አንድነት በመብራት ሃይል አዳራሽ በአጭር ጊዜ የጠራው ስብሰባ በድምቀት እና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ በመብራት ሐይል በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ የፓርቲው አመራር አባሎች እና ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ የሚሆን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን፤ በተለይ ዛሬ ለስብሰባው ቅስቀሳ ሲያደርጉ በህገወጥ መንገድ የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አባላት ተለቀው ወደስብሰባ አዳራሹ በማመራት ስበሰባውን መሳተፍ ችለዋል፡፡ ከነሱ መሀል ዛሩ ሳሪስ በፖሊስ ኮማንደሩ ፊት በደህንነቶች ቡጢ የቀመሰው ያሬድ አማረ እንድሚገኝበት ላምወቅ ተችሏል፡፡ ስብሰባውም ለዲያስፖራው ሕበርተሰብ በቀጥታ በቃሌ እና በሲቪሊቲ የፓልቶክ ክፍሎች ሲተላለፍ እንድነበረም ለማወቅ ተችሏል።
ስበስባው ከመጀምሩ በፊት መፈክሮች ከተሰሙ በኋላ የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ሰብሳቢ አቶ ትግስቱ አወሉ ስብሰባውን በንግግር ከፍተዋል፡፡ በመቀጠልም የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን ንግግር ያደርጉ ሲሆን በንግግራቸው “
የሃገሬ ወጣቶች፣ በነጻነት የምትኖሩበት አገር ትፈልጋላችሁ? እንግዲያውስ ኑ ሕዝባዊና ሠላማዊ ተቃውሞውን ተቀላቀሉ፤ ምሩ።”
የሚል ስሜት ነኪ ንግግር በማድረግ ተሳታፊዎቹ ከአንድነት ፓርቲ ጎን እንዲሳተፍ አነሳስተዋል፤ ተሳታፊውም ይሁንታውን እጅግ በደመቀ ጭብጨባ ገልፀዋል፡፡
መድረኩ ለውይይት ክፍት ከመደርጉ በፊት በወጣት ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ ም/ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የፀረሽብርተኝነት ህጉን አንድነት ፓርቲ የሚቃወምበትን ምክንያት በዝርዝር አስርድተዋል፡፡ ወጣት ሀብታሙ በመግለጫቸው አንድነት የጸረ ሽብር አዋጁ እንዲሰረዝ ለምን የህዝብ ድምጽ ማሰባሰብ ጀመረ? ለሽብር አዋጁ መሰረዝ መጠየቂያ መነሻ የሆኑት ዛሬ በእስር እየማቀቁ የሚገኙት ጋዜጠኞች፣ፖለቲከኞችና መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን የተቃወሙ ሰዎች ናቸው፡፡ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ አንድነት ከየትኛውም ፓርቲ በተለየ ሽብርተኝነትን እንደሚቃወም በፕሮግራሙ አስፍሯል፡፡ ሽብርተኝነትን እንደሚያወግዝ በይፋ በፕሮግራሙ የገለጸን ፓርቲ ኢህአዴግ ‹‹ሽብርተኝነትን ያበረታታል በማለት መክሰሱ አስተዛዛቢም አነጋጋሪም ነው፡፡
ኢሕአዴግ ሕገ መንግሥታዊ መብቶቻችንን ተንበርክከን እንድንጠይቀው ይፈልጋል፣ ይህን ማድረግ ይህን እንድናደርግ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ማንነታችን አይፈቅድልንም ”ወጣት ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ ም/ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመቀጠልም ሲያስረዱ የጸረ ሽብር አዋጁ ለኢቴቪ ሰፊ ዕድል የሰጠ ነው ሲሉ ገልጠዋል። ሃብታሙ ይህንን ሲያብራሩ‹‹ህገ መንግስቱ አንድ ሰው በተጠረጠረበት ወንጀል እስከሚፈረድበት ድረስ ነጻ ሆኖ የመታየት መብት እንዳለው ያረጋግጣል ነገር ግን ኢቴቪ የተጠረጠሩ ሰዎችን ሽብርተኞች እያለ ይወነጅላል፡፡
ከሽብርተኝነት አዋጁ የተወሰኑ አንቀጾችን የጠቀሱት ሃብታሙ‹‹የሽብር አዋጁ ፖሊስ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ይፈቅዳል፡፡ነገር ግን ተመጣጣኝ ሃይል ምን ማለት ነው? ለአንዱ ፖሊስ ጥርስ መስበር ሊሆን ይችላል፣ለሌላው ደግሞ በ1997 እንደተደረገው ተመጣጣኝ ሃይል ማለት በጥይት የሰውን ደረትና ጭንቅላት መምታት ሊሆን ይችላል፡፡ለአንዳንዱ ደግሞ ከመንግስተ ሰማያት ቢሆንም አመጣሃለሁ ማለት ሊሆን ይችላል በማለት ተሰብሳቢውን ፈገግ አሰኝተዋል ፡፡
በመጨረሻም መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆኖ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። አንድ ተሰብሳቢ
በመጨረሻም መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆኖ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። አንድ ተሰብሳቢ
“መንግስት የሚሰራውን ልማት ለምን አታደንቁም?”
ጥያቄውን አቅርባለች ወጣት ሃብታሙ መልስ ሲሰጥ ‹‹ አንድ መንግስት ይህንን ማድረግ ግዴታው ነው፡፡ነገር ግን ሰብዓዊ ልማት ሳይኖር የቁስ ልማት ላይ ብቻ ማተኮር ያሳስበናል፡፡መንገስት ልማቱን ለጊዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ሁለንታዊ በማድረግ እንዲሰራ እንጠይቃለን፡፡ ኦባማ ተፎካካሪ ፓርቲዎቹን ይሄን ሰርቻለሁ አመስግኑኝ ብለው አይውቁ››ብሏል፡፡ ከሌላው ተሳታፊ ደግሞ
“በአሳፋሪ ሁኔታ የባልና ሚስትን ፆታዊ ግንኙነት የሚሰልል ወራዳ መንግስት ነው ያለን”
የስብሰባው ተሳታፊ
በመጨርሻም በታዋቂው ምሁር በዶ/ር ኃይሉ አርአያ የመዝጊያ ንግግር አድርገው ስብሰባው ተጠናቋል፡: በእለቱ የርዕዮተ አለሙ ወላጅ አባት በስበስባው የተገኙ መሆኑ ታውቋል:: ስብሰባው እንደተጠናቀቀም አንድነት የጀመረውን የፊርማ ማሰባሰብ ሂደት ቀጠሏል። በመብራት ሃይል አዳራሽ ጎላ ብለው ከተሰቀሉ መፈክሮች መካከል
የተቋማት ነጻነት የህዝብ ጥያቄ ነው!!
የስርዓት ለውጥ የህዝብ ጥያቄ ነው!
መብትን መጠየቅ ሽብርተኝነት አይደለም!

በእለቱ የስብሰባውን መንፈስ ለመበረዝና ለማወክ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተደራጅተው የገቡ ቢሆንም ከመድረኩ በታየው በሳል አመራር ሀሳባቸው ሳይሳካ ቀርቷል። በተጨማሪም ኢቲቪ ባልተጠራበት ስብሰባ ሶስት ካሜራዎችን አምጥቶ ሲቅርጽ የንበረ ሲሆን ከመድርክ በተላልፈው መልዕክት ኢቲቪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃብት በመሆኑ ትክክለኛውን ዘገባ ለሕዝብ በትክክል እንዲያቅርቡ ጥሪ ተድርጓል።
ምስጋና ከአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል
የመንግስትን አፈና ጥሶ በመብራት ሃይል አዳራሽ ለተገኘው ጀግናው የአዲስ አበባ ነዋሪ የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ ይህ ተነሳሽነት በሚቀጥሉት የህዝባዊ ንቅናቄ መድረኮች ላይም እንደሚቀጥል ዕምነቱን ይገልፃል፡፡
በተጨማሪም ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛውም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል በመወሰን ፓርቲያችን የሚሰጣችሁን ተልዕኮ በፍፁም ጨዋነትና ሰላማዊነት ለምትተገብሩት የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል አክብሮቱን ይገልፃል፤ መታሰራችሁና መደብደባችሁ ትግሉን እንደማያስቆመው እንዲያውም ሌሎች ታጋዮችን እንደሚያፈራ ዛሬም ለሁሉም ወገን አስገንዝባችኋልና፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ #ADDISABABA
ዝርዝር ዘገባው እንደድረሰን እናቀርባለን

No comments:
Post a Comment