Friday, August 2, 2013

የቀባሪን ልብ የሰበረ የሕይወት ታሪክ (ከአዲስ አበባ)

ይሄይስ አእምሮ
ወያኔዎች በጣም እየከፉ ነው፡፡ ክፋታቸው ጠርዝ እየለቀቀ መጥቷል፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት ወትሮውንም ወያኔዎች ጋ እንደሌለ የታወቀ ቢሆንም አሁን አሁን ግን በጣም የለየላቸው ጋጠ ወጦችና ኅሊናቢሶች እየሆኑ ነው፡፡ እነሱን በሰው ልጅነት ለመፈረጅ እንኳን በጭራሽ የማይሞከር የሚገርሙ ፍጡራን ናቸው፡፡ ይቅርታችሁንና ወያኔዎች ዞሮ የሚያይ አንገት ያልፈጠረባቸው ባልጩት ራስ መሆን አለባቸው፡፡ የሚሠሯቸውን የሕጻን አይሏቸው የዐዋቂ ሞኛሞኝ ሥራዎች ስታዩ ከዚህም በላይ ልትናገሯቸው ትችላላችሁ፡፡ ሞኛሞኝ ማለቴ የሚያደርጓቸው ነገሮች ቁልጭ ያሉ አንጎል የሚባል ያልፈጠረበት የንክር ሰው ሥራ በመሆናቸው ነው እንጂ የሚሠሩት ሁሉ እነሱን የማይጠቅም ነው ለማለት ፈልጌ አይደለም፡፡ ለምሳሌ አንድ ዓይነት አገልግሎት ለማግኘት አንድ መስኮት ላይ ሁለት ሰዎች ቀርባችኋል እንበል፤ አንቺ ትግሬ ስላልሆንሽ ዐርባ ብር ትከፍያለሽ – አጠገብሽ ያለችው ሌላዋ ደግሞ ትግሬ በመሆኗ ብቻ ዐርባ ሣንቲም ትከፍላለች፡፡ እውነተኛ ገጠመኝ ነው እየነገርኳችሁ ያለሁት፡፡

(ለምን አሁኑኑ አልነግራችሁም፡- ቀደም ያለ ጊዜ ነው፡፡ ቦታው ዋናው ፖስታ ቤት ነው፡፡ ትግሬዋ የ‹ሕዝብ አገልጋይ› ሰዎችን በየተራ ታስተናግዳለች፡፡ ነገሩ በፖስታ ቤት በኩል ለመጣ ዕቃ የሚከናወን የቀረጥ ክፍያ ነበር፡፡ አንዷ ትግሬ ለአንድ አነስተኛ ዕቃ ዐርባ ብር እንድትከፍል ስትጠየቅ ‹ቧይ! እዚ ኩሉ ቐርሺ ነቲኣ ቅሩብ ክስታይ…› ትልና በትግርኛ ሥልት ትጮሃለች፡፡ ወቅቱ ወያኔዎች የትም ሥፍራ የሚገኘውን ‹የታገሉለትን የትግራይ ሕዝብ› እንደንብና እንደተርብ እየተራወጡ በወረት የሚያገለግሉበት ስለነበር – ለነገሩ አሁንም ያው ናቸው – ያቺ መስኮት ውስጥ የነበረችው ትግሬ፣ ‹ትግራዋይ ዲኺ? እንተኾንክን አየናይ ወገን?› ብላ ትጠይቃታለች፡፡(‹ትግሬ ነሽ እንዴ? ከሆንሽ ትግራይ ውስጥ የት ቦታ?› ማለቷ ነው) እርሷም ትግሬ መሆንዋን፣ ከትግሬም ዋናው የወቅቱ ነገሥታት መፍለቂያ ዐድዋ ውስጥ መሆንዋን እንደእፉኝት በመነፋፋት በኩራት ትነግራታለች፡፡ ያኔ ዐርባ ብር የተጻፈበትን ወረቀት አምጪው ብላ ትቀበላትና እሱን ‘void’(ዋጋቢስ) አድርጋ ዐርባ ሣንቲም ትጽፍና በራሷ ታሪፍ ታስከፍላታለች – ትግሬ ናታ! ተገልጋይዋም ትግሬ ነቻ! ይህች ትንሽዬ ግን እውነተኛ ታሪክ ናት፡፡ ውስጧ ግን የጊዜውን የወያኔ ኢትዮጵያ ቁልጭ አድርጋ ታሳያለች፤ በጉምሩክ አካባቢ፣ በአየር መንገድ አካባቢ፣ በምርትና አቅርቦት አካባቢ፣ በንግዱ አካባቢ፣ በባንኮች አካባቢ፣ በግንባታው አካባቢ፣ በምግብና መጠጦችና በሸቀጦች አካባቢ፣ በጨረታ ግዢና ሽያጭ አካባቢ፣ በትምህርት አካባቢ፣ በመሬት አስተዳደር አካባቢ፣ በኮንዶምኒየም ቤቶች ዕደላና ክፍፍል አካባቢ፣ … ስንቱ ተጠቅሶ … ብቻ በሁሉም አካባቢ የትግሬው የገዢ መደብ ሌሎችን በሰማይ ጠቀስ ዋጋ እየገረፈና ከጨዋታው ሜዳ እያስወጣ ለትግሬዎች ብቻ መቆሙን ስናይ ‹እነዚህ ሰዎች በርግጥ ሰዎች ይሆኑ ይሆን ወይንስ ሰው ለመሆን የሚቀራቸው አንዳንድ ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገር አለ?› ብለን ለነሱም ለራሳችንም ልንጨነቅ እንችላለን – በተፈጥሮ የሚከሰት አንዳች ጉድለት ከሌለባቸው በስተቀር እንዲህ ነፍሰ በላ ይሉኝታቢስ ይሆናሉ ብየ በበኩሌ ማመን ያቅተኛል፡፡ እርግጥ ነው ይሄ ‹ይሉኝታ› ወይም ‹ሀፍረት› የሚባል ቅመም በነዚህ ሰዎች ሰውነት ውስጥ ዜሮ መሆኑን ከተረዳሁ ቆይቻለሁ – ከዚህ የተለዬ ጄኔቲክ ጉድለት እንዳለባቸው እየተጠራጠርኩ መጥቻለሁ – ሰው በጤናው መቼም ለሥልጣንና ለገንዘብ ሲል ብቻ ወንድሞቹንና እህቶቹን እንዲሁም ሀገሩን ይህን ያህል በግፍና በበደል ያጥለቀልቃል ብዬ መቀበል በእውነቱ ይከብደኛል፡፡ [ለዲፕሎማሲ ያህል ‹አብዛኞቹ ወያኔዎች› የሚል ማባበያ ልጠቀም ይሆን?] አዎ፣ አብዛኞቹ ወያኔ ትግሬዎች እንዲህ ናቸው፤ ከመነሻው እንዲህ ያደርጉ ነበር፤ አሁንም እንዲህ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ‹ወርቃማ› ሀገርን የማጥፋት ዕድል በነሱው እጅ እስካለ ድረስም ለወደፊትም እንዲህ ማድረጋቸውን ያለሀፍረትና ያለአንዳች ይሉኝታ በስፋትና በጥልቀት እንደሚቀጥሉ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ማንን ፈርተው ሊተውት?
ወደርዕሴ ልመልሳችሁ፡፡ ባለፈው ሰሞን አንድ ተወልደ የሚባል ትግሬ ሞቶ ለቀብር ሄጄ ነበር፡፡ ሰውዬውን ሳይሆን ከሰውዬው ጋር በተገናኘ የማውቀው ሌላ ሰው ስለነበር እሱን ላጽናናና ቀብር ላይ መገኘቴን ለማሳወቅ ግምባሬን ላስመታ ነበር ወደ ቀብሩ ሥፍራ የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ያቀናሁት፡፡ እዚያ የገጠመኝ ነገር ግና አለመሄዴን የሚያስመርጥ ነበር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለመኖሬም እርግጠኛ መሆን ተሣነኝ፤ ትግሬዎች በሚባሉ ልዩ ሰብኣዊ ፍጡራን በምትመራና የነሱ ብቻም በሆነች የምናብ ሳይሆን የእውነት ሀገር ውስጥ በስደትና በግዞት የምኖር ያህል ተሰማኝ፡፡ እነኚህ በወያኔ ቡድን ሥር የተኮለኮሉ ትግሬዎች ለይቶላቸው ዐይናውጣዎች መሆናቸውን እስካሁን በእንደዚያን ዕለቱ ሁኔታ አልተረዳሁላቸውም ነበር – ግዴላችሁም አይሆኑ ሆነው ተበለሻሽተውላችኋል፡፡ እንደተለመደው በወንድሞቻቸው ጥጋብና ዕብሪት የሚበሳጩ ጤናማና ሰላማዊ ትግሬዎችን ይቅርታ መጠየቅ ካለብኝ ብዙ ሳይረፍድብኝ እዚችው አንቀጽ ግርጌ ይሄውና ጠየቅሁ፡፡
ሟች ትግሬ በደርግ ዘመን ለስምንት ዓመታት ታስሮ ተፈትቷል፡፡ የታሰረበትም ምክንያት በትግሬነቱ ሳይሆን በወሬ አቀባባይነቱና ለወያኔ በነበረው ቅርበት በደኅንነት ሰዎች ተደርሶበት እንደነበር አጠያይቄ ደርሼበታለሁ፡፡ ሞኙ የደርግ መንግሥት የዘረኝነት ባሕርይ ፈጽሞውን ስላልነበረበት – ይህን ዐረፍተ ነገር እባካችሁን ልድገመው – የደርግ ኅብረብሔራዊ መንግሥት ፈጽሞውን የዘረኝነት ጠባይ ስላልነበረው ዜጎችን በብሔረሰባቸው ምክንያት የሚያስር ወይ የሚገድል እንዳልነበረ በበኩሌ በሚገባ አስታውሳለሁ፡፡ ሰውም ሆነ ተቋም መታማት ካለበት በእውነተኛ ሥራው እንጂ በፈጠራ ወሬ ሊሆን አይገባም ብዬ አምናለሁ፤ ሰውዬው ወይም ድርጅቱ ሞተ ወይም ወደቀ ተብሎ አለሥራው ማማት ትልቅ ስህተትና ኩነኔም ነው፡፡ ደርግ የሚወቀስበትና የሚወነጀልበት ስንትና ስንት ኃጢኣትና የጭካኔ ተግባር ሞልቶ ሳለ “ዘረኛ ነበር፤ የአንድን አካባቢ ሕዝብ ለይቶ ያጠቃ ነበር” ብሎ በአደባባይ መናገር ለትዝብት ከመዳረጉም በላይ የራስን ማንነት በገሃድ አውጥቶ ማሳየት ነው፡፡ የዘመኑ ከፍተኛ ትግሬ ባለሥልጣን ጓድ ፍስሐ ደስታ አጠገብ “ትግሬዎችን አርቀን ቀብረናቸዋል!” እያለ በትዕቢትና በምፀት የሚናር የደርግ ባለሥልጣን አልነበረም፡፡ ከዚህ ነጥብ አንጻር የማፈሪያ ታሪክ ባለቤቶች ፀረ-ኢትዮጵያ ወያኔዎች እንጂ ደርግም ሆነ ከዚያ በፊት የነበሩ ኢትዮጵያውያን መንግሥታት አይደሉም፡፡
