Wednesday, August 7, 2013

***የመንግስት ስልጣን ከጠመንጃ አፈሙዝ ይመነጫል ***

የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኑሮ ውድነት እና የፍትህ እጦት፣የሀይማኖት ነፃነትን ለመቃወም የማንም ፓለቲካ ድርጅት መሆን አያሻም !!! ይህን ከተቀበልን

ለምን ህውሃት/ወያኔ እና ሰብዓዊ መብት እሳት እና ጭድ ሆኑ? 
የመግደል አቅም የሌላቸውን እንደ ድምጽ ማጉያ አይነት ቁሳቁሶችን ህውሃት ለምን ሊፈራ ቻለ? 
ለሚለው ጥያቄ እንወያይና መልስ እንስጥ።

የመንግስት ስልጣን ከምርጫ ሳጥን ይመነጫል የሚለው የፖለቲካ ትግል ባህል በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚፈጸም ነው። ህውሃት/ወያኔ ይኼን የፖለቲካ ባህል ከወሬ ባሻገር አያውቀውም። ባህሉም የለውም። በነፃ ምርጫ እመረጣለሁ ብሎም አያምንም። የመንግስት ስልጣን ከጠመንጃ አፈሙዝ ይመነጫል የሚለው እርስ በርስ መጨራረስን በይፋ የሚሰብከው ፍልስፍና ነው የህውሃት/ወያኔ የፖለቲካ እምነት። ህውሃት ተወልዶ ያደገው ይህን የፖለቲካ እምነት በመከተል እና በመፈጸም ነው። ይኽ የፖለቲካ ፍልስፍና ደግሞ ለስልጣን እንጂ ለሰብዓዊ መብት ዋጋ እንደማይሰጥ ግልጽ ነው። ትጥቅ ትግል እና ሰብዓዊ መብት የተባሉት ሁለት ነገሮች እሳት እና ጭድ ናቸው።
ባጭሩ ትጥቅ ትግል እየሰብክ እና እያራመድክ ሰብዓዊ መብት አክባሪ ነኝ አትበሉ ለሚሉት ትንሽ መልስ እንስጥና እንለፍ የተጨቆን፣ነፃነት ያጣን ህዝብ፣በመልካም አስተዳደር እጦት የተንገላታን ህዝብ፣በፖለቲካምና በማህበራዊ ኑር መኖር ያልቻለ ህዝብ፣ስደት ብቸኛ አማራጭ አድርጎ በሚኖርበት ሁናቴ የትጥቅ ትግል አያስፈልግም ማለት ምን ማለት ነው።
ህውሃት/ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ምንም አይነት ነገር እንደማያስረክብ ታልሞ የተፈታ ነው።
ህዝባችን ነፃነቱን ሲጠይቅ ድብደባ፣እስርና ጠመንጃ አፈሙዝ ይመነጫል ታድያ በዚህ አይነት ሁናቴ ሰላማዊ መንገድ ብቻ አማራጭ ሊሆን እንደማይችል የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ህውሃት/ወያኔ ሳያቋርጥ ለአስራ ሰባት አመቶች በእርስ በርስ ጦርነት ህዝብ አጫርሶ፣ መንደሮች አፍርሶ እና ህዝብን ለስደት ዳርጎ ለስልጣን የበቃ ድርጅት ነው። እንደሚታወቀው ህውሃት .አል.ኤፎችን በተኙበት አርዶ፣ .ዲዩ.ዎችን፣ ኢህአፖችን እና የደርግን ወታደሮች ፈጅቶ ነው እዚህ የደረሰው። በትግራይም ህውሃትን ከተቀላቀሉ ወጣቶች ውስጥ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ የፈለጉን በአረመኔነት ገድሎ፣ በውስጡም ቢሆን ከአምባገነኖቹ መሪዎቹ የተለየ አሳብ የነበሩዋቸውን አባላቱን እየፈጀ፣ ገበሬውን ስደተኛ እያደረገ፣ የውጭ እርዳታ ለማግኘት ድርቅ እልቂት በአረመኒነት እንዲባባስ እያደረገ ነው ለስልጣን የበቃው። ይህ ሁሉ ተግባሩ ህውሃትን የሰብዓዊ መብት አፍራሽነት የሻምዮንነት ማዕረግ ያስገኝለታል። ህውሃት እና ሰብዓዊ መብት እሳት እና ጭድ ናቸው።

ህውሃት/ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣም ወዲህ
አገር አፈረሰ።
1
የባህር በር አሳጣን።
2
የአልቢኒያ እና የሶቪየት ህብረት አምባገነኖች የጻፉትን ቃል በቃል ቀድቶ ኢትዮጵያን ሊያስተዳድር ሞከረ። 
3
አልሰራ ሲለው በሽብር በማስተዳደር ላይ ይገኛል። የአገሩን ህዝብ ታሪክ ጠንቅቆ አውቆ፣ ቀደም
4
ብለው የተፈጸሙ ስህተቶችን አስተካክሎ እና እንዳይደገሙ አድርጎ ህዝቡን አቀራርቦ አገር በመምራት ላይ የሚገኝ ቡድን አይደለም።

ህውሃት/ወያኔ የፈጸማቸውን እንቅፋቶች እና ወደፊት ሰላማዊ ትግል ለማራማድ የሚያደርጉትም ቢሆንም ጥረቶች ከህውሃት በኩል የሚገጥሙን ፈተናዎች ምንጫቸው ይህ የህውሃት ከሰብዓዊ መብት ማክበር ባህል ጋር እሳት እና ጭድ መሆኑ እንደሆነ መዘንጋት የለበንም። በህገ-መንግስቱ ውስጥ የተዘረዘሩት ሰብዓዊ መብቶችም ቢሆኑ የምዕራቡን አለም ለማጭበርበር እና የገንዘብ እርዳታ ለማግኛ እንጂ አምባገነኑ መለስም ሆነ ዛሬ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው የመኪና ጎማ አስተንፋሽ ወሮበላ ህውሃት/ወያኔ ፍጽም አያምንባቸውም። 
ህውሃት የፖለቲካ ባህሉ መግደል ነው። 
ስብዕናው የተሟጠጠ ነው። 
ታሪኩ ደም ነው። 
ስለዚህ ህውሃት በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ስርዓት መገንባት የሚያስችለው ባህል ፍጹም የለውም። 
በዚህ ሁሉ ምክንያት ሰብዓዊ መብት የሚቀሰቅስን የድምጽ ማጉያ ህውሃት ቢፈራ ሊገርመን አይገባም።

የፖለቲካ ትግል ባህል ሽግግሩ ሳያቋርጥ እንዲዳብር እና በህዝባችን ዘንድ እንዲሰርጽ እንዴት እንርዳ? ህውሃት/ወያኔ አምባገነን ነው። አምባገነን ይፈራል። ህውሃት/ወያኔ በህዝብ ይሁንታ ስልጣን ላይ አልወጣም። ህጋዊነት እንደሌላቸው ህውሃቶች ብቦናቸው ያውቁታል። ስለዚህ ከጠበንጃ ይልቅ ህዝባዊ ነፃ መሰባሰብን፣ ህዝባዊ ነፃ ውይይትን እና ህዝባዊ ተሳትፎን ይፈራሉ። ህዝቡ በነፃነት የሚያደርጋቸው ነገሮች አምባገነኖችን ያስደነግጧቸዋል። ያስበረግጓቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላማዊ ትግል ወታደሮች ነን የምንል ሁሉ እነዚህን የአምባገነኖች ሁሉ መለያ መሰረታዊ ጸባዮች ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል። የፖለቲካ ትግል ባህል ሽግግር ቀላል እንደማይሆንም በቅድሚያ ልንገነዘብ እና ልንዘጋጅ ይገባል። የሰላም ትግል ሰራዊት ትግባሮች ድርብርብ ናቸው። 

የፖለቲካ ትግላችንን ባህል ሽግግር ለማፋጠን ህውሃትን የተጀመረው የፖለቲካ ባህል ሽግግር አካል ማድረግ ለሁላችንም ይጠቅማል። ይኽን ለማድረግ ሰለአምባገነኖች ፀባይ ከፍ ብለን የዘረዘርናቸውን ማወቅ እና ተገቢውን ስራ መስራት ይጠቅማል። የሰላማዊ ትግላችን ግብ ህውሃትን ለመበቀል አይደለም። በፍጹም። የሰላም ትግል ወታደር ግቦች ህዝባችንን ወደ ነፃነት፣ ዲሞክራሲ እና ልማት ማሸጋገር ነው። ይኽን ከስኬት ለማድረስ እራስን በዘመናዊ ሰላማዊ ትግል ንድፈ አሳብ እና አፈጻጸም መቃኘት ያስፈልጋል። እንደትናንቱ በሰላማዊ ትግል መዝገበ-ቃላት ትርጉሙ ብቻ መወሰን በቂ አይደለም። የሰላማዊና የትጥቅ ትግል ክህሎታችንን ማዳበር አለብን።

የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኑሮ ውድነት እና የፍትህ እጦት፣የሀይማኖት ነፃነትን ለመቃወም የማንም ፓለቲካ ድርጅት መሆን አያሻም !!!
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment