Wednesday, August 7, 2013

አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል ፫)

ናደዉ ዋሺንግተን ዲሲ
በተከታታይ የፃፍኳቸዉ ሁለት ትችቶች የምክትል መቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ አፍራሽና ተንኳሽ የወያኔ ተልእኮ በጥቂቱ በመንደርደሪያ መልክ በማቅረቤ ብዙዎች በቴሌፎንና በአካል ቀላል የማይባሉ መረጃዎችን አድርሰዉኛል። በዚህ አጋጣሚ አመሰገንኩ።
ይህ የወያኔ ቅጥረኛ ግለሰብ ገንዘብ ያስገኛል የተባለበትን ሁሉ ይሞክራል፧አእምሮዉና አንደበቱ ለንጥቂያ ፈጣን ነዉ። ላለፉት አመታት ተጠቅሞበታል:: አሁንም አላቆመም። ብዙዎቻችን ዝም ብለን ስንመለከተዉ እንደ ጅል ቆጥሮናል። ከአሁን በኋላ ግን የምናዉቀዉን ሁሉ በማስረጃ ገሀድ እናደርገዋለን።ሕዝብ ሁሉንም የማወቅ መብት አለዉና! ዛሬ ይህ ግለሰብ ከሀመር ዉድ አዉቶሞቢል አንስቶ አገር ቤትም ሆነ እዚህ ዋሽንግተን አካባቢ የግል ቤቶች አሉት አገር ቤት ባለፉት አራት አመት ዉስጥ ያስገነባዉ ሁለት ፎቅ አፓርትመንቶች አበበ ዉርዉር ከሚባል ቱጃር ባለጊዜ ጋር በመሆን ያስገነባዉን ሕንፃ ለኪራይ ደርሶለታል መባሉን ሰማን ፎቶግራፍ እንደደረሰኝ በቅርቡ ይፋ አደርጋለሁ።

እጅግ የሚገርመዉ ግን በራሱ ራዲዮ ላይ በቅስቀሳ በየጊዜዉ የሚያሠለቸን በወያኔ ንብረቶች ላይ ማእቀብ እናድርግ ፤እንጀራ አትግዙ፣በየአየር መንገድ አትብረሩ እያለን ነዉ፧እሱ ግን እንደኪዮስክ አንድ ቄስና አንድ ዲያቆን ቀጥሮ የቤተክርስቲያንን ምሥጢራትን በሻንጣ ጭኖ በየኪራይ ቤቱ በማንከራተት በኦርቶዶክስ ሀይማኖቱ ላይ እየቀለደና ከየዋህ የእምነቱ ተከታዮች በሚሰበስበዉ ገንዘብ በተጠቀሰዉ ግለሰብ ስምና በሌላም መንገድ ሀብት ንብረት እያፈራ መሆኑ ደረስንበት።
ብዙ ወገኖች ይህ ጋጠወጥ ካድሬ የሚሰነዝራቸዉ ያልተገሩ ንግግሮች የግለሰቦችንና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን በስም እየጠቀሰ ያለይሉኝታ በዘለፋ ሲዘምትባቸው ንቀዉ ይሁን ምላሱን ፈርተዉ ትተዉታል። አንዳንዶቹም ከሱ ጋር መላተም አንፈልግም ሲሉ ይደመጣሉ። መቼ ይሆን እኛ ኢትዮጵያዉያኖች ያለ ይሉኝታ ያለፍርሃት የሚሠማንን መናገር የምንጀምረዉ? መቼ ነዉ አጭበርባሪና ሀፍረተቢሶችን ፊት ለፊት ተጋፍጠን ወግዱ ቃችሁ የምንላቸዉ ? እሱም ለዚህ ነዉ እንዲህ የልብ ልብ አግኝቶ ሰዉ አናት ላይ የሚወጣዉ።እሱና መሰሎቹ ራሳችን ከኪሳችን አዉጥተን በምንሰጣቸው ገንዘብ መንደርተኛ ራዲዮ ከፍተው ይሰድቡናል። ያዋርዱናል።
በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የጓድ ምርጫዉ ቤተ ክርስቲያን
በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የጓድ ምርጫዉ ቤተ ክርስቲያን