በበቀደሙ የወያኔው ሰውዬ ቀብር የታዘብኩት ነገር በቀላሉ የማይታለፍ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ታሪክ ጸሐፊዎች መዝግቡት፤ መጣጥፍ ጸሐፊዎችም ለጽሑፎቻችሁ ፈርጥ አድርጉት፤ ሕዝቡም ይወቀውና እነዚህን በመካከላችን የበቀሉ የታሪክ መጭና እንክርዳዶችን ለይቶ በተቻለው ሁሉ አምርሮ ይታገላቸው፡፡ እርግጥ ነው – የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጊዜው ያለው መሣሪያ ጸሎቱና ዕንባው ነው፡፡ ጸሎትና ዕንባ ደግሞ አንድን ዕብሪተኛ ኃይል እንዴት አድርገው ድራሽን እንደሚያጠፉ በኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ አይተናል፡፡ ክፉ የሠሩ መሪዎች የመጨረሻ ዕጣ ምን እንደሆነ በጉልህ ከታሪክ ተምረናል፡፡ በጨካኞች የሚፈስ የደም ጎርፍና የግፍ ዕንባ የሚያስከትለው መለኮታዊ መዘዝ የሥርዓት ቁንጮዎችን ሳይቀር ዘር ማንዘር ሳይወጣላቸው ተበታትነው እንዲቀሩ የማድረግ ኃይል አለው – የትናንት መለስ ዜናዊን መቅኖ አጥቶ መቅረት ያስቧል፡፡ ስለዚህ ይህ የትግሬዎች ጎጠኛ የገዢ መደብ በጀመረው የመበስበስና በብርሃን ፍጥነት የመንኮታኮት መንገድ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ትንሣኤ በቅርብ እውን እንዲሆን ሁላችን እንጸልይ፤ የሚቻለንንም ሁሉ ያለመታከት እናድርግ፡፡ መንጋቱ አይቀርምና የጠወለገ ተስፋችንን አለምልመን ሀገራችንን በጋራ ነጻ ለማውጣት እንበርታ እንጂ የተጫነብን መርግ እንደማይነሣ ቆጥረን አንቆዝም፡፡ የነሱ ዋና ተግባር ሕዝቡ የሕይወቱ ድርና ማግ ውል እንዲጠፋበትና በተስፋ መቁረጥ ማዕበል እንዲቀዝፍ ለማድረግ በሰበቡም የኛ አይደሉም የሚሏቸው ዜጎች እንደጪስ በንነው እንደጉም ተንነውና እንደጤዛ ረግፈው እንዲቀሩ ነውና ለዚህ ወጥመዳቸው ምቹ ሆነን መገኘት እንደሌለብን እንወቅ፡፡ ተስፋችንም ፈጣሪያችን ነውና ከርሱ ጋር ሆነን የምናምንባቸውንም የተቃውሞ ኃይላት በአመራር ሰጪነት አቅፈንና ደግፈን ትግላችንን ለፍሬ እናብቃ፡፡ እንዲያ ካደረግን የድላችን ቀን በዓመታት ሳይሆን በቀናትና በሣምንታት የሚቆጠር ይሆናል፡፡ …
በተወልደ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ያየሁት ጉድ ይሄ ነው – ነገር ነገርን እየጎተተብኝ ዋናውን ጉዳይ በማዘግየቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ የሰውዬው ማለትም የወያኔ ትግሬው ቀብር አለቀ፤ ለማሣረጊያ ጸሎት ወደዐውደ ምሕረቱ መጣን፤ ካህኑ ቃለ እግዚአብሔርን አሰሙ፤ ከማሣራጊያው የ‹ሥረይ ሎሙ ኃጢኣተ ሕዝብከ…› ጸሎት በፊት የሟች የሕይወት ታሪክ ይነበብ ያዘ – አንባቢው በወያኔያዊ አንደበት እንደሚከተለው ማንበቡን ቀጠለ፤ እኛም እየተገረምን ማዳመጣችንን ቀጠልን፡፡
አቶ ተወልደ እንትና በትግራይ ክልል በእንዲህ ያለ ቦታ ከአባታቸው ከአቶ እንትና ከእናታቸው ከወይዘሮ እንትና በዚህን ዓመተ ምሕረት ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ …..
የደርግ መንግሥት በትግራይ ሕዝብ ላይ በነበረው ከፍተኛ ጥላቻ ምክንያት የትግራይን ሕዝብ በጅምላ እያፈሰ ያስር በነበረባቸው የ1970ዎቹ አጋማሽ አካባቢ አቶ ተወልደንም ከመንገድ አፍሶ ማዕከላዊ በማስገባት ለስምንት ዓመታት አስሯቸዋል፡፡ …
የሕይወት ታሪክ ንባቡ በዚህ መልክ ቀጠለ፡፡ የሕዝቡን ስሜት ዘወርወር እያልኩ ሳጤነው ትግሬ ያልሆነው ሰው በተለይ ፊቱ ቅጭም እያለ ተቃውሞውን በአካላዊ እንቅስቃሴ ይገልጽ ነበር፡፡ በበኩሌ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ በወደድኩ – በአንድ ልቅሶ ሁለት ልቅሶ ይሏል እንዲህ ነው፡፡ በአንድ ሀገር ሁለት ዜጎች የሚኖሩበት ሁኔታም ፍንትው ብሎ ታየኝ፡፡ አማካሪ ማጣት እንጅ፣ የሰውዬውን ወያኔያዊ አስተዋፅዖ ለማጉላት ሲሉ እንዲህ ዓይነት ፀያፍ ነገር ውስጥ ገቡ እንጂ እንዲያ ብሎ መናገር ስህተት መሆኑን ሊረዱ በተገባቸው ነበር፡፡ እነዚህ ወያኔዎች ሕዝብን የሚንቁ በመሆናቸው ለሚናገሩት ቀርቶ ለሚያደርጉት ነገር ደንታቢስ ናቸው – ‹ሕዝብ ምን ይለናል?› የሚል አንዳችም የማስተዋል ነገር የለባቸውም፡፡ እንደዚሁ በገደምዳሜው ‹ኢትዮጵያን ከደርግ አፈና ነጻ ለማውጣትና የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት በማረጋገጥ አሁን ለምንገኝበት ዴሞክራሲ ለማብቃት በከተማ ወስጥ በኅቡዕ ካደረጉት ትግል ጋር በተያያዘ የደርግ ሥርዓት ለስምንት ዓመታት አሥሯቸዋል፡፡ ይህን ተጋድሏቸውንም ቀጣዩ ትውልድና ታሪክ ሲዘክሯቸው ይኖራሉ፡፡› ቢሉ በተሻላቸው ነበር፡፡ ለነገሩ ይህኛውም ከመጀመሪያው በባሰ የብዙዎቻችንን ልብ መስበሩ አይቀርምና ጥሩ አማራጭ ላገኝላቸው የምችል አይመስለኝም፤ ምናልባት ‹አቶ ተወልደ የቆሙለትን የሕወሓት ዓላማ በመደገፋቸው ምክንያት ለስምንት ዓመታት ለደርግ እሥር ተዳርገዋል› ቢባል የሚቀል ይመስለኛል፡፡ ያኔ የተናሩት ግን ታላቅ ትዝብትን ነው ያተረፈላቸው፡፡
ወያኔዎች ሀገርን ከመበታተንና ድህነትን ከማስፋፋት፤ መሬትን ለውጭ ባለሀብት ባወጣ ከመቸብቸብና ሀገርን ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ከማጋለጥ፣ በዘረኝነት ልክፍት ታውሮ አንዱን የበላይ ሌላውን የበታች ከማድረግ ባለፈ የማይፈልጓቸውን ዜጎች በገቡበት እያሳደዱ ከመፍጀት በስተቀር ምን ያመጡልን መልካም ነገር አለ?…
