ከብርሃኑ ተስፋዬ
ይድረስ ለአቶ ሀይለ ማሪያም ደሳለኝ ፖ.ሳ. ቁ. 1031 አዲስ አበባ
ጉዳዩ፣ የተደናበረው ማነው!
እንደ ጠቅላይ ሚኒሰትር ሳይሆን እንደ ተራ ካድሬ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አዳመጥሁት ገረመኝ፣ ፣ አግራሞት የፈጠረብኝ ደግሞ ከአፋዊ ህግ መንግስት አንቀጽ ቀንጨበው ጉዳዩን ለማስረዳት መሞከርዎ ሳይሆን ጠያቂዎ ያጎረሰችዎትን ቃላት እንዴት ለመጠቀም መሞከርዎ እሱዋ ሃላፊዎት እንጂ ጠያቂዎት ሳትሆን መሪ ካድሬዎት መሆኑዋን ማረጋገጥዎ ነው።
ይህ የተደናበረ መልስዎ ያጫረብኝ በሃይማኖት ሺፋን የፖሊቲካ እንቀስቃሴ ሃገሪቱ ውስጥ አለ ብለው አፍዎን ሞልተው የሸሪያ መንግስት ለመመስረት የተነሱ ናቸው ብለው መናገርዎ አንድን ጣልቃ አትግቡን የራሳችንን መጅሊሰ ያለ መንግስት ጣልቃ ገብነት ራሳችን እንምረጥ ያለን የሙስሊም ማህበረ ስብ ጥያቄ እንደዚህ ከፖሊቲካ ሃሳብ ጋር ማጋባተዎ የባጃጅነትዎን መጋረጃ ቀደው ለህዝብ ባደባባይ ራስዎን ያሳዩበትን በማየቴ ነው።
ለመሆኑ እየመራሁት አለሁት የሚሉትን መንግስት በዝርዝር እንመልከተው እስቲ፣
ገና ተጠባባቂ ተብለው ባቶ በረከት ስምኦን ከተሰየሙና የዱዳ ፓርላማ ማህተም ከማድረጉ በፊትና ካደረገልዎት ወቅት ጀምሮ የተዘጉ የሜዲያ ዉጤቶች ከደቡብና ሌሎች ክልሎች የተፈናቀሉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታ በመንግስት ወጪና ከቀረጥ ነጻ መብት ያለው ሃገሪቱን ያለወደብ ላስቀረና ማህበረ ሰባችንን በጎሳ ላከፋፈለ ህዝቡን አፈናቅሎ በሳንቲም ደረጃ መሬታችንን ላከራየና ለገደለ አርዮስ መታሰቢያ ድርጅት ለፓርላማ አቅርበው እንዲጸድቅ ማድረግዎ የሚጠቀሱት ናቸው።
ልብ ይበሉ በህዝብ ገንዘብ በሀገርም ሆነ በዉጭ እድሉን አግኝቶ ለተማረና የምእራብን የዴሞክራሲ አሰተዳደር ለማየት እድል ካጋጠመው እርስዎን ከመሰለ ግለሰብ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆቻችን እህቶቻችን ወንድሞቻችን እናትን አባቶቻችን በጠራራ ጸሃይ ሲደበደቡ ሲታሰሩና ሲገድሉ እይኔን ግንባር ያድርገው ብለው ምንም ያልተፈጠረ አድርገው እንዲህ አይነት ቃለ መጠይቅ ያሰደምማል።
ትንሽ ላሰታውሰዎ እስቲ አዋሳ እያሉ ሎቄ ላይ ሃሳባቸውን በመግለጻቸው በፌደራል አባላት ያስገደሉዋቸውና ያሰፈጁዋቸው የሲዳማ ብሄረ ሰብ አባላት ደም በእጅዎ የለም ከህዝብ በተሰበሰበ ታክስ ወጋጎዳ የሚባል አዲሰ ቑንቓ ፕሮጀክት መሃንዲሰነት መጫወትዎን እረሱት እንዴ።
መንግስትና ሀይማኖት በህገ መንግስታችን የተከበረ ነው ብለው ያፌዙና ሙስሊም ወንድሞቻችን ያነሱትን ጥያቄ ከፖሊቲካ ድርጅቶች እንቅስቃሴ ጋር ማጋባትዎና ከራስዎ አንደበት የወጡትን ቃላት ለመጥቀስ “…. አቃጥየ ፣ ደብድቤ፣ ገድየ፣ መስጊድ ማቃጠል ቤተ ክርስቲያን ማቃጠል…..የሸሪያ ህግ የበላይ መሆን አለበት፣ ህገ መንግስት መናድ” አምጥተው እድንጎርሳቸው ለምን ፈለጉ።
አቶ ሀይለ ማርያም እስኪ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያሰተለለፈውን ላሰታውሰዎት የተቀደደ ሰንደቅ አላማ በሙስሊሙ የአንዋር ተቃውሞ መሃል አሳይቶ ተቃጠለች የሚል ዘገባና አስተያየት በቤኒ መስጊድ እንደተደረገ ማናፈስ… ኮፈሌ ህዝብን ለመጨፍጨፍ ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ረብሻ አስነስቶ በመቅረጽ ያልሆነ ዘገባ ለህዝብ ማሰተላለፍ ፣ ሀዝበ ሙስሊሙ የሮመዳን ጾም ፍችን ከዚህ ቀደም እንደሚያደረጉት ሁሉ ሰታዲዮም ለማክበር ሲዘጋጅ ሙስሊሙን ለሁለት በመክፈል ላንዱ መግቢያ መስጠት ለሌላው መከልከል ሲተገበር የርሰዎ ቢሮ አያውቅም ነበር ቢሉኝ፣ በሰላማዊ መንገድ የተቃወሙ የሙስሊሙ ማህበር ሰብ በልዩ ሃይል እንዲደበደቡ ሲደረግና አዲሰ አበባ ሰው ሲፈነከትና ህጻናትና እርጉዞች ሲደበደቡ፣ ከአውሮፓ ፓርላማ ቃሊቲ ከሄዱ በሁዋላ የፖለቲካ እስረኞችን ለመጎበኘት መከልከላቸው የራስዎን መደናበር ከማመላከቱ ባሻገር አንድም ሀገሪቱን የምትመራበት ብለው የሚያላዝኑለት ቃላዊ ህገ መንግሰትን ወይ ያላነበቡት አሊያም እንደ ሌሎቹ ካድሬዎች በህወህት እንደ ኮካ ኮላ የተሞሉ ሆነው ነው የማይዎት።
በመሆኑም ይህንን ስጽፍ ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ መሆኑን ባልረሳውም እንደተናገሩት
ሳልሸራርፈው የተሞላሁትን ለመተግበር የተነሳሁ ነኝ ዲያቢሎሱ ቢሞትም ከላይ ኮቴን ከውስጥ የሱን ሰደርያ ለብሼ እንደምቀጥል እወቁት ያሉትን የመጀመሪያ ንግግርዎ ትዝ ይልዎት ይሆን?
ታዲያ እራሱን ሆኖ ከማይኖር ግለሰብ ህዝቡን ለመምራት ሳይሆን ራሱ ተደናብሮ ህዝብ ማደናገርን ከሚፈልግ የሚጠበቅ በመሆኑ እባክዎን ወደ ህሊናዎ ይመለሱ እላለሁ።
chillalo@gmail.com
No comments:
Post a Comment