የተከበራችሁ ኢትዮጵያዉያን የቀበሮ ባሕታዉያን የበግ ለምድ ለብሰዉ እንዲከፋፍሉን ልንፈቅድላቸዉ አይገባም፧ወደ አለቆቻቸዉ ጉያ በግልፅ ነግረዉን እስከሚሸጎጡ ድረስ ቆመን አንመልከታቸዉ ፥በመሠሪ አንደበታቸዉ መርዛቸዉን በማር ጠቅልለዉ እንዲያጎርሱንም እድል አንስጣቸዉ፧ጊዜ ያለፈበትን የወያኔ ቅራቅንቦ ቅስቀሳ አምጥተዉ ያቀረሹብናል ፧ካለቆቻቸዉ የኰረጁትን አኬልዳማና ፧ጀሀዳዊ ሀረካት አይነት ፊዝ ቆርጦ ቀጥል የሚሉት አይነት የጅሎች ቁማር ያሰሙናል።የሆድ አደር ባንዳ ምሁራኖችን፧ በሙስናና በክህደት አለያም በአፍቅሮተ ሥልጣን ምክንያት በቅሌት ከድርጅቶቻቸዉ የተባረሩትን ዘላኖች የሻገተ ቃለምልልሳቸዉን ያሰሙናል።
ይህ ደካማ ግለሰብ እጅ እጅ ባለና ባልተገራ የውሮበላ አንደበቱ በአየር ላይ የሚበትዉን ትፋት በአጋጣሚ ራዲዮኑን የከፈቱ ወጣቶች ይበሳጬበታል፤ ጎልማሶች ያላግጡበታል አዛዉንት አረጋዉያኖች አሳዳጊ የበደለዉ ይሉታል። ጓድ መቶ አለቃ ምርጫዉ አንድ ነገር ልጠቁምህ በተለይ አንተ ማንንም የመተቸት የሞራል ብቃት ሊኖርህ አይችልም ምክንያቱም ትከሻህን የሚያጎብጥ ያዘልካቸዉ ብዙ አስነዋሪ ስራዎችህ በተለይ በዲሲና በአካባቢዉ ነዋሪዎች ህሊና ዉስጥ ዛሬም አለ፥ እስቲ አንድ አፍታ ቁጭ በልና ራስህን ጠይቅ እኔ ማነኝ?
ምን እየሰራሁ ነዉ ?በል መልሱን ራስህን አዳምጠዉ ይነግርሀል ፥ይህ የብልሆች ምክር ነው። እንዲያው ማይክራፎን ጨብጦ ሮጦ እንዳልጠገበ ወጠጤ እምቡር እምቡር ማለት ፀያፍ ነዉ።ያውም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነህ፥ አይልም ደስ ወንድም ዐለም!!!
አንድ የማከብረው ወዳጄ በአንድ ወቅት በአንድ መድረክ ላይ ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር ፦ወያኔ ዛሬም እዚያው ጫካ እንደነበረ ጊዜ ነዉ የሚያስበዉ ፧በስልጣን የቆየበትን ጊዜ ያህል አንድን የዱር አራዊት አሰልጥኖ ለማዳ ማድረግ ይቻል ነበር አለ። ያችን ትልቅ አገርና ያን ክቡር ሕዝብ በነዚህ ግልብ ወሮበሎች ሲመራ በማየቱ ተበሳጭቶ ፧ እና አንተም አስብበት የጥንት ዘፈንህን አቁመህ ወደ ቀልቢያህ ተመለስ ማለቴ ነዉ። ዉድ ኢትዮጵያዉያን ስለዚህ ግለሰብ ካገኘሁዋቸዉ መረጃዎች ለማንነቱ ግንዛቤ ይረዳችሁ ዘንድ እንዲያዉ አለፍ አለፍ ብዬ ጥቂት ማለት ወደድኩ፦ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኘዉ የወያኔ ተላላኪ የሆነው የሃገር ፍቅር ራዲዮ አዘጋጅና አቅራቢ ከሆነዉ ከንጉሤ ወልደማርያም ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸዉ ሲሆን ንጉሤ በቀጥታ በግልፅ ያለሀፍረት የወያኔን ፕሮፖጋንዳ የሚያሰራጭ ሲሆን ፥ምርጫዉ ስንሻዉ ግን በስዉር ተቃዋሚ መስሎ ተቃዋሚን ወደ በታኝ ተልእኮ ይዞ የሚንቀሳቀስ አደገኛ ሆድ አደር ግለሰብ ነዉ። ለምሳሌ ንጉሤ ለወያኔ ሚላኒየም በዓል ጥሪ አገር ቤት ሄዶ ፫ ወራት ያህል ሲቆይ የራዲዪኑን አየር ሰዓት አስረክቦት የሄደዉ ለጓድ ምርጫዉ ነበር።
