበራቸው ሲነገር ገንዘብ የሚሰጠው ማነው መንግስት፣ አረቦቹ ወይስ ራሱ ከኪሱ ሰጣቸው..ይሄ ራሱ የግንዛቤ ማጣት ነው፡፡ ቢያውቅ እንዲህ አይነት ውሸት አይዋሽም ነበር፡፡ ሊቢያ በጋዳፊ ቤተሰቦች እንደዛ ለሆነችው መሰረት..ሉብናን በአደባባይ ከቆንስላው በር ላይ ተወስዳ ለሞት የተዳረገችው አለም ደቻሳ መገናኛ ብዙሀን የዘገቡላት እንኳን ቢሳቤስቲን አላገኙም፡፡

እሺ ጥናት አድርጌያለሁ ባዩ እንዳለው ይሁን (ውሸቱን እውነት እንበለው)እና የሟች እህት ግንዛቤማ በደንብ አገኘች በእህቷ ሞት ተማረች፡፡ ግን ችግር ሲፎክታት መጻኢው ጨለማ ሲሆንባት ርሃብ ሲዘምትባት ብሞትም ልሙት ያስባላት ችግር፣ ረሀብ መሆኑን እንዴት አይታሰብም? ‹‹ረሀብ ስንት ቀን ይሰጣል..›› የሚለውን የሎሬየት ፀጋዬ ግጥም ማሰብም ያስፈልጋል፡፡

ግንዛቤ ማጣትም ሆነ ገንዘብ ማጣት ሁለቱም ደህነት ነው፡፡ ስደት በየትም አልነው በየትም አሽሞነሞነው ስደት ድህነት ነው፡፡ ድህነት ደግሞ የብልሹ ፖለቲካ ስርዓት ውጤት ነው፡፡ ሰላም አጥቶ መብቱ ተረግጦ የሚሰደደው ኪሱ የዳለበውም ቢሆን የሰላም ደሀ ሆኖ ነው፡፡ ሌላ ታፔላ መለጠፉም ሆነ ማሽሞንሞኑ ስደትን አያጠቁረውም አያቀላውም፡፡ ጥናት አጥንተናል ባዮችም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ነውና ይልቅ የመፍትሄ ሀሳብ አቅርቡ…ህገ-ወጥ ደላሎች ያላቸውን ተዋረድ እና ሰንሰለት መናገሩ ብቻ ምን ፋይዳ አለው፡፡ እዚህ የመን ያለ ኤምባሲ ስንት የሚያዙትን ህገ-ወጥ ደላሎች ሲፈቱ ዝም ከማለት ውጭ ምን አደረገ? አሁን በቅርቡ ያየነው እንኳን ስልሳ ኢትዮጵያዊያንን አፍኖ የተያዘ ሰው ሲፈታ ዝም አይደል ያሉት ያውም ከነደበደባቸው 60 ልጆች ተይዞ እሱ ወጥቶ ልጆቹ ታስረው ቀርተዋል፡፡ አሁንስ ቢሆን በየመን ህገ-ወጥ አጓጓዦች ከኤምባሲው ምን ደረሰባቸው ገብተው ይወጣሉ፡፡ እጅና ጓንት ናቸው፡፡

ብቻ ሁሉ የይምሰል ነው፡፡ እውነቱን አሁንም ያለውን በተከታታይ ለማሳየት እሞክራልሁ፡፡እዚሁ ፌስ ብክ ላይ ይህን በተመለከተ ሰፍሮ ያገኘሁትን ሁልተ ፅሁፍ እነሆ…

