Tuesday, August 20, 2013

*እንዴት ይረሳል*

***መታሰቢያነቱ ለሞቱት ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ላበዱት ሌጋሲ አስቀጣዮች***
ብዙ የተቀበረና የተዳፈነ ብሶታችንን የሚኮረኩር ዘገባ ኢቲቪ ሲያስተላልፍ ቆይቷል ውሸት የባህሪው ተብሎ የሚነገርለት ኢቲቪ የጠቅላይ ሚኒሰትሩን የጤና ሁናቴ መታመም ሳይናገር በስተመጨረሻ በኢንፌክሽን ምክንያት ታመው በህክምና ሲረዱ ቆይተው እንደሞቱ አደባብሰው ለኢትዮጵያ ህዝብ አሳወቁ
/ ሚኒስትሩ ከመሞታቸው 2 አመት ወዲ በካንሰር ህመም እንደሚሰቃዩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገሩ ነበር :: በተለይ በቡድን 8 የመሪዎች ስብሰባ ላይ ዓርብ ግንቦት 10 / 2004 ከፍተኛ ተቋውሞ ደርሶባቸው ነበር በአሜሪካ አገር ውስጥ በሬገን ህንጻ በምግብ ዋስትና ስብሰባ ላይ አራት የአፍሪካ መሪዎች እንደነበሩና ሶስቱ በአግባቡ ንግግራቸውን እንደጨረሱ / ሚኒስትሩ ግን ንግግራቸው ሲጀምሩ ነበር ተቋውሞ በጋዜጠኛ በአበበ ገላው ከፍተኛ ድምፅ አዳራሹ የተናወጠው << WE NEED FREEDOM >> በሚል እና በተለያዩ የነጻነት ቃላት ጥያቄ አዳራሹ በነበልባል ድምፅ አስተጋባው በአዳራሹ ውስጥ ያሉ ታዳሚ እነ ባራክ ኦባማን እንዲሁም ትልልቅ የአለም መሪዎች ትኩረት እንዲሰጡበት ያደረገ ታላቅ ግዜም ነበር
ከዚያን በኋላ ነበር /ሚኒስትሩ ሳይኮሎጂካሊ የጤናና ፖለቲካዊ ክስረት የደረሰባቸው ከዚሁሉ ኪሳራ በኃላ ከቴሌቪዥን እይታ ውጪ ሆኑ ብዙም ሳይቆይ መታመማቸው በአንዳንድ ሚዲያ ይገለፅ ጀመረ ከትንሽ ቀናትም በኃላ መሞታቸው ሰማን በግል ሚዲያ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደግሞ ከወር አስራምስት ቀን በኃላ መሞታቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አሳወቀ ብዙም አልተደነቁም ውሸት የመስሪያቤቱ መርህ ሰለሆነ ብቻ ሳይሆን ለፕሮፓጋዳም የሚጠቀምበት ግዜም ያስፈልገውም ስለነበረ ነው።
ነሐሴ 15 / 2004 የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ኢትዮጵያ ታላቅ መሪዋን አጣች ብሎ ዘገበ። ከዚህ በኋላ ነበር ፕሮፓጋዳውን መንፋት የጀመረው ኢቲቪ ብዙዋኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢቲቪ ለየት የሚያደርግ ንግግር ሲናገሩም ተሰምተዋል ኢትዮጵያ ትንሿን መሪና አምባገነኑን አጣች !!
ሕዝብን ሲሰድቡ፣ ሕዝብን ሲንቁ፣ ሲያዋርዱ፣ ፓርላማ ውስጥ ተጠየኩ ብለው በአሽሙር ሲመልሱ ነው የምናየው የነበረው፣ ስለ አገራቸው ሕዝብ ፍቅር የሌላቸው መሆናቸውን ነው የምናውቀው፣ስለ ኢትዮጵያ ሲጠየቁ ስለ ጋና፣ ስለ ቻይና ሲናገሩ ነበር የምናዳምጠው የነበረው ላለፉት 21 ዓመታት እንዲ ሆኖ ሳለ ከሞቱ በኋላ በዚያን 15 ቀናት ውስጥ ያየነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀግና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለራዕይ ኢትዮጵያ ራሷን ምድሯን ከፍ አድርገው ወደ ሰማይ ያስባረኩ እስኪመስል ድረስ ኢቲቪ ፕሮፓጋንዳውን ሲሰጥ እንደነበር ይታወቃል ይህም የሆነበት ምክንያት ሙሾ ለማሰባሰብ የተጠቀመበት ዘዴ መሆኑን አያጠያይቅም ከጥቂት ወራት ብንመለከት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማት ሲነካ ሲፈራርስ ፣አባቶች ሲሰደዱ ፣በሙስሊሞች እምነት ላይ የመንግስት ጣልቃገብነት ጥያቄ ሳይመለስ ባለበት ወቅት፣ጋዜጠኞች በሚታሰሩበት ወቅት ፣ለፖለቲከኞች ዕድል ተሰቶ የማይታወቅበት አገር፣ፖለቲከኞች ተስማምተው እንኳን አውርተው የማያውቁባት አገር፣ ነፃነትና ፍትህ በሌለበት አገር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በግዳጅ አልቅሱ ማለት ተገቢ አይመስለኝም ነበር
ለኢትዮጵያ ሕዝብ 21 ዓመታት ግፍና በደሉን ተሸክሞ ያሳለፋቸው መሪር አዘን እራሱ ሕዝቡ ውስጥ ነው ያለው እንጂ ሰው እንዲሰብክለት ስለበደሉ አይፈልግም ሕዝቡ አንድ ቀን እንኳን ሳያያቸው በቴሌቪዥን መስኮት ብቻ የተመለከታቸው ህዝብ እሳቸው ሲያልፉ እንኳን መንገድ ተዘግቶ ይታጠራል ሕዝቡ ማለፍ ፣መንቀሳቀስ በማይችልበትና በመሳሪያ አፈሙዝ እያስፈራሩትና ፊትን አዙር እንዳትመለከት ተብሎ እሳቸውን እንዳያይ ይሁን ከቡዳ ለመከላከል አይገባኝም ነበር ምን አልባት 97 ምርጫ ሚያዚያ 29 ቀን ነበር በመስቀል አደባባይ ላይ ነበረ መአበል ባሉት ሰልፍ ያየናቸው ምን ዋጋ አለው ሚያዚያ 30 ቀን በንጋታው ደግሞ ሱናሜ የሆነባቸው በጣም የሚታዩት ካልን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ነበር ያን ጥሩ የሆነውን የስድብ ችሎታቸውን ሲያወርዱብን፣ ከሳቸው በላይ አዋቂ እንደሌለ የሚቆጥሩበት የግል ፓርላማ ፣አንድ ቀን እንኳን ሀገሬ ብለው ባልጠሯት ፓርላማ፣ሚኒስትሩ አሳሪና ፈቺ መሆናቸው በምናይበት ፓርላማ ነበር ኧረ ምኑ ተብሎ………………….
ይህን ሁሉ ሕዝብ ሳያቅ ቀርቶ አልነበረም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፕሮፓጋንዳውን ሲነፋ የነበረው ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ይባል የለ
ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ጀምሮ ጥቁር በጥቁር በመሆን ሽር ጉዱን ለማሳመር ተፍተፍ እያለ የለቅሶ ሴርሞኒ በአስለቃሽ ተዋናኝነት ለማሳመር ሲጠበብ ያሳለፈበት ግዜም ነበር። ይህም ደግሞ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜም ይመስለኛል ።ህገ-መንግስቱም እንደሚያዘው ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ፐሬዝዳንቱ ሲሞቱ የአንድ ቀን ብሔራዊ አዘን እንዲሆን ነው የሚደነግገው ነገር ግን ህገ መንግስቱን በጣሰ ሁኔታ አስራ አምስት ቀን ብሔራዊ አዘን እንዲሆን ተደርጓል። ይህ ድርጊት በአገር ላይ ያለው ጉዳት ስናይ ከባድ ነው። አስራ አንድ ፐርሰንት በእድገት ጎዳና ላይ ነች ብለው የሚናገሩላት አገር ምን ያህል ኪሳራ እንደደረሰ ማንም የሚገነዘበው ጉዳይ ነው ።ሕጉስ ቢሆን የራሳቸው አይደል ምንስ ይደረጋል
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሕዝብ ትኩረት እዲሰጥበት ብሎ የተለያዩ ሰዎችን ለለቅሶ ድምቀት በቲቪ መስኮት አውጥቶም ነበር ።ለምሳሌ የኢትዮጵያ አርቲስቶችና ዘማሪንም ጭምር ስለ መለስ ዜናዊ እልፈት በተመለከተ እንዲያወድሱ የተደረገው,,,,,በተለይ ጥበብና ጠቢባኞች፣ ከያንያን፣ ገጣሚዎች፣ሙዚቀኞች፣ሙዚቃ አቀናባሪዎች፣ቴአትረኞች፣ የማስታወቂያ ባለሙያዎች ወዘተ የጠቅላይ ሚኒስተሩን እልፈት አስመልክቶ ወደውም ይሁን ተገደው ወይም ለማስመሰል አልያም በትክክለኛው ስሜት የተለያየ አስተያየት ሰተው ደመቅ ለማድረግም ተደርጎ ነበር።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሃያ አንድ ዓመት የአመራር ውጤት የሚያደንቁ ገድል ሲነገር ቆራጥ አመራራቸውን ፣የስራ ታታሪነታቸውን፣ጀግና መሆናቸውን፣ እረፍትለምኔ መሆናቸውን፣ለኢትዮጵያ እንደሚቆረቆሩ፣ አገር ወዳድ መሆናቸውን በዘፈን፣ በዝማሬና በግጥም ተወድሰውም ነበር።
ሐዘኑን ወዶ ያዘነው ወዶ አዝኖ ነው ይባላል ወዶ ያላዘነውን ግን ለምንስ ይጎዳ በስንቱ ነገርስ ተጎድቶስ ይችላል።ይኽው እንደምናየው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቲቪ እንኳን አይቶአቸው የማያቁትን ሰው አልቅሱላቸው ብሎ ማስገደድ ምንስ ይባላል 21 ዓመታት አልቅሶ የተጎዳን ሕዝብ ድጋሚ እንዲያለቅስ ማስደረግ አምባገነናዊ ስርዓትን ማስፋፋት ይመስለኛል የሕዝብ ፍቅር የሌላቸውን መሪ የሕዝብ ፍቅር እንዳላቸው ተደርጎ በኢቲቪ ሰዎችን እየጠየቁ ጥሩነታቸውን እንዲናገሩ እንዲመሰክሩ እንዲያወድሱ ማድረጉ ለምን አስፈለገ ? ገድል ያለው ሰው ራሱ ስራው ይመሰክራል በተለይ ለተመልካች የሐዘን ገቢ ማሰባሰቢያ ያደረጉት የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስበው << እሳቸውን ስላሉ ነበረ ጎዳና የወጣነው እሳቸውን ተማምነን ነው አሁን አባት የሌለው ሰው ሆነናል >> አሉ ብለው ጎዳና ተዳዳሪዎችን በኢቲቪ አሳይተውን ነበረ። አንድ ቀንስ ቢሆን ስለ ጎዳና ተዳዳሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስበውና አውርተው አይተንም ሰምተንም አናውቅም እኔ እንግዲ የማውቀው ለእለት ምግባቸው እንኳን ሲለምኑ ፖሊሶች ሲያባርሯቸውና ሲያሳድዷቸው ነበር የምናውቀው። ለካስ ኢቲቪ ደብቆን ነበር ይህን ሚስጢር ?
ይባስ ብሎ ኢቲቪ ለተተኪው ትውልድ ያወረሰው ነገር በጣም ነው የገረመኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ መላዕክት እንዲወደሱና ፎታቸውን አስቀምጠው እንዲሳለሟቸው ማድረግ ምን ገድል ሰርተው ነው ? ወይንስ አገሬን አላውቅም እስከምል ድረስ ነበር ግራ ያጋባኝ እናንተስ ምን ትሉ ይሆን ?
በመጨረሻ ለማንሳት የምፈልገው ነገር ቢኖር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲ የሚወደዱና የሕዝብ ፍቅር ከነበራቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታመማቸው ለሕዝብ አሳውቆ የኢትዮጵያ ሕዝብ በየሐይማኖቱ እንዲፀልይላቸው ለምን አላደረገም ? ሕዝቡ እንኳን መታመማቸውንና መሞታቸውን ቀድሞ እንኳን የሰማው ከግል ሚዲያ ነበር። ለማንኛውም ሙት ወቃሽ አያድርገኝ.... ብዙ ብንል ብዙ እንላለን እያወቅን በትርጉም እንዳይሆንብን እንጂ !!!
እውነቱ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደርጎለት ቀርቶ ሳይደረግለትም የዋህ አዛኝ ሕዝብ መሆኑን ማወቅ ብቻ ሳይሆን መረዳትና መገንዘብ ተገቢ ይመስለኛል
<<
ሕዝብን በፍቅር መግዛት ቀብርን ያሳምራል >>
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!! 
ከሰብኣዊ

No comments:

Post a Comment