የግብፅ የፀጥታ ሀይሎች የአልቃይዳ ከፍተኛ አመራርና በመስከረም አንዱ ጥቃትና በለንደኑ የትራንስፖርት ጥቃቶች እጁ እንዳለበት የሚታመነውን የአይማን አልዛዋሪን ወንድም መሀመድ አልዛዋሪን በጋዛ አካባቢ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ ገለፁ፡፡
አሸባሪው መሀመድ አልዛዋሪ የማሀመድ ሙርሲ ደጋፊ ሲሆን በግብፅ ውስጥ አሁን ባለው ተቃውሞ ውስጥም ተሳታፊ ነው ፡፡
በግብፅ ካይሮ ከተማ በ1951 የተወለደው መሃመድ አልዘዋሪ ከኦሳማ ቢን ላደን ጋር በ1980ዎቹ አጋማሽ በፓኪስታን የተገናኙ ሲሆን የአልቃይዳ መረብ ዋና አስተባባሪና የቢላደን ቀን እጅ እንደነበርም ይታመናል፡፡
መሃመድ አልዘዋሪ በ1999 እ.ኤ.አ በግብፅ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን በኬንያና ታንዛኒያ የአሜሪካ ኢንባሲዎች ላይ ለደረሰውም ጥቃት ተጠያቂ ነው ይባላል፡፡
የአክራሪው ጂሀዲ ሳላፊስት ቡድን መሪ የሆነውን መሃመድ አልዘዋሪን እ.ኤ.አ በ2001 አሜሪካን ካወጣቻቸው እጅግ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ይገኝበታል፡፡
ምንጭ፡-ሜይል ኦን ላይን
No comments:
Post a Comment