1…. "ጩኸቴን ቀሙኝ"
ሰሞኑን ETV ሰለስደት ፕሮግራም ማስተላለፉን ተያይዞታል በቃ የኛ መንግስት ሁሉ ነገር ለፓለቲካ ጥቅም እንጂ ለሀገር:ለህዝብ ተብሎ የሚሰራው ነገር የለም ማለት ነው ?
የተለያዩ ሰዎች የኢትዮጵያዊያንን የስደት ስቃይ በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ ሰሚ አጥተው እንደውም ያን በመግለጻቸው የመንግስት ተቃዋሚ እየተባሉ በየመንግስት ባለስልጣኖች ማስፈራሪያ ሁሉ ይደረግባቸው ነበር ታዲያ ዛሬ ምን ተገኘና ነው መንግስት የህዝብን ጩኅት መልሶ ለህዝብ የሚያሰማው ?
ይህ ነገር ችግሮቹ ብዙ ቢሆንም የችግሮቹ መንሴዎችን የአንበሳ ድርሻውን የሚወስደው ያው የራሱን እንጂ የህዝቡን ድምጽ አልሰማም ብሎ ያስቸገረው መንግስት ነው :: ሁሉን ነገር ያበላሹ እና ሲበቃቸው ይሁን ወይም ለፓለቲካ ፍጆታ ለማዋል ሲሉ ያው የተለመደው በETV ሰዎቹን ሰብስቦ ለቅሶ ይቀመጣል:;ይህ ከዚህ በፊት ለሞተው ለተሰቃየው ምን ይጠቅመዋል ? መንግስታችን ከዚህ በፊት ሰዎች ሲጮሁ ለምን ለመስማት አልፈለገም? አሁንስ እውነት እርምጃ ለመውሰድ ነው ወይስ ያው እንደተለመደው ለፓለቲካ ፍጆታ ለማዋል ብቻ ? ለምን በህዝብ ይሾፋል ግን ? እያንዳዳቸው መሪ ቦታ ላይ ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስተሩ (ነኝ ካሉ) ጀምሮ ይህን ችግር ከዚህ አራት እና አመስት አመት በፊት ያውቁታል መፍትሄ ለመፈለግ አይደለም ችግራችንን (የስደተኞችን) ሰምተው ከቁብ አልቆጠሩትም ነበር ለ ETV ሲሆን ግን ዶክመንተሪ ሰርተው ለቀቁልን ? ልክ ዘፋኞቻችን ነጠላ ዘፈን እንደሚለቁት ማለት ነው :: የተውሰነ ቀን ይሰማ እና ይረሳል ! እስቲ ሌላው ቢቀር በየሀገሩ ያሉ ኤምባሲዎች የመንግስትን ተቃዋሚ ከሚያሳድዱበት ጊዜ በጣም ትንሹን 3/4 እንኳን የዜጋቸውን መብት የሚከበርበትን ሆኔታ ያመቻቹ ነገሮች በ ETV ሰለቀረበ ተቀረፈ ማለት አይደለም እውነት ችግሩን ለመቅረፍ ታሥቦ ከሆነ በየሀገሮቹ ካሉት ዜጎች ጋር የሚወያይ ልዕኳን ያስፈልጋል ለገንዘብ መሰብሰብ ሲሆን ልዕኳን ሳይሆን ልዕኳኖች ነው የሚላከው :: ይቅርታ በንዴት መንፈስ ነው የጻፍኩት ከዚህ በላይ ብጽፍ መጥፎ ስለሆነ እዚሁ ላይ ላብቃ ከተረጋጋሁ እቀጥላልሁ ለማንኛውም ግን ዘግይቶም ሆነ ለፓለቲካ ፍጆታ ETV ይህንን ዝግጅት በማቅረቡ መንግስታችን ባይማር እንኳን ህዝቡ የሚማረው ነገር ሊኖር ይችላል እና እናመሰግናለን ::
2………ማፈሪያ የሆነው ETV ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በሚል ዶክመንተሪ የሚመስል ነገር አሳይቶናል፤በጣም የሚያሳዝን ነው።ስለ ወገንም የማያዝን ልብ የለንም።ነገርግን ይህ ስርሃት አልበኛ መንግስት ያወጣው ወገንን የመፍጀት ስትራቴጂ አንዱ አካል ይመስለኛል፤ለወገን ተቆርቓሪም ሆኖ አይደለም ይህንን ዶክመንተሪ ያሳየን።
ወገኖቻችን ለምንድነው ለዚህ አደጋ ራሳቸውን የሚያጋልጡት?
ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን እያወቁ ለምን ይህን አደጋ ይጋፈጣሉ?አማራጭ ማጣት ነው።
ህዝቡ ተስፋ እንደቆረጠ ያሳያል፤እንጂ ወያኔዎች እንዳሰቡት ምንም ትርፍ አያመጣም።
ምነው በየአረብ አገራቱ ከደረሱ በኇላ እንኯን ቆንስላ ፅ/ቤት ሄደው አቤቱታቸውን እያሰሙ ለ3ናለ4 ቀናት በየቆንስላው በር ላይ ተቀምጠው የሲሚንቶ ቅዝቃዜና ውርጭ ሲፈራረቅባቸው እያዩ አላየንም ነበር ሊሉን አስበው ይሆን?
ታዲያ አሁን አዝነናል ለማለት በምን ሞራል ነው የሚነፋረቁት?

No comments:

Post a Comment