ከዚሁ ‹ታላቅ› ወያኔያዊ ቀብር በተያያዘ ሌላውና ትልቁ ትዝብት በየትኛውም የቀብር ሥነ ሥርዓት በፍጹም የማይፈቀደው የቤተ ክርስቲያኑ የማይክሮፎን አገልግሎት ባልተለመደና ሕዝብን ባስገረመ ሁኔታ ለዚህ ሰውዬ የሕይወት ታሪክ ማስነገሪያነት መፈቀዱ ነው፡፡ በዚህም ነገር ያልተደነቀ አልነበረም፡፡ ለነገሩ የሀገርን ሀብት ሙሉ በሙሉና ከላይ እስከታች ብቻውን የተቆጣጠረ ኃይል ይህችን አነስተኛ የቤተ ክርስቲያን ንብረት አለደንቡ መጠቀሙ ያን ያህል ሚዛን ደፍቶ ሊነገር የሚገባው ጉዳይ አይደለም፤ የዜጎችን ሕይወት ጨምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ሀብትና ንብረት የማን ሆነና? እንኳንስ የየካ ሚካኤልን ማጉሊያ የቅድስት ሥላሤ ካቴድራልን ግቢ እንዳለ ቀምተው በሕይወት ዘመኑ ሃይማኖት ላልነበረው መለስ ዜናዊ አስከሬን ሲሰጡትና ቤተ ክርስቲያንን በአረማውያን ሲያረክሷት፣ በብኤልዘቡሉ የመለስ ስዕል ቤተ ክርስቲያን ከእግር እስከራሷ ‹ስታሸበርቅና ስትዋብ› እዚቺው አጠገባቸው ቁጭ ብለን በዐይናችን በብረቱ እያየን ጉድ ብለን የለምን? በድኑ የት እንደተጣለ ወይም እንደተቀበረ (ተቀብሮም ከሆነ) እንኳን ያልታወቀው የዚህ መፃጉዕ ሰውዬ ሬሣ በሣጥን ውስጥ ያለ በማስመሰል ያን ሁሉ የቁጭ በሉ የሀዘን ትርዒት ካሳዩ በኋላ ወያኔዎች በሚቆጣጠሩት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በፌዴራል እየተጠበቀ ግቢው ወፍ ዝር እንዳይልበትና ለምዕመናን ሳይቀር አስፈሪ እንዲሆን ተደርጎ ካቴድራሉ የጣዖት ማምለኪያ ቦታ እንደመሰለ አሁን ድረስ አለ፤ ቤተ ክርስቲያንም በወንበዴዎች እጅ ገብታ የዲያብሎስ መንጋ በዲያብሎሳዊ ሥሮት እየፈነጨባት፣ በጎቿንም ቀበሮና ተኩላ ከሥር ከሥር እየሞጨለፉባት እንዲሁ እንደክርስቶስ በላማሰበቅታኒ የ‹ኢትግድፈኒ› ጸሎተ ምህላ ኤሎሄ እያለች ትገኛለች፡፡ ካህናቷም ለፊታውራሪ ሊቀ ሣጥናኤል እጅ ሰጥተውና በሥጋ ቅንጦት ተማርከው ከዲያብሎስ መንጋ ጋር አብረው የዛር ዳንኪራ እየረገጡ የውሸት ኑሮ እንዲኖሩ ጨካኙ ታሪክ አመክሮ የሌለው ብያኔውን አስተላልፎባቸዋል – ቢያንስ አሁንና እስካሁን፡፡ ዛሬና አሁን ያለን ብቸኛ ምርጫ ነገም ሌላ ቀን ነውና ፈጣሪ የሚያሳየንን የመጨረሻ ፍርድ በጸሎትና በትግስት መጠበቅ ነው፡፡
