Wednesday, August 14, 2013

ማቆሚያ የሌለው የኢህአዴግ አፍሶ የመልቀም አባዜ

ኢንጂነር ረዲ ዘለቀ
ዛሬ የመቀሌ ከተማንና የአዲስ አበበ 22 አከበቢ ትንሽ ልበለችሁ። የመቀሌ ከተማ ግሮሰሪዎችና የአዲስ አበባ 22 አካባቢ በርካታ የሚያመሰስላቸው ነገሮች አሉ። የትግራይ ክልል ከትሞች አብዛኛው ስም የተረፋቸው በኢህአዴግ ያልተጠቀሙ ለሌላው ግን የተሻለ ሥራ የተሰራላቸው የሚመስሉ ምስኪን ከተሞች ናቸው። በአሁኑ በርካታ የራያ ክልሎችን ወደትግራይ ክልል የተጠቃለሉ ሲሁን ወደ መቀሌ ሲሄዱ ከራያ ክልል በስተቀር አብዛኛው ወጣ ገባና ተራራ የሆነ ክልል ነው። የአላማጣን ከተማ ወጣ እንዳሉ ኮረም ከመግበትዎ በፊት ያለው ወጣ ገባና ጠመዝማዛ መንገድ ሲያዩት ከየት ወዴት እየሄዱ እንደሆነ ግራ ይገባዎታል። ብዙ ተጉዘው መንገዱን ሲያዩት ተመልሰው ከዚያው ነዎት። 

ከፊትዎም ይሁን ከኋላዎ ያለውን መኪና ዞር ብለው ሲያዩት ከፊትዎ የነበረው ከኋላዎ ከኋላዎ የነበረው ከፊትዎ ያለ ይመስልዎተል። አስገረሚ መንገድ ከኮረም ወደ አላመጣ ሲመጡ አላማጣ ሲገቡ የሚየልቀው ጠመዝማዛ መንገድ በተንጣለለ ሜዳ ላይ የተመረተች ውብ ከተማ የሚያገኙ አይመስልዎትም ነበር።
ሆኖም ለጥ ባለው ሜዳ ላይ የተመሠረተች አላማጣን ከዚያ እንደ እንባዞሬ ከሚያሽከረክር ጠመዝማዛ መንገድ ሥር ሲያገኙዋት ይገረማሉ። በደዚያም ሲሄዱ እንዲሁ ጠመዝማዛውን መንገድ እንደጨረሱ የውቦቹን ከተማ ኮረምን ያገኙዋታል። ከዚያም ብዙ ተጉዘው ማይጨው ይደርሳሉ የማይጨውን ቅዝቃዜ ሲያዩት አባቶቻችን ያንን ውርጭ ከጣሊያን አውሮፕላን ከሚወርደው ቦንብ ጋር እንዴት እንደቻሉት ሲያስቡ የጀግና ልጅ በመሆንዎ ኩራት ይሰመዎታል።

መቀሌ ከተማ የደጎችና እንግዶችን ለመስተናገድ የተፈጠሩ ሰዎች ከተማ ነች።በመቀሌ ማንም እንግዳ ሆኖ አይቸገርም። መቀሌ የሚፈልጉትን ቦታ ሲጠይቁ በጥቆማ የሚያሳይዎት ሳይሆን ከሚፈለጉት ቦታ የሚያደርሱዎት በርካታ ሰዎች ያሉባት ከተማ ነች።በመገረጃቸው ተጋርደው እንግዳ የሚጠብቁት የመቀሌ ከተማ ግሮሰሪዎች ፈገግታ ከማይለያቸው ባለቤቶችና አስተናጋጆች ጋር በየዕለቱ እንግዶቻቸውን ይጠብቃሉ። ሁለት ሰው በቻ ሲግባባቸው አፍ እስካፍ ጢም የሚሉት የመቀሌ ግሮሰሪዎች በተለምዶ 22 ከሚባለው ቦታ ካሉት ግሮሰሪዎች ጋር ይመሳሰላሉ። የሚለየዩት የመቀሌዎቹ መጋረጃ ሲኖራቸው የአዲሳቦቹ ያለመጋረጃ ሆነው በራቸው ገርበብ በማድረግ ብቻ ይለያያሉ።

