ሰው-ሰውን ገድሎ ወይም ሌላ ወንጀል ፈጽሞ የብዙ ዓመት እስራት ቢፈረድበትም ህሊናው የሠራውን ስህተት ስለሚነግረው ቅጣቱን በጸጋ ይቀበላል፤አዕምሮው ምክንያቱን ስላወቀው እስራቱን ይችለዋል።ብዙውን ጊዜ እንደዚህ ዐይነት እስረኞች የሚጎዱት በመታሰራቸው ሳይሆን- ለእስር ያበቋቸውን ስህተቶቻቸውን ባሰቡ ቁጥር ነው።አዎ! ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ሁሉም ባይሆኑ ብዙዎቹ ወንጀል የፈፀሙ እስረኞች፦ “ለምን ታሰርኩ? ሳይሆን “ለምን ይህን ወንጀል ፈጸምኩ?” በሚል ጸጸት ነው ሲናጡ የሚሰሙት።
በአንፃሩ ያለ ጥፋቱ ለታሰረ የህሊና እስረኛ ግን እያንዳንዷ የእስር ቤት ቆይታ ከባድ ነች። ከባድ የሚያደርጋትም ለእስር ያበቃውን ምክንያት ህሊናው ስለማይቀበለው ነው። “ወህኒ ቤት ውስጥ የተቆለፈብኝ፣ይህን ያህል ዓመት በእስራት እንድቀጣ የተፈረደብኝ ምን ወንጀል ፈፅሜ ነው?” ለሚለው ጥያቄ፤ አዕምሮው መልስ የለውም። የታሰረው ያለምንም ጥፋትና በደል እንደሆነ ውስጡ ያውቀዋል። ስለዚህም “ለምንድነው የምታሰረው?እስከመቼስ ነው ያለ፡ጥፋቴ ታስሬ ምቆየው?” እያለ ሁሌ ይጠይቃል ፤ የታሰረው በሱ ስህተት ሳይሆን በአሳሪዎቹ የማሰር ፍላጎት እንደሆነ ስለሚያውቅም ሀዘኑ ይከብዳል።
ያለምንም ጥፋታቸው ከቤተሰቦቻቸውና ከህፃናት ልጆቻቸው ተነጥለው በቃሊቲ- የወህኒ በር የተቆለፈባቸው የህሊና እስረኞች የአዕምሮ መልስ በማያገኙለት በዚህ ዓይነት ጥያቄ ውስጥ ሆነው ሁለት ዓመት እየሞላቸው ነው።የአንዳንዶቾ(ጋዜጠኞቹ) ጥፋታቸው፤ በህገ-መንግስቱ እውቅና ያገኘውንና ጥበቃ የተሰጠውን ሙያቸውን ሲተገብሩ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ ሁላችንንም በፍትህና በእኩልነት የምታስተናግድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲፈጠር በመጠየቃቸውና የመብት ይከበር ጥያቄ በማንሳታቸው ነው።በአንፃሩ ያለ ጥፋቱ ለታሰረ የህሊና እስረኛ ግን እያንዳንዷ የእስር ቤት ቆይታ ከባድ ነች። ከባድ የሚያደርጋትም ለእስር ያበቃውን ምክንያት ህሊናው ስለማይቀበለው ነው። “ወህኒ ቤት ውስጥ የተቆለፈብኝ፣ይህን ያህል ዓመት በእስራት እንድቀጣ የተፈረደብኝ ምን ወንጀል ፈፅሜ ነው?” ለሚለው ጥያቄ፤ አዕምሮው መልስ የለውም። የታሰረው ያለምንም ጥፋትና በደል እንደሆነ ውስጡ ያውቀዋል። ስለዚህም “ለምንድነው የምታሰረው?እስከመቼስ ነው ያለ፡ጥፋቴ ታስሬ ምቆየው?” እያለ ሁሌ ይጠይቃል ፤ የታሰረው በሱ ስህተት ሳይሆን በአሳሪዎቹ የማሰር ፍላጎት እንደሆነ ስለሚያውቅም ሀዘኑ ይከብዳል።
እደግመዋለሁ፦እነሱ ለሙያቸው፣ ለአገራቸውና ለወገናቸው በመታመን እና በመሰጠት በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ- “ህገ-ወጦችና አሸባሪዎች” ተብለው ወደ ወህኒ ከተጣሉ ሁለት ዓመት ደፈኑ። ታዲያ፦“የታሰሩት ለኛ ፍላጎትና ለአገራችን የተሻለ ለውጥ ሲሉ ነው” ብለን የምናስበው እኛ- እነዚህ የህዝብ ልጆች ፍትህ ያገኙ ዘንድ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምን አደረግን? እስኪ መለስ ብለን እንቃኘው።ልብ በሉ! ይህን ጥያቄ እያቀረብኩ ያለሁት፦” እነ ርዕዮት ዓለሙ፣ እነ በቀለ ገርባ፣ እነ እስክንድር፣ እነ አቡበከር፣ እነ አንዷለም፣ እነ ውብሸት፣ እነ ኦልባና ወዘተ….” የታሰሩት ሙያቸውን ሲተገብሩና ለተሻለ የስርዓት ለውጥ ሲታገሉ ነው ብለን ለምናስበው ብቻ ነው።
በኔ በኩል ባለፉት ሁለት ዓመታት እነዚህን የህሊና እስረኞች ለማስፈታትና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት በአገር ቤትም ሆነ በውጪ አልፎ አልፎ በተወሰኑ ወገኖች ጥሩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ እንደሆነ ብሰማም፤ እነሱ ካሉበት ሁኔታና እየከፈሉ ካለው መስዋዕትነት አኳያ -የኛ ጥረት በቂ አይደለም ብቻ ሳይሆን በጣም ኢምንት እንደሆነ ይሰማኛል። ስለ እነሱ ጉዳይ ለማሰብና ለመወትወት -ግዴታ ርዕዮት የረሀብ አድማ ማድረግ፣አለያም አንዷለም መደብደብ ያለበት አይመስለኝም።በየጊዜው እኛ የማናየውና የማንሰማው ብዙ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ እናስብ።
ስለዚህ ለህሊና እስረኞች ፍትህ ያስፈልጋቸዋል ብለን የምናስብ ሁሉ፤ እነሱን ለማስፈታት የሚደረጉ ጥረቶችን በመቀላል፣”ፔቲሺኖችን” በመፈረምና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ነገሮች እንድንተገብር ስንጠየቅ በተግባር በማድረግ፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን በቻልነው አቅም አጋርነታችንን ልንገልጽላቸው ይገባል። ያን ስናደርግ እኛም ከህሊና ወቀሳ እንድናለን፤እነሱም በተስፋ እየተሞሉ በጥንካሬያቸው እንደጸኑ ይቆያሉ።
-እስኪ ርዕዮት ዓለሙ ፍትህ ታገኝ ዘንድ የሚጠይቀውን “ፔቲሺን” በመፈረም የተቀናጀ ሥራ እንጀምር።
እነሆ፦
http://
-ደግሞ የፊታችን ሴፕቴምበር 27 ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ -ከልጁ ከናፍቆት ተነጥሎ በታጣቂዎች ወደ እስር ቤት የተጋዘበት 2ኛ ዓመት በሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ይከበራል። ክፉ ቀን ያለያያቸውን አባትና-ልጁን በህብረት እንድዘክራቸው ይሁን።
(በራሳችሁ ሃሳብና መነሣሳት ይህን Event ለፈጠራችሁት ወዳጆቻችን ምስጋችን ከፍ ያለ ነው)
No comments:
Post a Comment