‘‘ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝበ ሙስሊም ጥያቄ በኃይል፣ በጠመንጃ መፍታትን ያቁም’’
ኢህአዴግ የሕዝበ ሙስሊም ጥያቄን በኃይል፣ በጠመንጃ ለመፍታት መሞከር ችግሩን አባባሰው እንጂ ሊፈታው ስላልቻለ ኢህአዴግ ያሰራቸውን ሕዝበ ሙስሊም በአስቸኳይ ፈቶ የኢትዮጵያ ሕዝበ ሙስሊም ጥያቄ በዲሞክራሲያዊ ውይይት እንዲፈታ ጥሪአችንን እናቀርባለን።
በአዲስ አበባ ከተማ በአወሊያ ት/ቤት የተቀሰቀሰው ጥያቄ ዛሬ ተስፋፍቶ በአገሪቷ ላይ ሊፈታ ወደማይችልበት እድገት ሊደርስ የቻለው የገዥው ፓርቲ ‘‘ኢህአዴግ’’ የኃይል የጠመንጃ አፈሙዝ እርምጃ በመሆኑ በአስቸኳይ በቶሎ እርምት ተወስዶ ወደ ዲሞክራሲያዊ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪአችንን እናቀርባለን።
ኢህአዴግ በሺ የሚቆጠር ሕዝብ ኢድአልፈጥር የበዓል አከባበር ተንተርሶ ያሰራቸውን ሁሉ እንዲፈታም ጥሪአችንን እናቀርባለን። ዛሬ ‘‘የኢህአዴግን’’ የኃይል እርምጃ ምክንያት በማድረግ ብዙ ሕዝብ አገሩን ለቆ ወደ ሌላ አገር በመኮብለል ላይ ስለሚገኝ ገዢው ፓርቲ ስህተቱን በአስቸኳይ በማረም ወደ ዲሞክራሲያዊ ውይይት እንዲመለስ እንጠይቃለን።
ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄም ሆነ የጐረቤት አገር ጥያቄን በዲሞክራሲያዊ ውይይት የማይፈታ ከሆነና ወደ ኃይል እርምጃ የሚዞር ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እየተሰሩ ያሉት ትላልቅ የልማት ስራዎች ስለሚደናቀፉ ‘‘ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መንገድን ይዞ አገሪቷን እንዲመራ ጥሪአችንን እናቀርባለን።’
ሰንደቅ ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment