ከኢንጅነር ረዲ ዘለቅ
እንደሚታወቀው የጎንደር ህዝብ ኩሩ ነው።በአንገቱ ላይ የሚያስረው ክርና የሚያንጠለጥለው መስቀል ክርስቲያን የመሆኑ ምልክት ብቻ ሳይሆን የታማኝነቱ ምልክት ነው። በጎንደሮች ዘንድ ፊርማ ከማተብ አይበልጥም። መካካድ ብሎ ነገር የለም። በጨለማ ያለምስክር የተቀበሉትን በብርሐን መመልስ ለጎንደሮች ባህል ነው። በጎንደሮች ዘንድ በፊርማ ከመስጠት በእምነት መስጠት የተለመደ ነው። በዚህ በጎንደር ሙስሊም ክርስቲያኑ የህይማኖት እንጂ የበህል ልዩነት የለም። አትንኩኝ ባይነት በጎንደር ህዝብ ዘንድ የተለመደ ነው። በዚህ በጎንደር ከተሞች አጼ ቴዎድሮስን የሚያሞግሱ ጽሁፎች ይታየሉ ጽሁፎቹ ሁሉ አጼ ቴዎድሮስ ያለጊዜው የተወለድ መሪ መሆኑንና ሀሳቡን ከግብ ሳዩAደርሱ በመሞታቸው የጎንደርን ህዝብ ቆጭት ይገልጻሉ። ይህንን በቀጣይ ጽሁፎቼ ወደፊት እንመጣበታለን። ዛሬ ትንሽ ስለ ደብረታቦር በዓል
የዛሬ 1803 ዓ/ም አካባቢ ቅዱስ ጴጥሮስ ለእኛ በዚህ መኖር ይሻለናል።ለአንተ፣ለሙሴና ለኤሊያስ አንዳንድ ጎጆ ቤት በዚሁ ሰርተን ከዚሁ እንኑር አለ። በዚህ ወቅት ልጆቻቸው ጠፍተውባችው የሚጨነቁ ወላጆችና በብርሐኑ ተደስተው ጅረፋቸውን አያስጮሁ የሚጫወቱ ሊጆች የተደበላለቀ ሁኔታ የነበረበት ወቅት ነበር ይባላል። አበቶች ሲናገሩ። ነገሩ እንዲህ ነው በወቅቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሶስቱን ደቀመዘሙርቱን ጴጥሮስን፣ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ወደ ደብረታቦር ተራራ አንደወጣና በወቅቱ ክርስቶስ የለበሰው ልብስ ከበረዶ የበለጠ እንደነጠና አካባቢው በብርሐን እንደተሞላ የምጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 9፥2- ጀምሮ ያለው ክፍል ይናገራል።
በዚህ ወቅት ኤሊያስን ከብሔረ ህየውየን፣ሙሴን ከብሔረ ሙታን አምጥቶ በአንድ ላይ ሲaሳያቸው ቅዱስ ጴጥሮስ በፍቅር አብሮ መኖር አስደሳች መሆኑን ሲናገር አንደነበረ ያሳያል። በዚህ ወቅት በዚያ አከባቢ የነበሩ እረኞች በቦታው በነበረው ብርሐን ገነ ጊዜ መስሎአቸው ጅራፋቸውን እያጮሁ ይጫወቱ ነበረ። በመንደራቸው አከባቢ ግን መሽቶ ስለነበረ ቤተሰቦቻቸው በልጆቹ መቅረት ተረብሸው ችቦ አያበሩ ልጆቻቸው ሳይበሉ ስለዋሉ የሚበሉት ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወደ ልጆቻቸው ተደናግጠው ይሄዱ ነበረ። በዚህ ጊዜ ልጆቻቸው ጅራፋቸውን እያስጮሁ (እያኖጉ)ሲጨወቱ አገኙወቸው።
ዛሬ በሀገራችን ልጆች ጅራፍ ሰርተው ያስጮሀሉ (ያኖጋሉ) ምሳሌው ያን ጊዜ ያልመሸ የመሰላቸው ልጆች ሲያስጮሁት የነበረው ምሳሌ ሲሆን በገጠሩ አካባቢ ትንንሽ ሙልሙል ዳቦ እየተጋገረ ለልጆች ይሰጣል ያም በወቅቱ እነርሱ ከብት በሚጠብቁበት ቦታ ብርሐን ስለነበረ ያልመሸ መስሎአቸው ሲጨወቱ ለነበሪት ልጆች ቤተሰቦቻቸው ሙልሙል ይዘው መሔዳቸውን ሲያመለክት በዚህ ዕለት ችቦ የሚበራው በወቅቱ ልጆቻቸውን ሊፈልጉ የነበሩት ቤተሰቦች ከቢታቸው ሲወጡ ጨለማ ስለነበረ ችቦ የመብራታቸው ምሳሌ ነው። የተከበረችሁና ውድ እንባቢያን ሌሎች በርካታ ምስጢራት ያለው ይህ በዓል የቤተ ክርስቲያኑን ለባለቤቶቹ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች ትቼ ስለባዓሉ ከኣባቶች የሰማሁትንና ያቀረብኩትን የጠበበውን አስፍታችሁ የራቀውን አቅርባችሁ የተሳሳተውን አስትካክላችሁ እንድታነቡልኝ በአክብሮት እጠይቀለሁ።
ቀጥታ ወደዛሬው ርዕሴ ስግባ
በሀገራችን ጽንፍ መያዝ አሁን አሁን እንደሙያም እንደባህልም እየሆነ መጥቶአል። አሁን ባለው ሁኔታ ከዲያስፖራው አስከ ፖለቲከኛው ከጋዜጥኛው እስከ ሀይማኖተኛው ከካድሬው እስከመንግሥት ሁሉም የመሰለውን ጽንፍ ይይዛል።ጽንፎች የሚመጡት ካለመግባባትና ከገግንዛቤ ጉድለት ሲሆን ጽንፍ ወይምጥግ በራሱ በሰየውየው ሊፈጠር ሲችል ሚዛናዊ ከልሆነ ትችትም የሚመጡ ጽንፎች አሉ።
የመንግሥት ጽንፈኝነት
መንግሥት እንደመንግሥት ጽንፍ መያዝ አልነለበረበትም። ምክንያቱምየሚቀርቡ ትችቶችን ብዙውን ጊዜ ሆደ ስፊ ሆኖ በአባትነት ባህሪይ ሁሉንም በእኩል መያዝ ሲጠበቅበት አንድ ጽንፍ መያዝ ተገቢ አይደለም። የአንድን ወገን የደገፈ በሌላኛው ወገን ላይ ጽንፍ መያዙ አይቀርም። ጽንፍ የተያዘበት ወገን ሌላኛውን ጫፍ በመያዝ ጽንፈኛ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ሁለት የተለያየ ሀሳብ የያዙ ሁለት አካላት ደግሞ ሁለት ጎን በጎን የተሰመሩ ቀጥተኛ መስመርን(parallel lines) ይመሰላሉ። ጎን በጎን የተሰመሩ ሁለት ቀጥተኛ መስመሮች ደግሞ የቱንም ያህል ርቀት ይዘው ዓለምን መቶ ጊዜ ቢዞሩ ሊግናኙ አይችሉም። ሁለቱም የተለያየ የራሳቸው የሆነ መሥመር ስለሚይዙሳይገናኙ የራሳቸውን መስመር ይዘው ህይወታቸውን ወይም ጎዞአቸውን ይቀጥላሉ።
አሁን ባለንበትወቅታዊ ሁኔታ ገዢው ፓርቲ የሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ እርሱን ከማይደግፉት ሁሉ ከእርሱ በተቃራኒው እንዲቆሙአድርጎአቸዋል። የተቃወሙትን ሁሉ የተቹትን ሁሉ በአንድም ይሁን በሌላ የማራቅና የመወንጀል ሁኔታ አለ። ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ ተንታኞችን፣የሀይማኖት ሰባኪዎችን፣ የፖለቲካ መሪዎችንና የመሳሰሉትን የሚሰጡትን ትችት አጥንቶና አይቶ ለተሰጠው ትችት መስትካከል ያለበትን ከማስትካከል መልስ ለሚገባው መልስ ከመስጠት ይልቅ በቀጥታ ሀሳቡን በሰጠው ወይምትችቱን በሰጠው ግለሰብ ላይ የውግዘት ናዳ ማውረድ የተለመደ ነው። በዚህም የተወገዘው የራሱን ተከተይ ይዞ የራሱን ጽንፍ ስለሚይዝ ሀግራችን በርካታ ጊዜ ዋጋ ከፍላበታለች። አንድ ጽንፍ በያዘ አመለካከት ሳቢያ በርካታ ህዝብ በእርስ በርስ ጦርነቱ ጊዜ አጥተናል። በርካቶችም አካለ ጎዶሎ ሆነውብናል። በጦርነቱ ለሞቱት የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ ሆኖ ለማልቀስ ተቸግረን ቅጥ ያጣ ልቅሶ ሆኖብናል።
የደርግን መንግሥት ስንመለክት አገዛዙን የተቃወሙ ሰዎችን በቀጥታ ከመወንጀልና ከማውገዝ የዘለለ አገዛዙን የጠሉበትን ሁኔታ አይቶ ሁኔታዎች እንዲስትካከሉ ለማድረግ የሞከረው ሙክራ አልነበረም። በዚህም በወቅቱ እርሱ ወንበዴ ካላቸው የውቅቱ የትጥቅ ታጋዮች ከሚመስሉት ጋር የተገናኘ ከሀዲ ገንጣይ አስገንጣይ በማለት በጥርጣሬ ብቻ በርካቶች በንግድ ሥራቸውና በህይወታቸው ፈተና ደርሶባቸዋል። ሁኔታው በመጨረሻ አጠቃላይ ብሔርን ወደማውገዝ አድርሶት ነበር። በዚህም ፕሬዚዳንት መነገሥቱ ሀይለማሪያም የወቅቱን ታጋዮች እንኩዋን በመሳሪየ የኢትዮጵያ ህዝብ አፋፍ ላይ ወጥቶ ሽንቱን ቢሸና ጎርፍ ሆኖ ይወስዳቸዋል ለማለት በቅተው ነበር።
ያን ጊዜ እርሳቸው እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ወጥቶ አፋፍ ላይ ወጥቶ እርሳቸው እንዳሉት አድርጎ ቢሆንናጎርፉ ቢመጣ ጎርፍ እርሳቸው እንዳሰቡት የወቅቱን እርሳቸው ወንበዴ የሚሉአቸውን ብቻ አይወስድም ነበር። በዚየ አካባቢ ያሉትን ኢትዮጵያውያንን ጭምር እንጂ ስለዚህ እርሳቸው የሚጠሉአችው እስከጠፉ ድረስ ሌሎች እንደሆኑት ቢሆኑም ግድ አልነበራቸውም ማለት ነው።በዚህ መንግስትም ቢሆን መንግስትን ከመይደግፉ ወገኖች ገር መገናኘት የተለያየ ስም ያሰጣል። ተቀዋሚውም ቢሆን አንድ አበሉ ከመንግስት አካለት ጋር ታይቶ ሻይም ሆነ ቡና ሲጠጣ ቢያየው ያወግዘዋል። ይህ የአንድ ወገንተኝነት የመያዝ ችግር ሲሆን እኔ ብቻ ትክክል ነኝ የሚል ጽንፈኝነት ነው።ማንም ፍጹም ሊሆን አይችልም። ሁሉም የየራሱ ደካማ ጎን አለው ስለዚህ በጠንካራ ጎኑ ሲመሰገን በደካማ ጎኑ ደግሞ ይወቀስ ዘንድ ተገቢ ነው። ወቀሳው ወይም ትችቱ ጽንፈኝነት ከሌለው ለተተችው ለትምህርትና ለመስተካከል ይጠቅመዋል። ነገር ግን ወቀሳው ወገንትኝነት ካለውና ወደ አንድ ጎን ያዘነበለ ከሆነ ሌላ ጽንፍ ከመፍጠር የዘለለ ምንም ጥቅም የለውም። ይህ ደግሞሀገርን መከፋፈል ለሚሹ በተለይ አፍሪካን እንደርስት አድርገው ባንድም ይሁን በሌላ እንዳትረጋጋ ለሚሰሩት ቅኝ ገዥዎች እንጂ ለእኛ ለአፍሪካውያን ምንም ጥቀም የለውም።
በሀገራችን አንዳንድ የሚጀመሩ መልካም ሥራዎች ግባቸውን የማይመቱት ጽንፈኝነት ስለሚቀድማቸው ነው። ጽንፈኝነት መልካም ነገሮችን ቀድሞ ከመጣ የመጣው መልካም ነገርና መልካሙን ነገር ይዞ የመጣውን በአንድ ላይ እንዲፈረጁ ስለሚያደርግ ደጉን አስተሳሰብ የክፋት ያስመስለዋል። በዚህም ደገኛይቱ አስተሳሰብ በክፉ ሀሳብ ትበለጣለች።
የሀገራችንን መግሥታት ከቀድሞ እስካሁን ያሉትን ስንመለከት እነርሱ ካቀዱት ውጭ ያሉ አስተሳሰቦች ሁሉ እንደስህተት ይቆጠራሉ። በዚህም የትኛውም ጋዜጠኛም ይሁን ፖለቲከኛ የሚጽፈውና የሚናገረው እንደአጥፊ አስተሳስብ ስለሚያዩትሲያዳምጡትም ይሁን ሲያነቡት ከተቃውሞ አንጻር ነው። በዚህም በጽንፍ ችግር ምክንያት መንግስት ከጋዜጠኛውም የጽሁፍ ትችት ይሁን ከፖለቲክኘው ንግግር ማግኘት የሚገባውን ሳያገኝ ይቀርና ነገሮችን በበጎ እንዳይተረጉም ያደርገዋል። ቅን ነገሮቹ በቅን ያልታዩለት ጋዜጠኛም ይሁን ፖለቲከኛ ነገሮቹ በቅን ስላልታዩለት ሌላ ጽንፍ ይይዛል። በዚህም ጽንፎችና ጽንፈኞች ይፈጠራሉ። ከዚህ በመነሳት የጻፍው ማን ነው እንጂ የተጻፈው ምንድን ነው? የተናገረው ማንነውእንጂ ምን ተናገር የሚሉ ደገኛጥያቄዎች ይቀራሉ።
ገዥው ፓርቲ የግል ጋዜጦች እንዲነበቡ ያደርጋል። የሚነበቡት ጋዜጠኞች እንጂ ጋዜጣው ግን አይደለም። ለዚህም የአንዱን ጋዜጠኛ ጽሁፍ ሲተች በውስጡ ያለውንነቀፋ እንጂ የሰጠውንሀሰብ አይተችም። የጸፈበትን ምክንያት በማስረጃ ቢዘረዝር እንኩዋን ሊያስከስሰው የሚችለውምን ጉዳይ ከመፈለግ የዘለለ ለሀገር የሚጠቅም የሰጠውን ሀሳብ የተያዘው ጽንፍ እንደ ሀሳብ ይጋርደዋል። በዚህም ቀጥሎ ይህ ጽንፍ ከጸሐፊው ነጻ ሀሳብ ውጪ የፀሐፊውን ዘር ወደምቆጠር ይመጣና ጉዳዩ ግለስቡ ወደ ተወለደበት ብሔር እንዲሄድ ይደርጋል። ይህንን የጻፈው የዚህ ብሔር ስለሆነ ይህንኛውን ብሔር ሰልሚጠላው ነው የሚል የማይረባ እሳቤ ውስጥ ይገባል።
የጋዜጠኛ ጽንፍ
አንዳንድ የግል ጋዜጠኞች የሚጽፉት ነቀፋን ብቻ ስለሆነ ገዢውን ፓርቲ ጽንፍ እንዲይዝ የደርጉታል። ድሮ የአማርኛ አስተማሪየ ክፍሉን ባለስታውሰውም ደገኛ የአመርኛ አስትመሪ ነበሩና ክሁለተኛ ደረጃ በእንዱ ክፍል ውስጥ ብቻ ስለ ገሎ ማዳንና አድኖ መግደል ሲያስትምሩኝ የነገሩኝ ሀሳብ እስካሁን ከልቤ ጠፍቶ አያውቅም። እርሳቸው እንድን ሰው ስህተቱን ስትነግረው ከሰራው መልካም ስራ የምትጀምር ከሆነ መጀመሪያ ስላዳንከው ስለነገርከው መልካም ነገር ሲል ቀጠይ የምትወቅሰውን ወቀሳ ጆሮ ሰጥቶ ያዳምጥሀል። ከስህተቱም ይማራል። ቀድመህ ካጠፋው ስህተቱ ከጀመርክ ግን ቀድመህ ገደልህዋል የሞተ ሰው ደግሞ ጆሮው አይሰማም ይላሉ። ማንም ሰው አጥፍተሀልን አይወድም ምክንያቱም ሁሉም የሚሰራው ሥራ ለራሱ ትክክል ነውና ነው። ጥፋት መስሎ የሚታየው ከውጭ ላለ ሰው ስለሁነ ውጭ ያለው ሰው ለአጥፊው በሚገባው ቁዋንቁዋ በፍቅር ሊነግረው ይገባል ፍቅር ሁሉን የማድረግ ሀይል ስላለው። እውነቱን ለመናገር ሌለውን የሚተቸው ሁሉ ለራሱ ሲተች አይፈልግም። በራሱ ላይ ሊደረግበት የማይፈልገውን ግን በሌላው ላይ ሲያደርግ ግን ምንም አይመስለውም።
በአንድ ወቅት እኔ በአገር አቁወራጭ አውቶቡስ ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ ስሄድ አውቶቡሳችን ለፍተሻ ወለቴ አካባቢ ይቆማል። በዚህ ወቅት አንድ ጋዜጣ አዙዋሪ በፊት ለፊት ገጹ ላይ የአቶ መለስንና የኮለኔር መንግስቱ ሀይለማርያምን ፎቶ ጎን ብጎን ይዞ የወጣና ርዕሱ መለስ ዜናውና መንግስቱ ሀይለመርያም ተፋጠጡ የሚል ርዕስ የለበት ጋዜጣ ይዞ እርሱም ይህንኑ እያነበበ ይሸጣል። እኔም ፍጥጨውን ለማወቅ ጋዜጣውን ገዛሁ በእርግጥ ያን ዕለት ያንን ጋዜጣ ያልገዛ ተሳፋሪ የለም። ከህጻናት በስተቅር በሌሎች ተሳፋሪዎችም ይህ ይኖራል የሚል ግምት አለኝ። ጋዜጣውን ሳነበው ግን ፈጽሞ ስለሁለቱ ሰዎች የሚያወራ አንድ ዘለላ ህሳብ የለውም። ይህ አይነቱ አካሄድ አሁን ያለውን የመንግስት አንድ አቅጠጫ መያዝ አስትዋጽኦ አብርክቶዋል የሚል ግምት አለኝ።
በአንዳንድ ጋዜጠኞች ላይ ጽንፈኝነት ይታያል። ይህ ጽንፈኝነት እነርሱ የመንግስት ጋዜጠኞች ከሚሉአቸው ጋር አብሮ ያለምሄድ ትችትን ከነጋቲቭ ጀምሮ በነጋትቭ መጨረስ መነቁዋቆር ነገሮችን ባላንስ ያለመድረግ ወደ አንድ ጎን ማዘንበልና የጫፍዋን ጥግ መያዝሌላ ጫፍ እንዲፈጠር ማድረግ ይታይባቸዋል። በእርግጥ ጋዜጠኛና ፖለቲክኛ ይለያያል። ፖለቲከኛ ለሥልጣን ስለሚሄድ የገዥውን ፐርቲ መልካም ጎን ነግሮ እራሱ የሚደበደብበትን ዱላ ማቀበል የለበትም። ስህተቱን ፈልጎ ያንን ስህተት እርሱ ቢሆን እንደማይሰራውና የተሻለ መስራት እንደሚችል በመንገርና በማሳመን ቢሄድ ተቀናቃኝ እስከሆነ ድረስ ችግር ያለው አይመስለኝም። ጋዜጠኛ ግን ያንን ያክል ጫፍ ይዞ መሔድ አለበት የሚል እምነቱ የለኝም። ጋዜጠኛ የሚለው ስም በራሱ የሚያሳየው ወገንተኛ ማለት አይደለምና ነው። በእርግጥ አንድ ሰውከጋዜጠኛነት ወደ ፖለቲከኛነት ራሱን መለውጥ ይችላል። ከዚያም የራሱን አስተሳሰብና ያመነበትን መጻፍም ይሁን መስተለለፍ መብት ነው። ይቅርታ ይደረግልኝና የጋዜጠኝነት ስልጠና ያልወሰድኩ በዚህኛው መስክ መሐይም ስለሆንኩ የምሰጠው አስተያየት ፈሩን የሳተ ክሆነ ማንም በአሳማኝ ነጥብ ለሚሰጥኝ አስተያየት በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ።
አንዳንድ የመንገስት ጋዜጥኞች ደግሞ የግል ጋዜጠኞች በመረጀ ተደግፈው የሚጽፉት ነገር እንደሌለ የግል ጋዜጠኞች አስተማሪ እንዳልሆኑ ይጽፋሉ። ይህ ሌላኛው ጫፍ ሲሆን የእነርሱ ጫፍ መያዝ ደግሞ በተደራሲያን ላይ ተጽእኖ በማሳደሩ አንዳንድ እነርሱ የሚያዘጋጁዋቸው ጋዜጦች በውስጠቸው ካለው ማስታወቂያ ውጪ ሌላው ሀሳብ እንዳይነበብ አድርጎታል። በዚህም ከመንግሥት ውጪ ያለው ሰው የመንግስትን ሀሳብ እንዳይረዳ አድርጎታል። ይህ ጽንፍ የመያዝ ጣጣ ነው።
አሁን ያለውን አንዳንድ የግል ጋዜጠኞች የሚስጡት ትችት ቀድሞ ተተችውን ስለሚገለው ቀጣይ ለሚሰጥ መልካም ህሳብ አድማጭ እያጣ ይገኛል። ከዚህም በዘለለ አንድ ጊዜ ለሚሰጠው አስተየየት ብቻ ሳይሆን የተሻለ አስተሳሰቡ ሁሉ እንዳይደመጥ እያደረገው ስለሆነ ያ ሁሉ ልፋት ከንቱና እሪ በከንቱ እየሆነ መጥቶአል። በዚህ ረገድ መንግስት ጫፍ ከያዘና ወግንትኛ ሆኖ ጽንፍ ከያዘ በስሩ ያሉት ካድሬዎች ሁሉ ጫፍ እንዲይዙ ስለሚያደርግ የተሻለ አስተሳሰብ እንዳይዙ ይሆናል። የተሰጠውን ትችት አንብቦ ትክክለኛአካሄድ እንዲጎለብት የተሳሳት አረማመድ እንዲስትካከል ከማድረግ ይልቅ በፀሐፊው ጽሁፉ እንዲገመገም ያደርገውና የአስትያይት ሰጪው ልፋት የባከነው ጊዜ ሁሉ aሐፊው እገሌ ከሆነ ስለ እኛ በጎ አይጽፍም በሚል ቅድመ ትንበያ ምክንያትሀሳቡን ሳይረዱት ይቀራሉ። የጋዜጠኛውም ብዙ መረጃዎችን አዘጋጅቶ የለፋበት ጽሁፍ ከንቱ ይሆናል። ይህ የሚመጣው ተደራሲያን ጽንፍ ስለሚይዙ እገሌ የሚጽፈው እንዲህስለሆነ ከዚህ ተነስቶ ነው በሚል አያነቡትም። ተቀራኒው ቡድን ሊታረምበት የማይችልጽሁፍ ደግሞ ከንቱ ነው።
በሌለ መልኩ አንድ ጋዜጠኛ ጽንፍ ይዞ የሚሄድ ከሆነ ተከታዮችን ጽንፈኞች ያደርገቸዋል። በዚህም የዚህ ጋዜጠኛ ተከታዮች እርሱ የሚናገርው ትክክል ሌላው የሚናገረውና የሚጽፈው ስህተት አድርገው ስለሚቆጥሩት የእርሱ ተደራሲያን አንድ ጥግ ይይዛሉ ማለት ነው። በዚህ በኩልከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈለጊ ነው። የምንጽፈው ጽሁፍ በተለይ ጋዜጠኛ ከሆንን ጋዜጣው እንዲሸጥ አለበለዚያ ተከታይ እንዲኖረን ከሆነ እኛ ለራሳችን የሀገር አደጋ ነን ማለት ነው። ጋዜጠኛ ኦፒኒየን መጻፍ የለበትም የሚል ጭፍን አመለካከት የለኝም። ነገር ግን ጋዘጠኛ ሁለት ነገሮችን ባላንስ ማድረግ አለበት። ሁል ጊዜ የውሸታሙን እረኛ ማስታወስ ተገቢ ነው። ዛሬ የመንግስት ፈተና ይሆናል ብየ የማስበው ተደጋጋሚ ያልሆነን ነገር ለማሳመን የሚጠቀምባቸው ነገሮፕችን ነው። በተለያዩ ጊዜያት ለማሳመን የሚያቀርባቸው ማስረጀዎች አሁን አሁን እንደልማድ እየተወስዱ ይገኛሉ። በዚህም መንግስት ለወደፊት የከፋ ነገር ገጥሞት አሰማኝ የሆነ መረጀ ቢያቀርብ እንኩዋንበተቀበይነቱ ላይ ችግር ሊፈጥርበት ይችላል። ይህ በጣም አደገኛ ነገር ነው። ሀገርንም ችግር ውስጥ ሊከት ይችለል። ይህ ከሆነ ደግሞ ጉዳቱ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሆነ ማለት ነው።
አሁን አንዳንድ የል ጋዘጠኞች መንግስትን ሲነቅፉ ምንም እንዳልሰራ አድርገው ነው። በዚህ መልኩ መሰራት በሚገበው በኩል አልተሰራም ሊሆን ሲገባው ምንም አልተሰራም የሚለው ሌላው ጽንፍ ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ የመንግስት ጋዜጠኞች መንግስት ያልሰራው ስራ እንደሌለ ሌላ ጫፍ ወይም ጥግ ይዘው ሲለፍፉ ይስማል። ይህ እነርሱ እንደሚሉት መንግስት ያንን ሁሉ ሥራ ግን ሰርቶት አይደለም። በዚህም ተደራሲያንን በሁለት ሊከፈሉ ችለዋል። የመንግስት ወገን የሆኑት ያልሰሩትን ሁሉ ሰርተዋል የሚላቸውን ጋዜጣ እንደ እዲስ ዘመን ያሉትን ጋዜጦች ብቻ ሲያነቡ የሞከሩትን ሁሉ ፈጽሞ እንዳልሰሩ የሚቆጥረውን አንዳንድ የግል ጋዜጦችን ፈጽሞ ሊያዩዋቸው አይፈልጉም። ይህ ጉዳት አለው በተቃራኒው ጎራ ያለው ሰው ሀሳባችንን አንብቦ ከስህተቱ እንዲስተካከል አያደርገውም።
የዲያስፖራው ጽንፈኝነት
ይህ የራስን ጥግ የያዝ ጽንፈኝነት መዘዙ በዲየስፖራው ዘንድ አሀቲ የሆነችውን ቤተክርስቲያን ለሁለት ሶስት ሰንጥቆአት ይታያል። አንድ ሰው መጥፎ ሊሆን ይችላል። ይህ ሰው መጥፎ የሆነው በራሱ መጥፎ ስለሆነ እንጂ ኦሮሞ፣አማራ፣ትግሬ፣ወላይታ፣ሀዲያ፣ከምባታ… ስለሆነ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ወደቤተእግዚአብሔር ሄደህ መባህን ከመስጠትህ በፊት ያዘነብህ ወንድም ካለህ ሄደህ ይቅርታ ጠይቅ ይላል። በዲያስፖራው አካባቢ ደግሞ ይህ የነገሌ ቤተክርስቲያን ነውና እዚያ እንሄድም ይባላል። ይህ ጽንፍ የመያዝ አባዜ ደግሞ አንዲትን ቤቴክርስቲያን የነገሌ ነችና እኛ እንሄድም። የእኛ ማርያም እንትን አካባቢ ያለችው ነች ይባላል። ይህንን ያህል ጽንፍ ተይዞ ደግሞ ይጸለያል።
ይህ ጉዞአችን አጠገብ ላጠገብ የተሰመሩ ነገር ግን ጎን ለጎን ከምሄድ ውጭ የማይገናኙ ሁለት ቀጥተኛ መስመሮችን አስመስሎናል። ይህንን ይዘን የምንሄድ ክሆነ መቼም ልንገናኝ አንችልም። አሁን ባለው ሁኔታ በብሔር የተጠቀመ አንድም ብሔር የለም ግለሰቦች ግን አልተጠቀሙም አላልኩም። ግለሰብ ደግሞ ብሔርን አይወክልም። ቀደም ባሉት ጊዜያት አማራ ገዥ እንደነበረ ይነገራል። ነገር ግን በአማራ ክልል ያሉ አመሮችን ብናያቸው ምስኪኖችና ከመቶ አንዱ እንኩዋን ጫማ ያላደረጉ ናቸው። በአማራ ነኝ ስም የገዛ ሊኖር ይችል ይሆናል። ነገር ግን የአማራ ህዝብ ግን ወክሎት አይደለም። ለኣማራ ህዝብ ግን የፈየደው ነገር የለም። የአማራ ህዝብ ዛሬም ድረስ በሽተኛ በቃሬዛ በአልጋ ተሸክሞ ክሊኒክ የሄዳል። ይህ ነገር ዛሬ በትግራይም፣ በኦሮሚያም፣በደቡም፣ በቤኒሻንጉልም … አለ። ስለዚህ ሁሉን ህዝብ ያካተተ ትግል ማድረግ ሲገባ ተለያይተን ለማምጣት የምንፈልገው ለውጥ ጉንጭ አልፋ ወግ ነው የሚሆነው።ይቀጥላል ቸር ይግጠመ
ወደ ዋናው ርዕሴ ከመግበቴ በፊት ዛሬ በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደርበደብረ ታቦርከተማ እገኛለሁ።ደብረታቦርን የመረጥኩት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለምዶ የደብረታቦር በዓል ዛሬ ስለሚከበር ከዚያ ጋር አያይዤ ትንሽ ለማለት ነው። ባለፈው እንደነግርኩዋችሁ አሁን መንገዶች ክልሎችን እያያገናኙ ስለሆነ በቀጥታ ከወልዲያ በደብረታቦር አድርጌ ሰሜን ጎንደር እስከ ጎርጎራ ሄጄ ስለነበር ስለእያንዳንዱ ትንሽ ትንሽ ለማለትእሞክራለሁ።
ስለደብረታቦር ከተማ ጋዜጠኛ ብዙአየሁ ወንድሙ በአንድ ወቅት ጎግል በተባለው ጋዜጣ ዘርዝር አድርጎ የጻፈው ነገር ነበር። በደርግ ጊዜ መቼም በርካታ እናቶች ልጆቻችውን ከብሔራዊ ውትድርና ለመደበቅ የቀበሌ ሊቀመንበር እንዳያይባችው ይሆኑ የነብሩት መሳቀቅ የቅርብ ጊዜ ትዝታ የነብረ ሲሆን የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም ብለው ልጆቻቸውን የሚገሉባቸው ሰዎችም ነበሩ። ጋዜጠኛ ብዙአይሁ ወንድሙ እንደጻፈው ሴትዮዋ ልጃቸው በመላኩ ተፈራ ተይዞባቸው ሞቱን ሲጠባበቅ ባለበት ሁኔታ መላኩ ተፈራ ያለበት ድረስ በመሄድ መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም የዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም።
እንዳሉና ልጃቸውን እንዳስፈቱ በወቅቱ ታስሮ የነበረውና እናቱ እርሱ የታሰረበትን ቦታ ለማግኘት ስትንከራተት የታጠቀችው መቀነት በላይዋ ላይ አልቆ ስለነበረችው እናቱ እያለቀስ የተናገረውን የዚያን ጊዜውን ታሳሪ የአሁኑን መምህርና የአንድ ዘመናዊ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ ጠይቆ ታሪኩን ሲጽፈው በዚያው ስለነበርኩ ጉዳዩን ለማወቅ ችያለሁ። የወቅቱን የእርሱን እስርና የእናቱን መንከራተት ያስታወሰው ግለሰብ ስለእናቱ ሲያነሳ ከዓይኑ በጉንጮቹ ላይ ይወርድ የነበረውን እንባ አስቤ ይህችን ቦታ ስፅፍ አስለቅሶኛል። ይህ ህዝብ ያልታደለ ከአንዱ መከራ ወደ ቀጣዩ ችግር መሸጋገር በእርግጥ አሳዛኝ ነው።ስለደብረታቦር ከተማ ጋዜጠኛ ብዙአየሁ ወንድሙ በአንድ ወቅት ጎግል በተባለው ጋዜጣ ዘርዝር አድርጎ የጻፈው ነገር ነበር። በደርግ ጊዜ መቼም በርካታ እናቶች ልጆቻችውን ከብሔራዊ ውትድርና ለመደበቅ የቀበሌ ሊቀመንበር እንዳያይባችው ይሆኑ የነብሩት መሳቀቅ የቅርብ ጊዜ ትዝታ የነብረ ሲሆን የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም ብለው ልጆቻቸውን የሚገሉባቸው ሰዎችም ነበሩ። ጋዜጠኛ ብዙአይሁ ወንድሙ እንደጻፈው ሴትዮዋ ልጃቸው በመላኩ ተፈራ ተይዞባቸው ሞቱን ሲጠባበቅ ባለበት ሁኔታ መላኩ ተፈራ ያለበት ድረስ በመሄድ መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም የዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም።
እንደሚታወቀው የጎንደር ህዝብ ኩሩ ነው።በአንገቱ ላይ የሚያስረው ክርና የሚያንጠለጥለው መስቀል ክርስቲያን የመሆኑ ምልክት ብቻ ሳይሆን የታማኝነቱ ምልክት ነው። በጎንደሮች ዘንድ ፊርማ ከማተብ አይበልጥም። መካካድ ብሎ ነገር የለም። በጨለማ ያለምስክር የተቀበሉትን በብርሐን መመልስ ለጎንደሮች ባህል ነው። በጎንደሮች ዘንድ በፊርማ ከመስጠት በእምነት መስጠት የተለመደ ነው። በዚህ በጎንደር ሙስሊም ክርስቲያኑ የህይማኖት እንጂ የበህል ልዩነት የለም። አትንኩኝ ባይነት በጎንደር ህዝብ ዘንድ የተለመደ ነው። በዚህ በጎንደር ከተሞች አጼ ቴዎድሮስን የሚያሞግሱ ጽሁፎች ይታየሉ ጽሁፎቹ ሁሉ አጼ ቴዎድሮስ ያለጊዜው የተወለድ መሪ መሆኑንና ሀሳቡን ከግብ ሳዩAደርሱ በመሞታቸው የጎንደርን ህዝብ ቆጭት ይገልጻሉ። ይህንን በቀጣይ ጽሁፎቼ ወደፊት እንመጣበታለን። ዛሬ ትንሽ ስለ ደብረታቦር በዓል
የዛሬ 1803 ዓ/ም አካባቢ ቅዱስ ጴጥሮስ ለእኛ በዚህ መኖር ይሻለናል።ለአንተ፣ለሙሴና ለኤሊያስ አንዳንድ ጎጆ ቤት በዚሁ ሰርተን ከዚሁ እንኑር አለ። በዚህ ወቅት ልጆቻቸው ጠፍተውባችው የሚጨነቁ ወላጆችና በብርሐኑ ተደስተው ጅረፋቸውን አያስጮሁ የሚጫወቱ ሊጆች የተደበላለቀ ሁኔታ የነበረበት ወቅት ነበር ይባላል። አበቶች ሲናገሩ። ነገሩ እንዲህ ነው በወቅቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሶስቱን ደቀመዘሙርቱን ጴጥሮስን፣ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ወደ ደብረታቦር ተራራ አንደወጣና በወቅቱ ክርስቶስ የለበሰው ልብስ ከበረዶ የበለጠ እንደነጠና አካባቢው በብርሐን እንደተሞላ የምጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 9፥2- ጀምሮ ያለው ክፍል ይናገራል።
በዚህ ወቅት ኤሊያስን ከብሔረ ህየውየን፣ሙሴን ከብሔረ ሙታን አምጥቶ በአንድ ላይ ሲaሳያቸው ቅዱስ ጴጥሮስ በፍቅር አብሮ መኖር አስደሳች መሆኑን ሲናገር አንደነበረ ያሳያል። በዚህ ወቅት በዚያ አከባቢ የነበሩ እረኞች በቦታው በነበረው ብርሐን ገነ ጊዜ መስሎአቸው ጅራፋቸውን እያጮሁ ይጫወቱ ነበረ። በመንደራቸው አከባቢ ግን መሽቶ ስለነበረ ቤተሰቦቻቸው በልጆቹ መቅረት ተረብሸው ችቦ አያበሩ ልጆቻቸው ሳይበሉ ስለዋሉ የሚበሉት ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወደ ልጆቻቸው ተደናግጠው ይሄዱ ነበረ። በዚህ ጊዜ ልጆቻቸው ጅራፋቸውን እያስጮሁ (እያኖጉ)ሲጨወቱ አገኙወቸው።
ዛሬ በሀገራችን ልጆች ጅራፍ ሰርተው ያስጮሀሉ (ያኖጋሉ) ምሳሌው ያን ጊዜ ያልመሸ የመሰላቸው ልጆች ሲያስጮሁት የነበረው ምሳሌ ሲሆን በገጠሩ አካባቢ ትንንሽ ሙልሙል ዳቦ እየተጋገረ ለልጆች ይሰጣል ያም በወቅቱ እነርሱ ከብት በሚጠብቁበት ቦታ ብርሐን ስለነበረ ያልመሸ መስሎአቸው ሲጨወቱ ለነበሪት ልጆች ቤተሰቦቻቸው ሙልሙል ይዘው መሔዳቸውን ሲያመለክት በዚህ ዕለት ችቦ የሚበራው በወቅቱ ልጆቻቸውን ሊፈልጉ የነበሩት ቤተሰቦች ከቢታቸው ሲወጡ ጨለማ ስለነበረ ችቦ የመብራታቸው ምሳሌ ነው። የተከበረችሁና ውድ እንባቢያን ሌሎች በርካታ ምስጢራት ያለው ይህ በዓል የቤተ ክርስቲያኑን ለባለቤቶቹ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች ትቼ ስለባዓሉ ከኣባቶች የሰማሁትንና ያቀረብኩትን የጠበበውን አስፍታችሁ የራቀውን አቅርባችሁ የተሳሳተውን አስትካክላችሁ እንድታነቡልኝ በአክብሮት እጠይቀለሁ።
ቀጥታ ወደዛሬው ርዕሴ ስግባ
በሀገራችን ጽንፍ መያዝ አሁን አሁን እንደሙያም እንደባህልም እየሆነ መጥቶአል። አሁን ባለው ሁኔታ ከዲያስፖራው አስከ ፖለቲከኛው ከጋዜጥኛው እስከ ሀይማኖተኛው ከካድሬው እስከመንግሥት ሁሉም የመሰለውን ጽንፍ ይይዛል።ጽንፎች የሚመጡት ካለመግባባትና ከገግንዛቤ ጉድለት ሲሆን ጽንፍ ወይምጥግ በራሱ በሰየውየው ሊፈጠር ሲችል ሚዛናዊ ከልሆነ ትችትም የሚመጡ ጽንፎች አሉ።
የመንግሥት ጽንፈኝነት
መንግሥት እንደመንግሥት ጽንፍ መያዝ አልነለበረበትም። ምክንያቱምየሚቀርቡ ትችቶችን ብዙውን ጊዜ ሆደ ስፊ ሆኖ በአባትነት ባህሪይ ሁሉንም በእኩል መያዝ ሲጠበቅበት አንድ ጽንፍ መያዝ ተገቢ አይደለም። የአንድን ወገን የደገፈ በሌላኛው ወገን ላይ ጽንፍ መያዙ አይቀርም። ጽንፍ የተያዘበት ወገን ሌላኛውን ጫፍ በመያዝ ጽንፈኛ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ሁለት የተለያየ ሀሳብ የያዙ ሁለት አካላት ደግሞ ሁለት ጎን በጎን የተሰመሩ ቀጥተኛ መስመርን(parallel lines) ይመሰላሉ። ጎን በጎን የተሰመሩ ሁለት ቀጥተኛ መስመሮች ደግሞ የቱንም ያህል ርቀት ይዘው ዓለምን መቶ ጊዜ ቢዞሩ ሊግናኙ አይችሉም። ሁለቱም የተለያየ የራሳቸው የሆነ መሥመር ስለሚይዙሳይገናኙ የራሳቸውን መስመር ይዘው ህይወታቸውን ወይም ጎዞአቸውን ይቀጥላሉ።
አሁን ባለንበትወቅታዊ ሁኔታ ገዢው ፓርቲ የሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ እርሱን ከማይደግፉት ሁሉ ከእርሱ በተቃራኒው እንዲቆሙአድርጎአቸዋል። የተቃወሙትን ሁሉ የተቹትን ሁሉ በአንድም ይሁን በሌላ የማራቅና የመወንጀል ሁኔታ አለ። ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ ተንታኞችን፣የሀይማኖት ሰባኪዎችን፣ የፖለቲካ መሪዎችንና የመሳሰሉትን የሚሰጡትን ትችት አጥንቶና አይቶ ለተሰጠው ትችት መስትካከል ያለበትን ከማስትካከል መልስ ለሚገባው መልስ ከመስጠት ይልቅ በቀጥታ ሀሳቡን በሰጠው ወይምትችቱን በሰጠው ግለሰብ ላይ የውግዘት ናዳ ማውረድ የተለመደ ነው። በዚህም የተወገዘው የራሱን ተከተይ ይዞ የራሱን ጽንፍ ስለሚይዝ ሀግራችን በርካታ ጊዜ ዋጋ ከፍላበታለች። አንድ ጽንፍ በያዘ አመለካከት ሳቢያ በርካታ ህዝብ በእርስ በርስ ጦርነቱ ጊዜ አጥተናል። በርካቶችም አካለ ጎዶሎ ሆነውብናል። በጦርነቱ ለሞቱት የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ ሆኖ ለማልቀስ ተቸግረን ቅጥ ያጣ ልቅሶ ሆኖብናል።
የደርግን መንግሥት ስንመለክት አገዛዙን የተቃወሙ ሰዎችን በቀጥታ ከመወንጀልና ከማውገዝ የዘለለ አገዛዙን የጠሉበትን ሁኔታ አይቶ ሁኔታዎች እንዲስትካከሉ ለማድረግ የሞከረው ሙክራ አልነበረም። በዚህም በወቅቱ እርሱ ወንበዴ ካላቸው የውቅቱ የትጥቅ ታጋዮች ከሚመስሉት ጋር የተገናኘ ከሀዲ ገንጣይ አስገንጣይ በማለት በጥርጣሬ ብቻ በርካቶች በንግድ ሥራቸውና በህይወታቸው ፈተና ደርሶባቸዋል። ሁኔታው በመጨረሻ አጠቃላይ ብሔርን ወደማውገዝ አድርሶት ነበር። በዚህም ፕሬዚዳንት መነገሥቱ ሀይለማሪያም የወቅቱን ታጋዮች እንኩዋን በመሳሪየ የኢትዮጵያ ህዝብ አፋፍ ላይ ወጥቶ ሽንቱን ቢሸና ጎርፍ ሆኖ ይወስዳቸዋል ለማለት በቅተው ነበር።
ያን ጊዜ እርሳቸው እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ወጥቶ አፋፍ ላይ ወጥቶ እርሳቸው እንዳሉት አድርጎ ቢሆንናጎርፉ ቢመጣ ጎርፍ እርሳቸው እንዳሰቡት የወቅቱን እርሳቸው ወንበዴ የሚሉአቸውን ብቻ አይወስድም ነበር። በዚየ አካባቢ ያሉትን ኢትዮጵያውያንን ጭምር እንጂ ስለዚህ እርሳቸው የሚጠሉአችው እስከጠፉ ድረስ ሌሎች እንደሆኑት ቢሆኑም ግድ አልነበራቸውም ማለት ነው።በዚህ መንግስትም ቢሆን መንግስትን ከመይደግፉ ወገኖች ገር መገናኘት የተለያየ ስም ያሰጣል። ተቀዋሚውም ቢሆን አንድ አበሉ ከመንግስት አካለት ጋር ታይቶ ሻይም ሆነ ቡና ሲጠጣ ቢያየው ያወግዘዋል። ይህ የአንድ ወገንተኝነት የመያዝ ችግር ሲሆን እኔ ብቻ ትክክል ነኝ የሚል ጽንፈኝነት ነው።ማንም ፍጹም ሊሆን አይችልም። ሁሉም የየራሱ ደካማ ጎን አለው ስለዚህ በጠንካራ ጎኑ ሲመሰገን በደካማ ጎኑ ደግሞ ይወቀስ ዘንድ ተገቢ ነው። ወቀሳው ወይም ትችቱ ጽንፈኝነት ከሌለው ለተተችው ለትምህርትና ለመስተካከል ይጠቅመዋል። ነገር ግን ወቀሳው ወገንትኝነት ካለውና ወደ አንድ ጎን ያዘነበለ ከሆነ ሌላ ጽንፍ ከመፍጠር የዘለለ ምንም ጥቅም የለውም። ይህ ደግሞሀገርን መከፋፈል ለሚሹ በተለይ አፍሪካን እንደርስት አድርገው ባንድም ይሁን በሌላ እንዳትረጋጋ ለሚሰሩት ቅኝ ገዥዎች እንጂ ለእኛ ለአፍሪካውያን ምንም ጥቀም የለውም።
በሀገራችን አንዳንድ የሚጀመሩ መልካም ሥራዎች ግባቸውን የማይመቱት ጽንፈኝነት ስለሚቀድማቸው ነው። ጽንፈኝነት መልካም ነገሮችን ቀድሞ ከመጣ የመጣው መልካም ነገርና መልካሙን ነገር ይዞ የመጣውን በአንድ ላይ እንዲፈረጁ ስለሚያደርግ ደጉን አስተሳሰብ የክፋት ያስመስለዋል። በዚህም ደገኛይቱ አስተሳሰብ በክፉ ሀሳብ ትበለጣለች።
የሀገራችንን መግሥታት ከቀድሞ እስካሁን ያሉትን ስንመለከት እነርሱ ካቀዱት ውጭ ያሉ አስተሳሰቦች ሁሉ እንደስህተት ይቆጠራሉ። በዚህም የትኛውም ጋዜጠኛም ይሁን ፖለቲከኛ የሚጽፈውና የሚናገረው እንደአጥፊ አስተሳስብ ስለሚያዩትሲያዳምጡትም ይሁን ሲያነቡት ከተቃውሞ አንጻር ነው። በዚህም በጽንፍ ችግር ምክንያት መንግስት ከጋዜጠኛውም የጽሁፍ ትችት ይሁን ከፖለቲክኘው ንግግር ማግኘት የሚገባውን ሳያገኝ ይቀርና ነገሮችን በበጎ እንዳይተረጉም ያደርገዋል። ቅን ነገሮቹ በቅን ያልታዩለት ጋዜጠኛም ይሁን ፖለቲከኛ ነገሮቹ በቅን ስላልታዩለት ሌላ ጽንፍ ይይዛል። በዚህም ጽንፎችና ጽንፈኞች ይፈጠራሉ። ከዚህ በመነሳት የጻፍው ማን ነው እንጂ የተጻፈው ምንድን ነው? የተናገረው ማንነውእንጂ ምን ተናገር የሚሉ ደገኛጥያቄዎች ይቀራሉ።
ገዥው ፓርቲ የግል ጋዜጦች እንዲነበቡ ያደርጋል። የሚነበቡት ጋዜጠኞች እንጂ ጋዜጣው ግን አይደለም። ለዚህም የአንዱን ጋዜጠኛ ጽሁፍ ሲተች በውስጡ ያለውንነቀፋ እንጂ የሰጠውንሀሰብ አይተችም። የጸፈበትን ምክንያት በማስረጃ ቢዘረዝር እንኩዋን ሊያስከስሰው የሚችለውምን ጉዳይ ከመፈለግ የዘለለ ለሀገር የሚጠቅም የሰጠውን ሀሳብ የተያዘው ጽንፍ እንደ ሀሳብ ይጋርደዋል። በዚህም ቀጥሎ ይህ ጽንፍ ከጸሐፊው ነጻ ሀሳብ ውጪ የፀሐፊውን ዘር ወደምቆጠር ይመጣና ጉዳዩ ግለስቡ ወደ ተወለደበት ብሔር እንዲሄድ ይደርጋል። ይህንን የጻፈው የዚህ ብሔር ስለሆነ ይህንኛውን ብሔር ሰልሚጠላው ነው የሚል የማይረባ እሳቤ ውስጥ ይገባል።
የጋዜጠኛ ጽንፍ
አንዳንድ የግል ጋዜጠኞች የሚጽፉት ነቀፋን ብቻ ስለሆነ ገዢውን ፓርቲ ጽንፍ እንዲይዝ የደርጉታል። ድሮ የአማርኛ አስተማሪየ ክፍሉን ባለስታውሰውም ደገኛ የአመርኛ አስትመሪ ነበሩና ክሁለተኛ ደረጃ በእንዱ ክፍል ውስጥ ብቻ ስለ ገሎ ማዳንና አድኖ መግደል ሲያስትምሩኝ የነገሩኝ ሀሳብ እስካሁን ከልቤ ጠፍቶ አያውቅም። እርሳቸው እንድን ሰው ስህተቱን ስትነግረው ከሰራው መልካም ስራ የምትጀምር ከሆነ መጀመሪያ ስላዳንከው ስለነገርከው መልካም ነገር ሲል ቀጠይ የምትወቅሰውን ወቀሳ ጆሮ ሰጥቶ ያዳምጥሀል። ከስህተቱም ይማራል። ቀድመህ ካጠፋው ስህተቱ ከጀመርክ ግን ቀድመህ ገደልህዋል የሞተ ሰው ደግሞ ጆሮው አይሰማም ይላሉ። ማንም ሰው አጥፍተሀልን አይወድም ምክንያቱም ሁሉም የሚሰራው ሥራ ለራሱ ትክክል ነውና ነው። ጥፋት መስሎ የሚታየው ከውጭ ላለ ሰው ስለሁነ ውጭ ያለው ሰው ለአጥፊው በሚገባው ቁዋንቁዋ በፍቅር ሊነግረው ይገባል ፍቅር ሁሉን የማድረግ ሀይል ስላለው። እውነቱን ለመናገር ሌለውን የሚተቸው ሁሉ ለራሱ ሲተች አይፈልግም። በራሱ ላይ ሊደረግበት የማይፈልገውን ግን በሌላው ላይ ሲያደርግ ግን ምንም አይመስለውም።
በአንድ ወቅት እኔ በአገር አቁወራጭ አውቶቡስ ከአዲስ አበባ ወደ ጅማ ስሄድ አውቶቡሳችን ለፍተሻ ወለቴ አካባቢ ይቆማል። በዚህ ወቅት አንድ ጋዜጣ አዙዋሪ በፊት ለፊት ገጹ ላይ የአቶ መለስንና የኮለኔር መንግስቱ ሀይለማርያምን ፎቶ ጎን ብጎን ይዞ የወጣና ርዕሱ መለስ ዜናውና መንግስቱ ሀይለመርያም ተፋጠጡ የሚል ርዕስ የለበት ጋዜጣ ይዞ እርሱም ይህንኑ እያነበበ ይሸጣል። እኔም ፍጥጨውን ለማወቅ ጋዜጣውን ገዛሁ በእርግጥ ያን ዕለት ያንን ጋዜጣ ያልገዛ ተሳፋሪ የለም። ከህጻናት በስተቅር በሌሎች ተሳፋሪዎችም ይህ ይኖራል የሚል ግምት አለኝ። ጋዜጣውን ሳነበው ግን ፈጽሞ ስለሁለቱ ሰዎች የሚያወራ አንድ ዘለላ ህሳብ የለውም። ይህ አይነቱ አካሄድ አሁን ያለውን የመንግስት አንድ አቅጠጫ መያዝ አስትዋጽኦ አብርክቶዋል የሚል ግምት አለኝ።
በአንዳንድ ጋዜጠኞች ላይ ጽንፈኝነት ይታያል። ይህ ጽንፈኝነት እነርሱ የመንግስት ጋዜጠኞች ከሚሉአቸው ጋር አብሮ ያለምሄድ ትችትን ከነጋቲቭ ጀምሮ በነጋትቭ መጨረስ መነቁዋቆር ነገሮችን ባላንስ ያለመድረግ ወደ አንድ ጎን ማዘንበልና የጫፍዋን ጥግ መያዝሌላ ጫፍ እንዲፈጠር ማድረግ ይታይባቸዋል። በእርግጥ ጋዜጠኛና ፖለቲክኛ ይለያያል። ፖለቲከኛ ለሥልጣን ስለሚሄድ የገዥውን ፐርቲ መልካም ጎን ነግሮ እራሱ የሚደበደብበትን ዱላ ማቀበል የለበትም። ስህተቱን ፈልጎ ያንን ስህተት እርሱ ቢሆን እንደማይሰራውና የተሻለ መስራት እንደሚችል በመንገርና በማሳመን ቢሄድ ተቀናቃኝ እስከሆነ ድረስ ችግር ያለው አይመስለኝም። ጋዜጠኛ ግን ያንን ያክል ጫፍ ይዞ መሔድ አለበት የሚል እምነቱ የለኝም። ጋዜጠኛ የሚለው ስም በራሱ የሚያሳየው ወገንተኛ ማለት አይደለምና ነው። በእርግጥ አንድ ሰውከጋዜጠኛነት ወደ ፖለቲከኛነት ራሱን መለውጥ ይችላል። ከዚያም የራሱን አስተሳሰብና ያመነበትን መጻፍም ይሁን መስተለለፍ መብት ነው። ይቅርታ ይደረግልኝና የጋዜጠኝነት ስልጠና ያልወሰድኩ በዚህኛው መስክ መሐይም ስለሆንኩ የምሰጠው አስተያየት ፈሩን የሳተ ክሆነ ማንም በአሳማኝ ነጥብ ለሚሰጥኝ አስተያየት በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ።
አንዳንድ የመንገስት ጋዜጥኞች ደግሞ የግል ጋዜጠኞች በመረጀ ተደግፈው የሚጽፉት ነገር እንደሌለ የግል ጋዜጠኞች አስተማሪ እንዳልሆኑ ይጽፋሉ። ይህ ሌላኛው ጫፍ ሲሆን የእነርሱ ጫፍ መያዝ ደግሞ በተደራሲያን ላይ ተጽእኖ በማሳደሩ አንዳንድ እነርሱ የሚያዘጋጁዋቸው ጋዜጦች በውስጠቸው ካለው ማስታወቂያ ውጪ ሌላው ሀሳብ እንዳይነበብ አድርጎታል። በዚህም ከመንግሥት ውጪ ያለው ሰው የመንግስትን ሀሳብ እንዳይረዳ አድርጎታል። ይህ ጽንፍ የመያዝ ጣጣ ነው።
አሁን ያለውን አንዳንድ የግል ጋዜጠኞች የሚስጡት ትችት ቀድሞ ተተችውን ስለሚገለው ቀጣይ ለሚሰጥ መልካም ህሳብ አድማጭ እያጣ ይገኛል። ከዚህም በዘለለ አንድ ጊዜ ለሚሰጠው አስተየየት ብቻ ሳይሆን የተሻለ አስተሳሰቡ ሁሉ እንዳይደመጥ እያደረገው ስለሆነ ያ ሁሉ ልፋት ከንቱና እሪ በከንቱ እየሆነ መጥቶአል። በዚህ ረገድ መንግስት ጫፍ ከያዘና ወግንትኛ ሆኖ ጽንፍ ከያዘ በስሩ ያሉት ካድሬዎች ሁሉ ጫፍ እንዲይዙ ስለሚያደርግ የተሻለ አስተሳሰብ እንዳይዙ ይሆናል። የተሰጠውን ትችት አንብቦ ትክክለኛአካሄድ እንዲጎለብት የተሳሳት አረማመድ እንዲስትካከል ከማድረግ ይልቅ በፀሐፊው ጽሁፉ እንዲገመገም ያደርገውና የአስትያይት ሰጪው ልፋት የባከነው ጊዜ ሁሉ aሐፊው እገሌ ከሆነ ስለ እኛ በጎ አይጽፍም በሚል ቅድመ ትንበያ ምክንያትሀሳቡን ሳይረዱት ይቀራሉ። የጋዜጠኛውም ብዙ መረጃዎችን አዘጋጅቶ የለፋበት ጽሁፍ ከንቱ ይሆናል። ይህ የሚመጣው ተደራሲያን ጽንፍ ስለሚይዙ እገሌ የሚጽፈው እንዲህስለሆነ ከዚህ ተነስቶ ነው በሚል አያነቡትም። ተቀራኒው ቡድን ሊታረምበት የማይችልጽሁፍ ደግሞ ከንቱ ነው።
በሌለ መልኩ አንድ ጋዜጠኛ ጽንፍ ይዞ የሚሄድ ከሆነ ተከታዮችን ጽንፈኞች ያደርገቸዋል። በዚህም የዚህ ጋዜጠኛ ተከታዮች እርሱ የሚናገርው ትክክል ሌላው የሚናገረውና የሚጽፈው ስህተት አድርገው ስለሚቆጥሩት የእርሱ ተደራሲያን አንድ ጥግ ይይዛሉ ማለት ነው። በዚህ በኩልከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈለጊ ነው። የምንጽፈው ጽሁፍ በተለይ ጋዜጠኛ ከሆንን ጋዜጣው እንዲሸጥ አለበለዚያ ተከታይ እንዲኖረን ከሆነ እኛ ለራሳችን የሀገር አደጋ ነን ማለት ነው። ጋዜጠኛ ኦፒኒየን መጻፍ የለበትም የሚል ጭፍን አመለካከት የለኝም። ነገር ግን ጋዘጠኛ ሁለት ነገሮችን ባላንስ ማድረግ አለበት። ሁል ጊዜ የውሸታሙን እረኛ ማስታወስ ተገቢ ነው። ዛሬ የመንግስት ፈተና ይሆናል ብየ የማስበው ተደጋጋሚ ያልሆነን ነገር ለማሳመን የሚጠቀምባቸው ነገሮፕችን ነው። በተለያዩ ጊዜያት ለማሳመን የሚያቀርባቸው ማስረጀዎች አሁን አሁን እንደልማድ እየተወስዱ ይገኛሉ። በዚህም መንግስት ለወደፊት የከፋ ነገር ገጥሞት አሰማኝ የሆነ መረጀ ቢያቀርብ እንኩዋንበተቀበይነቱ ላይ ችግር ሊፈጥርበት ይችላል። ይህ በጣም አደገኛ ነገር ነው። ሀገርንም ችግር ውስጥ ሊከት ይችለል። ይህ ከሆነ ደግሞ ጉዳቱ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሆነ ማለት ነው።
አሁን አንዳንድ የል ጋዘጠኞች መንግስትን ሲነቅፉ ምንም እንዳልሰራ አድርገው ነው። በዚህ መልኩ መሰራት በሚገበው በኩል አልተሰራም ሊሆን ሲገባው ምንም አልተሰራም የሚለው ሌላው ጽንፍ ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ የመንግስት ጋዜጠኞች መንግስት ያልሰራው ስራ እንደሌለ ሌላ ጫፍ ወይም ጥግ ይዘው ሲለፍፉ ይስማል። ይህ እነርሱ እንደሚሉት መንግስት ያንን ሁሉ ሥራ ግን ሰርቶት አይደለም። በዚህም ተደራሲያንን በሁለት ሊከፈሉ ችለዋል። የመንግስት ወገን የሆኑት ያልሰሩትን ሁሉ ሰርተዋል የሚላቸውን ጋዜጣ እንደ እዲስ ዘመን ያሉትን ጋዜጦች ብቻ ሲያነቡ የሞከሩትን ሁሉ ፈጽሞ እንዳልሰሩ የሚቆጥረውን አንዳንድ የግል ጋዜጦችን ፈጽሞ ሊያዩዋቸው አይፈልጉም። ይህ ጉዳት አለው በተቃራኒው ጎራ ያለው ሰው ሀሳባችንን አንብቦ ከስህተቱ እንዲስተካከል አያደርገውም።
የዲያስፖራው ጽንፈኝነት
ይህ የራስን ጥግ የያዝ ጽንፈኝነት መዘዙ በዲየስፖራው ዘንድ አሀቲ የሆነችውን ቤተክርስቲያን ለሁለት ሶስት ሰንጥቆአት ይታያል። አንድ ሰው መጥፎ ሊሆን ይችላል። ይህ ሰው መጥፎ የሆነው በራሱ መጥፎ ስለሆነ እንጂ ኦሮሞ፣አማራ፣ትግሬ፣ወላይታ፣ሀዲያ፣ከምባታ… ስለሆነ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ወደቤተእግዚአብሔር ሄደህ መባህን ከመስጠትህ በፊት ያዘነብህ ወንድም ካለህ ሄደህ ይቅርታ ጠይቅ ይላል። በዲያስፖራው አካባቢ ደግሞ ይህ የነገሌ ቤተክርስቲያን ነውና እዚያ እንሄድም ይባላል። ይህ ጽንፍ የመያዝ አባዜ ደግሞ አንዲትን ቤቴክርስቲያን የነገሌ ነችና እኛ እንሄድም። የእኛ ማርያም እንትን አካባቢ ያለችው ነች ይባላል። ይህንን ያህል ጽንፍ ተይዞ ደግሞ ይጸለያል።
ይህ ጉዞአችን አጠገብ ላጠገብ የተሰመሩ ነገር ግን ጎን ለጎን ከምሄድ ውጭ የማይገናኙ ሁለት ቀጥተኛ መስመሮችን አስመስሎናል። ይህንን ይዘን የምንሄድ ክሆነ መቼም ልንገናኝ አንችልም። አሁን ባለው ሁኔታ በብሔር የተጠቀመ አንድም ብሔር የለም ግለሰቦች ግን አልተጠቀሙም አላልኩም። ግለሰብ ደግሞ ብሔርን አይወክልም። ቀደም ባሉት ጊዜያት አማራ ገዥ እንደነበረ ይነገራል። ነገር ግን በአማራ ክልል ያሉ አመሮችን ብናያቸው ምስኪኖችና ከመቶ አንዱ እንኩዋን ጫማ ያላደረጉ ናቸው። በአማራ ነኝ ስም የገዛ ሊኖር ይችል ይሆናል። ነገር ግን የአማራ ህዝብ ግን ወክሎት አይደለም። ለኣማራ ህዝብ ግን የፈየደው ነገር የለም። የአማራ ህዝብ ዛሬም ድረስ በሽተኛ በቃሬዛ በአልጋ ተሸክሞ ክሊኒክ የሄዳል። ይህ ነገር ዛሬ በትግራይም፣ በኦሮሚያም፣በደቡም፣ በቤኒሻንጉልም … አለ። ስለዚህ ሁሉን ህዝብ ያካተተ ትግል ማድረግ ሲገባ ተለያይተን ለማምጣት የምንፈልገው ለውጥ ጉንጭ አልፋ ወግ ነው የሚሆነው።ይቀጥላል ቸር ይግጠመ
No comments:
Post a Comment