ይህን እውነተኛ ታሪክ የምታነቡ ወያኔዎች ግን በአሳቻ ሥፍራና ሰዓት በምታድርጓት በዚያች የምናውቃት ዝግ ስብሰባችሁ ‹አብዚ አብዚ› ተባብላችሁ ብትነጋገሩበትና ይህን በኢትዮጵያ የሃይማኖትና የባህል ትውፊቶች ላይ የምታወርዱትን መቅሰፍታዊ ውርጅብኝ ለመተው ወይም ለመቀነስ ብትሞክሩ አወዳደቃችሁን መልክ ያለው ለማድረግ ይረዳችኋልና ጊዜ ባትሰጡት የተሻለ ነው እላለሁ፡፡ ‹ምክር የድሃ ነበርሽ፣ ማን ቢሰማሽ› ሆነና ነገሩ ሰሚ እየጠፋ ተቸገርን እንጂ ‹እዩኝ እዩኝ› ያለ ‹ደብቁኝ ደብቁኝ› የሚልበት ወቅት መምጣቱ በጭራሽ አይቀርምና ቢያንስ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ብታስቡላቸው ጥሩ ነው፡፡ ዛሬ የጠገበ ነገ የሚራብ የማይመስለው የመሆኑ መጥፎ ዕጣ በሚጥልብን አእምሯዊ ሞራ እየተወናበድን ብዙዎቻችን የምንገባበት አዘቅት ከኛ ተርፎ ሌሎችን የሚጎዳበት አጋጣሚ እንዳለው በጊዜ መገንዘብና ራስን ከጠማማ መንገድ ባፋጣኝ ማውጣት ከአስተዋይ ጥጋበኛ ይጠበቃልና ወያኔዎች እባካችሁን አሁን አመሻሽ ላይም ቢሆን ከገባችሁበት የስህተት አረንቋ በቶሎ ውጡ፡፡ ዛሬ ጊዜ አላችሁ፤ ነገ ግን ላይኖራችሁ ይችላል፡፡ የሆድን ነገር አያችሁት፤ በላችሁ፤ጠጣችሁ፤ በመጠጥና በምግብ ከሰምበሌጥነት ተነስታችሁ ጌታዋን የገደለች በቅሎ ሆናችሁ፤ ሁሉን አያችሁት፤ ጎናችሁንም በሚመች ቦታ ላይ አሣርፋችሁ ሰላም ያጣ እንቅልፋችሁን ስትደቁ ይሄውና 22 ዓመታትን አስቆጠራችሁ – ምን የቀራችሁ ነገር አለ? ታዲያ በሰው ስቃይ መደሰታችሁን ከአሁን በኋላ ማቆም የለባችሁምን? በሌሎች ስቃይና እንግልት እየተደሰታችሁ እስከመቼ ልትኖሩ ትፈልጋላችሁ ? ከሰማይ ወርዶ ወይም ከመሬት ውስጥ ወጥቶ ይህን ክፉ ሥራችሁን እንድትተው ሊመክራችሁ የሚችልስ ማን ነው? ‹ሕዝቡን እስከመቼ ነው የምናስለቅሰው?› ብላችሁ ወደ ኅሊናችሁ በመመለስ ኢትዮጵያን ለመካስ የምትጀምሩት መቼ ይሆን? የኅሊና ዕውርነትና የልቦና ድንቁርና ምን ዓይነት አደጋ እንደሚያስከትልስ አስባችሁ ታውቃላችሁን?… ያሳዝናል በጣም፡፡
ግን ግን በቁማችሁም በሞታችሁም አካላችንንና ኅሊናችንን እየጎዳችሁ መቀጠሉን ከመረጣችሁ ጥጋባችሁን የሚያበርድ ነገር እንዲልክላችሁ አምላክን ከመማጸን በስተቀር ለጊዜው ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ የሁላችንም አባት ኅያው እግዚአብሔር ፍርዱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ይስጥ፡፡ ዙሪያ ገብ ዳፋው ይጠነክራል እንጂ መስጠቱ ደግሞ አይቀርም፡፡ ለማንኛውም ሁላችንንም ልቦና ይስጠንና የጋራ ሀገራችንን እንዳሁኑ በተናጠል ሳይሆን በጋራ የምንጠቀምበትን ሁኔታ እንድንፈጥር ኅያው እግዚአብሔር ይርዳን፤ አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment