Monday, August 19, 2013

የመንግስቱ ኃይለማርያም አጃቢ “የሌ/ኮ መንግስቱ ያልተነገሩ ሚስጢሮች” የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመው በተኑ

(ዘ-ሐበሻ) ዙምባብዌ በስደት የሚገኙት የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም በስማቸው የሚወጣው መጽሐፍ ቁጥር በ10ሮች የሚቆጠሩ ሲሆኑ እርሳቸው ግን አንድ መጽሐፍ ብቻ አውጥተዋል። “የመንግስቱ ትዝታዎች”። ዛሬ ደግሞ በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የፕሬዚዳንቱ የቀድሞ አጃቢ ያሳተመውና “የሌ/ኮ መንግስቱ ምስጢሮች” የተሰኘ መጽሐፍ መሰራጨቱን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል።
በቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም የቤተመንግስትና የሥራ ህይወት ዙሪያ እንደተጻፈ የሚነገርለት ይኸው “የሌ/ኮ መንግስቱ ያልተነገሩ ሚስጥሮች” የተሰኘው መፅሀፍ የተጻፈው የቀድሞው ልዩ ኃይል አባል እና የፕሬዝዳንት መንግስቱ አጃቢ በነበሩት እሸቱ ወንድሙ ወልደስላሴ እንደሆነ ታውቋል።
ይህ መጽሐፍ ባለ 120 ገፅ እንደሆነ የገለጹት የዘሐበሻ ዘጋቢዎች የመጽሐፉ ደራሲ ለ14 ዓመታት በልዩ ጥበቃነት መስራታቸውን አስታውቀዋል። እኚሁ የቀድሞው የመንግስቱ ኃይለማርያም አጃቢ ካሁን ቀደም “ህይወት በመንግስቱ ቤተመንግስት” በሚል ርዕስ ሁለት ቅፅ መጻሕፍትን ያሳተሙ መሆኑ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment