በልጅግ ዓሊ
አርባ ቀኔ ሆነ ከተለየኋችሁ፣
ድምጼን ከሰማችሁ ዓይኔንም ካያችሁ፣
ከጠየቃችሁኝ ካነጋገርኳችሁ፣
አርባ ቀኔ ሆነ ከሄድኩኝ ትቻችሁ።
ድምጼን ከሰማችሁ ዓይኔንም ካያችሁ፣
ከጠየቃችሁኝ ካነጋገርኳችሁ፣
አርባ ቀኔ ሆነ ከሄድኩኝ ትቻችሁ።
ምን አደረጋችሁ እኔ ከተለየሁ፣
ጉልበቴ ከከዳኝ ትንፋሼንም ካጣሁ፣
ዝናብ ካረጠበኝ፣
ፀሐይም ከመታኝ ፣
ከተለየኋችሁ አርባ ቀኔ ሆነኝ ።
ጉልበቴ ከከዳኝ ትንፋሼንም ካጣሁ፣
ዝናብ ካረጠበኝ፣
ፀሐይም ከመታኝ ፣
ከተለየኋችሁ አርባ ቀኔ ሆነኝ ።
ለአርባው ፍትሃት በሚዘጋጀው ዝግጅት ላይ ውድ ባለቤቱ እንድታነብለት ያሰበውን ግጥም የመጀመሪያውን ክፍል ጽፎ አረፍ አለ። አልጋ ውስጥ ሆኖ ሰው ያለ አይመስልም። ስጋው ከላዩ አልቆ አጥንቱ ብቻ ቀርቷል። ፈገግታው ግን ያው ነው። አንዳንዴ ሃሳብ ይዞት ጭልጥ ይላል። ምን እያሰበ ይሆን ? ባለፈው ወር ዶክተሩ ነቀርሳ(ካንሰር) እንዳለበት ሲነግረው ምንም የመደንገጥ ሁኔታ አላሳየም። እንዲያውም በደስታ ነው የተቀበለው። ለነቀርሳ የሚሆነውን መዳህኒት ትጀምራለህ ሲባል ሳያቅማማ ነበር እሺ ያለው። መዳህኒቱ ጎፈሬ የነበረውን ጸጉሩን መድምዶ ባዶ ራስ አድርጎታል። ፊቱን በመስታወት ሲመለከተው “ጣዕረ ሞት መስያለሁ አይደለም እንዴ ?” ብሎ ራሱን ጠየቀ። መልስም ሳይጠብቅ በፈገግታ አለፈው። ተመልሶ ያወጣና ያወርድ ጀመር። Read story in PDF
EMF
No comments:
Post a Comment