የአረመኔዉ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ወታደሮች ደግሞ መንግስት አልባዉን ሶማልያን በቅጥረኝነት በወረሩበት ወቅት አለምአቀፍ ሚዲያዎች ወረራዉን ሲያወግዙ ምርጫዉ ግን ይህንን ወረራ እንኳን መለስ ዜናዊ ሙባረክም ቢመራዉ እደግፋለሁ ሲል ለፈፈ ለዚህ የሰጠዉ ምክንያት ደግሞ በዚያች ደካማ አገር ተሰግስገዉ ያሉትን ኦነግን ፧ኦብነግንና ኤርትራዉያኖችን ለመጥረግ ይቻላል አለን። ወረራዉ ጥቂት ሳይቆይ የመለስን ወታደሮችሬሳ በመንደር ሴቶችና ህፃናት በአዉራጐዳናዎች ላይ እየተጎተተ በድንጋይ ሲወገር በቴሌቪዥን መስታወት ተመለከትን፤ መለስ ዜናዊም በወታደሮቹ ሽያጭ ያገኘዉን የደም ገንዘብ በልጆቹና በቁባቶቹ ስም አስቀምጦ እሱም ሳይበላዉ አፈር በላ።
እንድትገነዘቡት የምፈልገዉና ለብዙ ጊዜ ያስተዋልኩት አንድ እዉነት አለ ፤ይኸውም በዳያስፖራ የሚገኙት ወያኔ መራሽ ራዲዮ ጣብያዎች የጓድ ምርጫዉንም ጨምሮ የሚቅበጠበጡበትና የሚይዙትና የሚጨብጡት ነገር የሚጠፋቸዉ ዳያስፖራው በዉስጡ ያሉትን ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ብሎ አንድ በሚሆንበት የጋራ ጠላቶቹን በጋራ በአንድነት ቆሞ ጠንካራ እንዲቅስቅሴዎችንን በማድረግ ሊፋለም በነሳባቸውወቅቶች ነዉ። ለማዳከም ለማፍረስ ከፍተኛ ርብርብ የሚያደርገው።፡እስቲ ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል ወደኋላ ልመልሳችሁ።
የዲሲና የአካቢዉ ነዋሪዎች እንደምታውቁት ከቅንጅት ምስረታ በፊት ጓድ ምርጫዉ በነገር አርጩሜዉ ያልዘመተበት የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅትና የአመራር አባል የለም በተለይ አብዝቶ ይኮንናቸዉ የነበሩት ኦነግ። ኢሕአፖንና ሻቢያን እንደነበር አይዘነጋም፧ከቅንጅት ምስረታ ማግስት አንስቶ ደግሞ የቅንጅት አመራሮችን የኢሕአፖ ጥርቅም ናቸዉ ፧ሲል ከረመ ። የቅንጅት መሪዎች በታሰሩ ማግስት ደግሞ እብደቱ ተነሳበትና በራዲዮ ጥሪ ለፈፈ ፧ከፋፋይ ጥሪ፣የአዲስ ፖርቲ ምስረታ ጥሪ ፧እኩይ የወያኔ ተልእኮ ፧ በቨርጂንያ ሮዝሊን አዳራሽ ዉስጥ ጥቂት የዋህ አገር ወዳድ ኢትዮጵያኖችን ሰበሰበ፧ የኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ንቅናቄ የሚል ስም ራሱ ሰይሞና ደንብ አርቅቆ ቀረበ። ከተሰብሳቢዎቹ ጥቂት ምፅዋት ሰበሰበ ፥ ይሄ አካሄዱ በወቅቱ አልተወደደለትም በጠንካራ ኢትዮጵያዉያኖች ትግል ከሸፈበት፤እኛ የፖርቲ ረሃብ የለብንም ተባለ !ሕዝቡ መሪዎቹን ሊያስፈታ አንድ በሆነበት ወቅት መሆኑ እርግጥ ነዉ፣ዛሬም እንዲሁ ዘር ሀይማኖት ፆታ ሳይለይ በአንድነት በተነሳበት ጊዜ ሁሉ ያንቀዠቅዣቸዋል ያልኩት ያለምክንያት አይደለም።
አንድ ወዳጄ እንዲህ አለ ቢጨንቀው፦ይሄ ሰውዬ ራዲዮ ጣቢያ አለው፣ ቤተክርስቲያን አለዉ፤ ፖርቲ አለው፤ እስር ቤት ቢከፍት እኮ መንግስት ይሆን ነበር አለና አሳቀን! እንዲህ አያሰኝም ብላችሁ ነዉ!?
ግለሰቡ ገንዘብ አምላኪነቱና ዉስልትናው እዚህ የመጣበት አገር አይደለም ፧ የጀመረዉ ይህን ልናገር ያስቻለኝ ባለፈዉ ሰሞን አንድ እህቴ ደወለችልኝ ከኦሀዮ፧እጅሽ ከምን አልኳት በዚህ ግለሰብ ዙርያ መረጃዎችን እሰበስብ እንደነበር ነግሬያት ስለነበር በመስመሩ ላይ አንድ ሰዉ እንዳለ ነገረችኝና የአንድ ወጣት ድምፅ ሀሎ አለ ራሱን ካስተዋወቀኝ በኋላ እንባና እልኽ በሚተናነቀዉ ድምፅ ንግግሩን ቀጠለ ፦እኔና ጓደኞቼን ምርጫዉ ስንሻዉ ወደዚህ አገር ሊመጣ ጥቂት ሳምንታት ሲቀረው ፧ሰባት ሺህ ብር ካመጣችሁ ወደአሜሪካ የሚያስኬድ ቪዛ አሰጣችኋለሁ ብሎ ብሩን ተቀበንና ተሰወረ ፧ባለቤቱንም ብንጠይቃት ለሷም ሳይነግራት መሄዱን በማዘን ነገረችን ፧እኛም አሜሪካን ሄደን ሰርተን እንከፍላለን ብለን ከዘመድ አዝማድ በተበደርነዉ ገንዘብ ምክንያት ብዙ ችግር ደርሶብን ጥቂት አመታት ከቆየን በኋላ ድንበር አቋርጠንና ብዙ አሰቃቂ ችግሮችን አልፈን በአምላክ ረዳትነት ያሰብንበት አገር አሜሪካን መጣን ብሎ አጫወተኝ።
እዚሁ ዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ የሆነችዉ ሌላዋ እህት ስሟን እንድደብቅላት አስጠንቅቃኝ ይኸው ጓድ ምርጫዉ እዚህ አገር በመጣ ሰሞን በሲቪኤስ መደብር በሚሰራበት ወቅት በዚህ ድህረገፅ ላይ ለመግለፅ በማይመች ሁኔታ ላይ ተገኝቶ ከሥራዉ መባረሩን በሀዘኔታ አጫወተችኝ።
የተከበራችሁ የዚህ ድህረገፅ እድምተኞች አንድ በግልፅ እንድትረዱልኝ የምፈልገዉ ነገር ቢኖር ፅሁፌ በግል ጥላቻ ላይ የተመሠረተ እሰጥ አገባ አይደለም። የአንድነት ጥብቅናና ፀረ ወያኔነት እንጂ!እንዲህ አይነቱ ነገር ላይ ጊዜ ማባከኑ ባልተገባም ነበር። በተለይም ከአንድ አገር ስደተኞች መሃል ።ነገር ግን ይህ ግለሰብና ግብረአበሮቹ የዚያች ምስኪን አገር ጠላቶች ፤ባንዳ ሆድ አደሮች የወያኔ ተላላኪዎች ፤ ምንም የሞራል ለከት የሌላቸው ሂሊና ቢስ መንደር አደግ የወያኔ የሜዳ አህዮች ስለሆኑ ነው። እንዴት ለናት ጡት ነካሾች ይታዘናል?!
ፋሺሽቶች ኢትዮጵያን በወረሩበት ወቅት ለጠላት ዕንቁላልና ወሬ አቀባይ ባንዳዎችን ለመቅጣት ሲነሱ እንዲህ ብለዉ ነበር፦፦ጠላትማ ምንግዜም ጠላት ነው አስቀድሞ መምታት አሾክሻኪዉን ነዉ!! ጀግኖች አባቶቻችን አጥንታቸዉን የድንበር አጥር አድርገው ይችን አገር ያቆዩልን።
እና እነዚህን የወያኔ ግብረበላዎችን ብዕሬ መብላትዋን የምታቆመው እነሱም እንደአለቃቸዉ ወደመቃብራቸዉ ሲያመሩ ብቻ ነዉ!!!
በክፍል ፬ ጠብቁኝ
ናደዉ ዋሺንግተን ዲሲ

No comments:

Post a Comment