Friday, August 2, 2013

“እርምጃ እወስዳለሁ” አለች የኢህአዴግ ፌደራል ፖሊስ!

- By Nasrudin Ousman

በአገራችን የቅርብ ዘመን የፖለቲካ ታሪክእርምጃ መውሰድየሚለው አባባል ተደጋግሞ የተሰማው በዘመነ ደርግ 1960ዎቹ መጨረሻ ገደማ ነበር፡፡ በደርግ መዝገበ ቃላት እርምጃ መውሰድ ማለት መግደል ማለት ነው፡፡ እንደ እውነቱ ደርግ በወቅቱ የእርሱን ያህል ባይሆንም ጠብ መንዣ ከታጠቁና የደርግ አመራር እና ቁልፍ አባላትን ለመግደል ከሚሹ የፖለቲካ ኃይላት ጋር ነበር የተፋጠጠው፡፡ በተለይ ኢህአፓ የሚባለው የፖለቲካ ድርጅት የደርግ አመራሮችን ለመግደል ወስኖ በመንቀሳቀሱ፣ ደርግ በአፀፋው በኢህአፓ አባላት ላይአብዮታዊ እርምጃ መውሰድማለትም መግደል ጀመረ፡፡ ይህንን ውሳኔውን ለማስፈፀም በመሻትም ‹‹የአብዮታዊ ዘመቻ መምሪያ›› በሚሰኝ መሥሪያ ቤት አማካይነት አብዮት ጠባቂዎችን መልምሎ፣ አሰልጥኖ እና አስታጥቆ በአሥር ሺህዎች በሚቆጠሩ የአገሪቷን ወጣቶች የጥይት እራት አደረጋቸው፤ ማለትምአብዮታዊ እርምጃ ወሰደባቸው፡፡
ያንን ግፍ የፈፀሙት ደርጎች ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር፣ እነርሱም በቁጥጥር ስር ውለው፣ በልዩ አቃቤ ሕግ አማካይነት ክስ ተመሥርቶባቸው፣ ‹‹አብዮታዊ እርምጃ›› ስም የቀጠፏቸውና ያስቀጠፏቸውን በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደም ባይተካም፣ አብዛኞቹ የዕድሜ ልክ እስር ተፈርዶባቸው፣ በአመክሮ ከሃያ ዓመት እስር በኋላ ከእስር ተፈትተዋል፡፡

ይህ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ገና በወጉ ተጽፎ እንኳ ሳያልቅ፣ እነ በረከትን የመሰሉ ከደርግ አብዮታዊ እርምጃ የተረፉ ኢህአፓዎች፣ ዛሬ መንግሥት ሁነው፣ የደርግየአብዮታዊ ዘመቻ መምሪያአቻ በሆነውየፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንአማካይነትህገ መንግሥታዊ የእምነት ነፃነታችን ይከበር!” እያሉ በየመስጂዱ ስለ ፍትኅና ስለ ሕግ የበላይነት መከበር ድምጻቸውን የሚያሰሙ ሰላማዊ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላትን እርምጃ እወስዳለሁለማስፈራራት አቆበቆቡ፡፡ የደርግአብዮታዊ እርምጃጠባሳ ሳይሽር፣ ዴሞክራሲን አመጣሁላችሁ እያለ የሚገበዘው ኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ እርምጃየዛሬውን ዘመን ወጣት ትውልድ ሊያስፈራራ ሲሞክር አያሳፍርምን?

ኢህአዴጎች እንዲያውቁት የምንፈልገው አንድ እና አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊም ኅብረተሰብ ማንንም የመግደል ፍላጎትም፣ ዓላማም፣ ምክንያትም የለውም፡፡ ነገር ግን በኢህአፓ ስር የተሰባሰቡ የአገራችን አፍላ ወጣቶች ከተሰዉለት ዓላማ እጅግ፣ እጅግ የላቀ የምንሰዋለት ቅዱስ ዓላማ አለን፡፡ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት በግልፅ ለተደነገገው የሃይማኖት ነፃነታችን በምልዓት መከበር የጀመርነውን ሰላማዊ ትግል፣ በአላህ ፈቃድና እገዛ ማንኛውንም መስዋዕትነት ከፍለንም ቢሆን በድል እንወጣዋለን፡፡ የእናንተአብዮታዊምይሁን፣አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ እርምጃለዚህ የተቀደሰ፣ ሕጋዊና ፍትኃዊ ዓላማ ከምናደርገው ፍፁም ሰላማዊ ትግል አንዲት ጋት ፈቀቅ አያደርገንም፡፡ ጌታችን አላህ ጥራት ይገባዋል፡፡ እርሱ (..) የታላቆች ታላቅ፣ ጌቶችሁሉ ጌታ ነው፡፡ ኢንሻአላህ የነገውን የጁሙአ ሶላት ፍልዉሃ አቅራቢያ በሚገኘው ተውፊቅ መስጂድ እሰግዳለሁ፡፡ በአላህ (..) ፈቃድ ሰግጄ እንዳበቃሁ፣ በፍፁም ዝምታ፣ በፍፁም ፀጥታ ብሶቴን እጮሃለሁ፡፡ መንግስት ባይሰማኝ፣ ጌታዬ አላህ (..) ይሰማኛል፡፡ እርሱ የተበዳይን ልመና ሰሚ ነውና፡፡ በእርግጥም ድልን ከአላህ (..) ዘንድ ብቻ እንጂ ከማንም አንጠብቅም፡፡

አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment