የኢትዮጵያ ወይስ የትግራይ ኤምባሲ?
ዛሬ እግር ጥሎኝ በሆዳሙና በአጋሰሱ ንጉሴ ወ/ማርያም አዘጋጅነት የሚቀርበውን በስም የአገር ፍቅር በተግባር ግን «የሕወሃት ፍቅር» ራድዪ ሳደምጥ ያስተላለፋቸው ማስታወቂያዎች ግርምት ቢጭሩብኝ ነው ብቅ ያልኩት። በተለይም አሜሪካ የሚገኙት የሕወሃት ጀሌዎች ዓመታዊ በዓል (የትግራይ ፌስቲቫል) ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደሚከበር ሲያስተዋውቅ የታወሰኝ ነገር ቢኖር አባ መላ በአንድ ወቅት ከኢሳት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ላይ የተናገረው ነገር ነበር።
አዎን! የስርዓቱ የፕሮፓጋንዳ ሰራተኛ በመሆን ለዓመታት ያገለገለው አባ መላ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ውስጥ በዲፕሎማት ስም የተሰገሰጉት አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን ገልፆ ነበር። አረ! ምን አባ መላ ብቻ? … የህወሃት አባል የነበሩትና አሁን በስደት የሚኖሩት አቶ ተስፋዬ አፅብሃስ በሚኖሩበት አገር ያለውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተመሳሳይ መልኩ ገልፀውት ነበር። ለነገሩ እኔ በምኖርበት አገርም ከዚሁ የተለየ አይደለም። ታዲያ በኢትዮጵያ ስም በተከፈተ ኤምባሲ ውስጥ የሕወሃት ጀሌዎች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማፍረስ ሲዶልቱ ዝም ብለን የምናየው እስከመቼ ይሆን?
Aster Hailu
No comments:
Post a Comment