በዚህ ሰሞን የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ኢራን በምትከተለው የኢንተርኔት ተቆጣጣሪ ፖለሶች ደንብ መሰረት ልምዱን የቀሰመው የወያኔ ጁንታ የተለያዩ ሰላዮችን በማሰማራት ሳይሳካለት ቢቀርም በአሁኑ ወቅት በየኢንተርኔት ቤቱ እየዞረ ሰራተኞቹን በማስፈራራት ከፖለቲካ ጋር ግንጩነት የሚፈጥሩ እና የሚያወሩትን ሰርቨሩ ተከታትሎ ለፖሊስ እንዲጠቁም ካልሆነ መንግስት እስከመዝጋት ደረጃ እንደሚደርስ በይፋ ማስፈራራት ጀምረዋል::
ከ 22 ማዞሪያ አከባቢ እስከ ቦለ መድሃኒያለም ያሉ የኢንተርኔት ካፌዎች የዚህ ሰለባ መሆናቸውን ሰርቨሮቹ የሰጡት መረጃ ሲጠቁም በኢንተርኔት ቤቶቹ ገብተው በፌስቡክ እና በተለያዩ ድህረገጾች ብልጎች ላይ የፖለቲካ ጉዳዮችን የሚያነቡ ወጣቶችን እንዲወጡላቸው እየነገሯቸው መሆኑንም አክለው ገልጸዋል::
ከ 22 ማዞሪያ አከባቢ እስከ ቦለ መድሃኒያለም ያሉ የኢንተርኔት ካፌዎች የዚህ ሰለባ መሆናቸውን ሰርቨሮቹ የሰጡት መረጃ ሲጠቁም በኢንተርኔት ቤቶቹ ገብተው በፌስቡክ እና በተለያዩ ድህረገጾች ብልጎች ላይ የፖለቲካ ጉዳዮችን የሚያነቡ ወጣቶችን እንዲወጡላቸው እየነገሯቸው መሆኑንም አክለው ገልጸዋል::
በዚህ ሰሞን የተለቀቁ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ገዢው ፓርቲ በፌስቡክ ህዝብን ያነሳሳሉ ብሎ ያሰባቸውን በኢትዮዽያ ውስጥ የሚገኙ ወጣት የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን ወደ ቃሊቲ ለመወርወር እየተዘጋጀ ነው :: ለስውር አላማው ይረዳው ዘንድ የonline user's location finder ሶፍትዌር በስራ ላይ አውሎአል ነገር ግን ይህ ሶፍትዌር የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን ትክክለኛ መገኛ እና ቦታ ይፋ ማድረግ የሚችለው የፌስቡክ ተጠቃሚዎቹ ቻት በሚያደርጉበት ወቅት ነው :: እናም በኢትዮዽያ ለምትገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በሙሉ የማታውቁትን ግለሰብ ቻት ከማድረግ በመቆጠብ እራሳችሁን ከወያኔ መንጋጋ አድኑ ::
No comments:
Post a Comment