የመቀሌ ከተማ መጋረጃ ምስጢር በመቀሌ ከተማ ቀደም ብሎ እንዳሁኑ የኮብልስቶን ሳይሰራ አፈር ስለነበር ንፋስ ሲነፍስ በግሮሰሪ የሚጠቀሙ ሰዎች መጠጥና ምግብ ውስጥ አፈር እየጨመረ ስላስቸገራቸው ያንን ለመከላከል መጋረጃ ይጠቀሙ ነበር። አሁን ንፋሱ እንጂ አፈሩ ባይኖርም ድሮ አፈሩን በዚህ መልኩ በመጋረጃ ሲክላከሉት ስለነበር ዘሬ አፈሩ ባይኖርም የመገረጃን ውልታ ባለመርሳት ለመመለስ የሚያደርጉ ይመስላል። ምክንያቱም መጋረጃ ያኔ መቀሌ አቧራ በነበረች ጊዜ እንግዶቻቸውን ከአቧራና ከነፋስ ታድጎአልና ነው። የመቀሌ ባለመጋረጃ ግሮሰሪዎች እንግዳ በጣም ያከብራሉ። ያንን በመሰለ ፈገግታ ጠብ እርግፍ ብለው ሲያገለግሉ ፍቅር ለሆነው መስተንግዶአቸው ሲባል ገንዘብ በኖረና ምግብና መጠጡን ብቻ ሳይሆን ቤቱን ሁሉ በገዙዋቸው እንዴት ደስ ባለዎት ይሉ ነበር።

መቀሌ ከሄዱ ሳይዉሉ ሳያድሩ ነው የሚለምዱት እንግዳ መሆን ብሎ ነገር የለም። በተለይ ባለትዳር ካልሆኑ በዚያው ስላለመቅረትዎ ምንም ዋስትና የለዎትም። ይገርማል ከኔ ጋር የሄዱ ከኔ ድርጅት ስራተኞች ለስራ የሄዱት የተመለሱት ባለትዳሮቹ ብቻ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ፔርሙዳው የመቀሌ ፍቅር በዚያው ነው ያስቀራቸው። እኔም ብዙ ሆኜ ወጥቼ ጥቂት ሆኜ የተመለስኩበትን የመቀሌውን ጉዞዬን አልርሳውም። በእርግጥ ማታ ማታ በነፋሻው የመቀሌ አየር እንደ ቅባት በሚያብረቀርቀው ኮብል ስቶን ላይ በግሮሰሪዎቹ በረንዳ ተቀምጦ መዝናናት እንደሱስ ይሆናል። በዚህ ላይ ከሥራ መልስ ሁሉም ሰው በዚህ መልኩ ስለሚዝናና ለብቻው የተቀመጠ ሰው ቢኖር የመቀሌ ሰዎች ጠርተው አብሮ ተቀላቅሎ እንዲዝናና ማድረግ የተለመደ ባህላቸው ነው። ብቻየን ነኝ ብለው አያስቡም ከሚመጡት ግሩፕ እንዱ እንዲቀላቀሉ ያደርግዎታል። እርስዎም በአዲሱ ግሩፕ ውስጥ አባል ሆነው ይቀጥላሉ። የመቀሌ ከተማ ንጽህና ግርም ይላል። በመሬት ላይ ምንም የፌስታልም ይሁን የወረቅት ቁራጭ አያዩም መንገዱ ንጹህ ነው። 

በአዲስ አበባችን በተለምዶ 22 በሚባለው ቦታ ያሉ ጠበብ ጠበብ ያሉ ግሮሰሪዎች በራቸውን መለስ መለስ አድርገው እንግዶቻቸውን ይጠብቃሉ መቀሌ በመጋረጃ በሩ የሚከለል ሲሆን እነዚህ ደግሞ በራቸውን ገርበብ አድርገው ይከልሉታል። በግሮሰሪዎቹ ውስጥ ሶስት ሰው ቢግባባቸው አፍ እስካፋቸው ጢም ነው የሚሉት ነገር ግን የነዚህም መስተንግዶ ግሩም ስለሆነ አስፓልቱ አጠገብም ቢሆን ወንበሩን ይዞ ተቀምጦ ይስተናገዳል እንጂ ሰው ቤቱ ሞልቶብኛልና ሌላ ቦታ ሄጄ ልብላ ልጠጣ አይልም። ልዩነቱ በመቀሌ ትግርኛ ዘፈን ለማድመጥ አስተናጋጅዋን ጠርተው ሊጠይቁ ይችሉ ይሆናል። በዚህ በአዲስ አበባ የማይሰሙ የአማርኛ፣ የኦሮምኛ፣የጉራጌኛ፣ የደቡብና ሌሎች የብሔር ብሔረሰቦችን ዘፈን ማድመጥ የሚችሉት በመቀሌ ነው ቢባል ውሸት አይሆንም። ለነገሩ ብሔር ብሔረሰቦች ሆቴል የሚል ስያሜ ያለው ቤትም በመቀሌ አለ። 

ከሲሚንቶ ይልቅ ውሃ የተወደደባት መቀሌ ከፊት ለፊቷ የውሃ ችግር አንዣቦ ይታያል፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የመቀሌ ህዝብ ዉሃ ተጠምቶ በሌላ አካባቢ ያሉ ወገኖቹ በመኪና ውሃ ጭነውለት መሄዳቸው አይቀርም። የኢህአዴግ መንግስት መቼም ሥራዎችን የሚሰራው ከጥናት በፊት ነው። ሥራውን ጀምሮት የተጀመረው ሥራ ፌል ሲያደርግ (fell) አልሳካ ሲል ወደ ጥናቱ ይሄዳል። ዓይናለም በሚባለው ቦታ የመቀሌን ህዝብ ከሀያ ዓመት በላይ በውሃ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ቢታሰብና ቢሰራም የተባለው ውሃ ብዙ ወጪ ወጥቦት ሲያበቃ በሦስት ዓመቱ ነው ያለቀው። አሁንም ለመቀሌ ህዝብ የታሰበው ውሃ ግልጽ አይደለም፡፡ ችግሩ ከደረሰ በኋላ መሮጥ የተለመደ ነው።

ኢህአዴግ አሁን አሁን እየሰራ ያለው የልጅ ጫወታ ነው ማለት ይቻላል። ልጆች ሲጫወቱ አፈር ይከምራሉ መልሰው ይንዱታል። እንደገና ይከምሩታል፡፡ ለምን እንደሚከምሩና ለምን እንደሚንዱት አያውቁትም። ኢህአዴግ ዛሬ በከተመይቱ በአዲስ አበባ በርካታ ነገሮችን ሲስራ ይታያል። ተሰርተው የታዩት ነገሮች መልስዉ ሲፈርሱ ደግሞ ይስተዋላል። ይህ ዓይነቱ ሀላፊነት የጎደለው ሥራ ደግሞ መቆሚያው የት እንደሆነ መገመት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ አሁን እየተሰሩ ያሉትን ገንብቶ የማፍረስ ሥራ ማን እየስራው እንደሆንና ለዚህ ተግባር ተጠያቂው ማን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም።

የአንድ ከተማ ማስተርፕላን የሚከለስው በየ አስር ዓመቱ ነው። ማስተር ፕላን ሲከለስ ሊኖሩ የሚችሉ የዕድገት ግንባታዎች ሁሉ በማስተር ፕላኑ ይካተታሉ። በዚህ ማስተር ፕላን ክለሳም ቢሆን የመስፋፋት እንጂ የማፍረስ ሥራ አይሰራም። ምክንያቱም መንገዶች በማስተር ፕላኑ ሲቀመጡ የረጂም ጊዜ የከተማዋን ህዝብ ቁጥርና የመኪናዎችን ፍሰት ከግንዛቤ አስቀምጦ ነው። በእርግጥ አንዳንድ ግለሰቦች ሀላፊነት ከጎደላቸው የከተማው መሀንዲሶች ጋር በመሆን ማስተር ፕላኑ መንገድ እያሳየ ባላየሽ መንገዱ ላይ እንዲገነቡ ያደርጋሉ። የዚህ ዓይነቱ ግንባታ በማስተር ፕላኑ መሠረት ከተማው ሲስፋፋ እነዚያ በማስተር ፕላኑ መንገድ ላይ የተሰሩ ቤቶች አንዲፈርሱ ይደረጋል።

ይህ ቤት ሲፈርስ በርካታ የሀገር ኢኮኖሚ አፈር ይበላል። የመጀመሪያው ይህንን ቤት እንዲፈርስ ለማድረግ የሚባክነው ጊዜ ነው። ማስተር ፕላኑ መንገድ እያሳየ ከመሀንዲሱ ጋር በመመሳጠር የተሰራ ቤት ባለቤቱ አይኔን ግንባር ያድርገው ይህንን ነገር አላውቅም ይላል። ካሳ ይከፈለኝ በማለት ለህገወጥ ግንባታ መፍረስ ድርድር የሚባክነው ጊዜ የመጀምሪያው ኪሳራ ሲሆን ይህንን ማፍረሻ ከመንግሥት ካዝና የሚወጣው ገንዘብ ሁለተኛው ኪሣራ ነው።

ሌላው ይህንን ግንባታ እንዲገነባ የወጣው ወጪ በእሳት ላይ እንደተጣደ ቅቤ ሆነ ማለት ነው። ገንዘብ ለዚህች ደካማ ሀገራችን አንድ ሽንቁር ይደፍን ነበር። በከተማችን በአዲስ አበባ የሚሰሩ ሥራዎች ሁሉ ተቆጣጣሪ አላቸው ብሎ መገመት አስቸጋሪ ነው። ባለሀብቱም የሚሠራው ግንባታ የመኪና መንገዱን ጠርዝ ካልያዘ ለሠራው ሥራ ገበያ የሚያግኝ ወይም የተግነባው ግንባታ ውበት የሚኖረው አይመስለውም። መንግሥትም አስፓልት ዳር ወጥተው የሚገነቡ ግንባታዎች ሲጀመሩ አስቆሞ ወደሁዋላ እንዲያሸገሽጉ ከማድረግ ይልቅ ከተገነቡ በሁዋላ ማፍረስን እንደሙያ ይዞታል።

በከተማችን በአዲስ አበባ የሚገነቡ ህንጻዎች ሁሉ ፓርኪንግ እንዲኖራቸው አይደረግም። ፓርኪንግ እንዲሰሩ ቁጥጥር ተደርጎባቸው የተሰሩትም ቢሆኑ የጭፈራ ቤትና ከፋፍለው ሱቅ ሲያደርጉት ማንም ተከታትሎ እርምጃ አይወስድባቸውም። በዚህም በበርካታ ቦታዎች ያሉ ሆቴሎችና ግንባታዎች የራሳቸውን ፓርኪንግ ጭፈራ ቤት አድርገው መንገዱን ፓርኪንግ ስለሚጠቀሙበት መንገዱ ተጨናንቆ የትራፊክ ፖሊስ ፈተናና ተጨማሪ ሥራ ሆነዋል። እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተከስተው መንገዶች ተዘግተው ነዋሪው ሲቸገር ዝም ይባላል። ደግሞ የእዲስ አበባ አስተዳደር ለከተማው ዕድገት ወገቤ ተቀነጠሰ ይለናል፡፡ እኛ ደግሞ ካታማው ሲያድግ ሳየሆን ተገነብቶ ሲፈርስ ነው የምናየው፡፡ 

የቀደሞ መንግሥታት ከዕውቀት ማነስም ይሁን ከሌላ ልዩ ልዩ ነገሮች መንገዶችንም ይሁን አጥብቦ ማስተር ፕላኖችን አጥብቦ ሊስራ ይችላል፡፡ አሁን 21ኛው /ዘመን ያለ መነግሥት ግን ይህንን አስተካክሎ መሥራት ግዴታ አለበት፡፡ ይህንን መሥራት ካቃተው የአቅም ማነስ ችግር ወይም የሀላፊነት ማጣት ችግር አለ ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ችግሩ የአቅም ማነስ ከሆነ አቅም ላለው ማስተላልፍ ይገባል። ኢህአዴግ በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ ገነባኋቸው ያላቸው ትላልቅ ግንባታዎች በብድር የተሰሩት ብድሩ ሳይከፈል ለኮንትራክተር ተሰጥተው የተሰሩት ገና ርክክብ ሳይፈጸም መልሰው እየፈረሱ ይገኛሉ። እነዚህ አላግባብ ተሰርተው እየፈረሱ ላሉት ግንባታዎች ተጠያቂው ማን ነው ለሚለው መልሱን እንኳን ይህ ፀሐፊ ለራሱ ኢህአዴግም አይመልሰውም፡፡ በብድር የተሰሩትም ቢሆን ኢህአዴግ ዝንተ ዓለም ኑሬ እከፍላቸዋልሁ ብሎ ሳይሆን ቀጣዩ ትውልድ ይከፍላል በሚል እሳቤ ነው፡፡ በብድር የሚሰሩት ታዲያ ጠያቂውስ ለምን ግንባታ አበድሬያችሁ ነበር ይላል። ቀጠዩ ትውልድስ ምን የተሠራበት ነው ብሎ ይከፍለል?

ኢህአዴግ የሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ ማለት ይቻላል፡፡ አጥንቶ ሰርቶአል ማለት አይቻልም። ተሰርተው ከሚፈርሱት መንገዶች በተጨማሪ የተሰሩት መንገዶች ሁሉ ማለት በሚቻልበት ሁንታ በተመረቁ ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ ይታይበቸዋል። ይህ የሚያሳየው ገዥው ፓርቲ ነገሮችን አርቆ አስቦ ለሚመጣው ትውልድ የመስራት ችግር እንዳለበት ነው። ለምሳሌ አፍሪካ ጎዳና የሚባለውን በቅርቡ ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ኤርፖርት ያለውን መንገድ መመልከት ይቻላል። በዚህ መንገድ በግራና በቀኝ ያሉት ህንጻዎች (comertial area) የንግድ አካባቢዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ቀደም ብለው የተሰሩ ሲሆኑ ፓርኪንግ የላቸውም። ሌሎቹ ከስር የተሠራውን የፓርኪንጉን ቦታ ሱፐር ማርኬት አድርገውታል። በዚህ አካባቢ መኪና ማቆም ደግሞ ምልክቶቹ ይከለክላሉ። ይህ በማስተር ፕላኑ የንግድ ቦታ የሚለው ወደ መኖሪያ ቦታነት ደግሞ ተቀይሮ ሰዎቹ ሌላ ቦታ ሄደው መነገድ አልቻሉም፡፡ ግብር ደግሞ ይጠየቃሉ፡፡ ቤተሰቦቻቸውንም የመመገብ ልጆቻቸውን የማስተማር ግዴታም አለባቸው። ይህ አሁን የተሰራው አፍሪካ ጎዳና ደግሞ መተላለፊያ ብቻ ሆኖአል። በዚህ አካበቢ መቆም እንዳይችል ከምልክቱ በተጨማሪ ታርጋ የሚፈቱበት የብሎን መፍቻ ይዘው የሚንጎራደዱ የትራፊክ ፖሊሶች አሉ።

በጥናት ማነስ ችግር ብቻ በርከታ ወጪና ኪሳራ እያስከተለ ያለ መንገድ ሆኖአል። መጀመሪያ በአካባቢው ፓርኪንግ እና የመኪና ማቆሚያ አለመኖሩ ሲታወቅ መሆን ያለበት የመጀመሪያው መንገዱን አንድ መም (len) ጨምሮ በመስራት አንዱዋን መም ለመኪና ማቆሚያ ማድረግ ሲሆን ሌላው በአካባቢው ያሉ በዶ ቦታዎችን እንደ አሜሪካና አውሮፓ ለመኪና ማቆሚያ ማዘጋጀት ነው፡፡ ሌላው ከምድር በታች ቤቶች ሰርተው ለሱቅም ይሁን ለሌላ ነገር ያዋሉትን አስለቅቆ መኪኖች እንዲቆሙበት ማድረግ ይገባ ነበር። በሌላ መልኩ ለዚህ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት የሚውሉ ፎቆችን የሚሰሩ ባለሀብቶችን ማበረታታት ችግሩን ይቀርፈዋል። አሁን የተያዘውን ያንን የተዋበ ከተማ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ መተላለፊያ መንገድ ብቻ ማድረግ ሀላፊነት የጎደለው ሥራ ነው ባይ ነኝ።

በተሰሩ በጥቂት ወራትና ዓመታት እየፈረሱ ያሉ መንገዶች ኪሣራ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ሀገርን ይህ ነው ለማይባል ኪሣራ እየዳረጋት ሲሆን አሁን በከፍተኛ ወጪ አየተሰራ ያለው የባቡር መንገድስ ላለመፍረሱ ምን ዋስትና አለ? ባለፉት ጥቂት ዓመታት መኪናየን እየነዳሁ ሰሄድ አንድ ነገር አየሁ፡፡ አንድ ኤክስካቬተር ኩነቢውን እንዳ ጥንብ አነሳ ወደሰማይ አድርጎ የደሴ ሆቴልን ሲንደው አየሁ፡፡ ለምንድን ነው ብየ ጠየቅሁ መተላለፊያ መንገድ ሊሰራ ነው ተባለኩ በእርግጥ መንገዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ አገለግሎት መስጠት ጀመረ ጥሩ ነው፡፡ ጥቂት ጊዜ ሳይቆይ ደግሞ ያንኑ የሚመስል ኤክስ ካቬተር ኩነቢውን ወደመድር አድርጎ አዲሱን አስፓልት ሲንዳው አየሁ ምነው ብየ ብጠይቅ ለባቡር መንገድ ተበሎ እየፈረሰ ነው ተባለኩ አሳዛኝ ድርጊት ቀጥሎ የተሰራው የባቡር መንገድ ምን ያህል ጊዜ ይቆይ ይሆን ይህ ሁሉ የዲዛን ችግር ሲሆን የተሰራውን ዲዛይን የተረከበው ባላሙያ ችግርም ነው፡፡እነዚህን ነገሮች ሳይነካ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ ለነገሩ ይህ መሆን ይችል የነበረው ለሀገር ማሰብ ሲቻል ብቻ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment