Friday, August 9, 2013

በማሸበር የሚኖሩ በመግደል የሚከብሩ የሰው አረሞች

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

አረም ማለት ያልተዘራበት የሚበቅል ገበሬ የዘራውን ሰብል የሚሻማ፣ ውሀውን የሚጠጣበት፣ ለበሽታና ተባይ መጠለያ በመሆን ለሰብል ጉዳት ምክንያት የሚሆን እጽዋት ማለት ነው። አረም በስሮቹ አማካይነት የሰብሉን ስር አንቆ የሚገድል፣ አንዳንዱም እንደ ፓራሳይት ሰብል ላይ ተጣብቆ የሚበቅል እንደ አቀንጭራ ያለ ማለት ነው። አረሞች በፈጣን አስተዳደጋቸው ሳቢያ አልሚ ንጥረ ነገሮችን ከመሬት የፀሀይ ብርሃን ከሰማይ በመሻማት የሚያቀጭጩና የሚገድሉ ናቸው። የስንዴ ማሳ ውስጥ የበቀለ በቆሎም እንኳ ቢሆን አረም ነው፣ ገብስም ቢሆን አረም ነውና ተነቅሎ ይጣላል። 

አረም ዘሩን በማባዛትና የመኖር እድሉን ለማራዘም በርካታ ዘዴዎችን እየተጠቀመ በብዛት የሚንሰራፋና በወቅቱ ካልታረመ ሰብል የሚያጠፋ ነው። ጎበዝ ገበሬ አርሞና ኮትኩቶ ሰብሉን ካልተንከባከበ በሰብል ምርት ምትክ አረሙን ማፈስ ይገደዳል። ልክ እንደ ምሳሌው ኢትዮጵያዊነትን የሰው አረም ውጦታል።
ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አቋምን የያዘ በሌሎች ስም ይልቁንም በትግሬ ስም ኢትዮጵያዊነት ላይ ተጣብቆ አገር እያፈረሰ ያለ የዘራፊ ቡድን አገርና ሕዝብ እያቀጨጨ ነው። ወያኔ በቆሎና ማሽላ ላይ ተጣብቆ እንደሚበቅል አቀንጭራ (ፓራሳይት፣ ጥገኛ አረም) ኢትዮጵያዊነትን ተጣብቶ ኢትዮጵያን እየገደለ ያለ ቡድን ነውና ተነቅሎ መጥፋት አለበት። በምስሉ የተቀረጹኦፖርቹኒስትገንጣዮችና ከፋፋይ ድርጅቶችም እንዲሁ።

ስንዴ ማሳ ላይ የበቀለ ገብስ አረም የመሆኑን ያህል ኢትዮጵያዊነትን አቀጭጮ የሚገድል ኢትዮጵያዊም ቢሆን የሰው አረም ነውና ተነቅሎ ሊጣል ወይም ለፍርድ ሊቀርብ ይገባዋል። ምንጫቸው ትግራይ ስለሆነና የትግራይ ተገንጣይ ግንባር ነኝ ስላሉም የትግራይ ሕዝብ ውክልና የላቸውም። በመጀመርያ እኒህ የሰው አረሞች ጭካኔና ግድያን የተለማመዱት ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ያደረጉ የትግራይ ተወላጆችን በማደን መሆኑን እናውቃለን። የታታሪ ገበሬን ምሳሌነት የመጠቀሚያ ጊዜው እየረፈደ ቢሆንም አረም ለማጥፋት በደቦ መጠራራት የመጨረሻው የመኖር ያለመኖር ተስፋችን ነው። እያዩ ማለቅንም እለት በእለት እየተለማመድነው ከብት ወደ መታረጃው እንደሚነዳው አቅመ ቢስነት ውስጥ ከገባን ያበቃልናል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አምርረው በሚጠሉ ሰዎች ጥፋት ምክንያት ኢትዮጵያን ልንጠላ ግን አይገባም። ሰሞኑን ሰላማዊ ሕዝብ ላይ በሚደርሰው ጭፍጨፋ ኢትዮጵያዊነታቸውን እስኪጠሉ ድረስ የሚማረሩት ወገኖች ምሬታቸው ከፍቶ ሰው መሆናቸውን እስኪጠሉና የሚፈራውና ለብዙዎች ጥፋት ምክንያት የሚሆነው የአጥፎ መጥፋት እልቂት እስኪመጣ መጠበቅ ሞኝነት ነው። 

በሀገራችን ገበሬው የአረም ማጥፊያ መርዝ የሚጠቀመው ጥቂቱ ነው። የገንዘብ አቅም ስለሚያንሰው መርዛማነቱም ለሌላው ስለሚተርፍ። ልክ እንደዚያው ወያኔን ለማጥፋት የድርጅት አቅም አንሶናል ወደ መሳርያ ማንሳቱ ሁሉም እየተገፋ ከመጣ ለብዙ ህይወት መጥፋትም ምክንያት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ገበሬዎች አረምን ለማጥፋት አንድ ግሩም ባህል አላቸው። ያም ደቦ፣ ጅጊ ወዘተ የሚባልና ተጠራርቶና ተሰባስቦ በህብረት ማሳቸውን ከአረም ማጽዳት የሚችሉበት መንገድ። ተመሳሳይ ብልህነት ከጠፋንና እያማረርን ዘመን ከቆጠርን ተራ በተራ አንዴ የተበደሉ ጎሳዎች አንድ ሰሞን፣ የተፈናቀሉ ወገኖች በሌላ ሰሞን፣ ክርስቲያኖች አምና እስልምና ተከታዮች ዘንድሮ፣ ሴቶች ትናንት፣ ወጣቶች ዛሬ ልላ እያልን በወረፋ መታረድን ልንለማመደው የግድ ይሆናል። አንዱ በሌላው ሞት ዝም በመሰኘት አጥፊዎቻችንን ጉልበት እየሰጠ፣ እነርሱም እየናቁንና እያፌዙብን በመጨረሻም አገር እንዲያሳጡን መፍቀድ የለብንም። ሕዝቡና የፖለቲካ ድርጅቶች ተበታትነው እየሮጡ ሲያልቁ የሰው አረሞች እየተሰፋፉና እየተመቻቸው መኖር የሚችሉበትን ሁኔታ እያመቻቹ የመቀጠል መዘናጋት ሊያበቃ ይገባል።

ዛሬ ያስቸገረንና የከበደን ሀገር በቀል አረም ነው ነገ ግን ጉልበተኛና ጨካኝ አንዴ እግሩን ከተከለ ማጥፊያ መንገድ የሌለው መጤ አረም ይውጠናል። በዚህ ከቀጠልን የዛሬዎቹ አረሞች ነገ ስማቸውን ለኛ ሰጥተውን እኛ እንደ አረም በመርዝ እናልቃለን። በዚህ ከቀጠልን ካሁኑ በከፋ ሁኔታ እንሰደዳለን እንሳደደለንም። ተቆጥቶ ለመነሳት በጣም አርፍደናል ባለቀ ሰዐትም እንኳ ቢሆን ለመነሳቱ ዛሬ ከነገ ይሻላል። ወያኔዎች በማሸበር የሚኖሩ በመግደል የሚከብሩና ሀገሪቱ የጦርነት ቀጠና ሆና እነሱ ወታደራዊ ስርዐትን አስፍነው ያሻቸውን እየገደሉ ለመኖር እየጣሩ ነው። አምባገነኖች ሁሌም በጦርነትና በቀውስ ሁኔታ ውስጥ መኖርን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ሰላም ሲሆን እነርሱ መመለስ የማይችሉአቸው የመብት ጥያቄዎች ስለሚነሱ በስልጣን መቆየት አያስችላቸውም። 

በፖለቲካ ድርጅትም ይሁን በጎበዝ አለቃ ሕዝቡ መንደሩን ሊያጸዳ ገዳዮቹን ለፍርድ ሊያቀርብ የሚችል ሀይል እንደሆነ ጠላቶቹ ሊያውቁት ይገባል። ተደጋግሞ እንደተገለጸው ወያኔ እርጉም ጠላት እንጂ መጥፎ መንግስት አይደለም። የሕዝብ ክብርና የሰዎች ነጻነትም አይገባውምና ተነቃቅሎ ሊጣል የሚገባው አረም ሊወገድ የሚገባው የሀገር ጠላት ነው። 

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከነፃነት ሰንደቅዓላማችን ጋር ለዘለዓለም ይኑርልን!

No comments:

Post a Comment