ከስምምነቱ ሳይርቁ ላለመስማማት መስማማት፤ ይሄን ‹‹ከኔ ሃሳብ ጋር መቶ በመቶ ካልተስማማህ ጠላቴ ነህ›› የሚለውን ጎጂ እምነት የተቃዋሚ አመራሮችና ደጋፊዎቻቸው፤ጨርሰው ማጥፋት አለባቸው፡፡
ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ይሄ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ተቃዋሚ ታዲያ በመቻቻል በስምምነት በመግባባት ላይ መሰረቱን ያዋቀረ የተባበረና የብዙሃኑን ፍላጎትና ራዕይ መሰረት ያደረገ ተቃዋሚ ሃይል ነው፡፡ ሕብረቱ በሕዝቡ ፍላጎትና እምነት ላይ መሰረቱን ያደረገ ሲሆን ሂደቱ ለምርጫ ውድድር መዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ሰፊ ምህዳር ያለው ፖሊሲ በመቅረጽ የሰፋ ውክልና ሊኖረው የሚችልና ለምርጫውም ቢሆን ሰፊ ድጋፍ የሚቸረው ሕዝባዊ ተቀባይነትና አመኔታ የተጣለበት አለኝታ ይሆናል፡፡ በሕብረት ውስጥ ሰፊ የሆነ ሃሳብና እቅድ የሚቀርብ በመሆኑ ይህንንም ወደ ተግባር ለመለወጥ የከረረ ውይይትና እሰጥ አገባ ተካሂዶበት ወደ ዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ስለሚደርስ የአብዛኛውን ሕዝብ ፍላጎት የሚያካትት ዓላማቸውን የሚያስፈጽም በመሆኑ ሊፈጠር የሚችለውን አለመግባባት ሁሉ በውይይት ፈትቶ ለውሳኔ ይደርሳል፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ እራሱን በሕብረት በሚያጣምር ፖሊሲ ላይ በማጠናከር መቆም ሲችልና በአንድነት አንድ ሆነው ሲንቀሳቀሱ ገዢውን ፓርቲና ፖሊሲዎቹን ለመሞገት ብቃት ይኖረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ተግባሩ ምን ሊሆን ይገባል?የሚለውን በደንብ ተንቅቆ ማወቅ ይገባል። የ2010ን ምርጫ አስከትዬ የምክር ሃሳቤን በፎከስ
ማጋዚን ላይ ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች አቅርቤ ነበር::የነበረውንም ክስተት ሁሉም የኢትዮጵያ ያውቃል ብዬ እገምታለሁ በወቅቱ ምክሬ አንድም ተቀባይ ያገኘ አይመስለኝም፡፡ እኔ ደግሞ ያመንኩበትን በይሉኝታ ለመቀልበስ ዝግጁ አይደለሁም፤እና አሁንም ደግሜ ያንኑ ምክሬን በማጠናከር የፖለቲካ ጨዋታው መለወጡን እየጠቆምኩ የገዢው ፓርቲ ግን ተደጋጋሚ የማስመሰያ ቃላት ከመሰንዘር ባለፈ ምንም ለውጥ ያለሳዩ ናቸውና እንደነበሩት ለመቀጠል ነው ሃሳባቸው፡፡ ባልታሰበ መንገድ ሁኔታዎች መለወጥ ጀምረዋል:: ይህ ጅማሮም በፈጠነ ሂደት ላይ መጓዙን አጠናክሮ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ ለውጥ ጉዞውን መቀጠሉ ማቆሚያ የሌለው ነው፡፡ በምድር ላይ ምንም አይነት ሃይል ይህን የለውጥ ጅማሬ ሊያቆመው ጨርሶ አይችልም፡፡ በስላጣን ላይ ያሉት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ባሻቸው መንገድ ሊያከሽፉትና ለራሳቸው እንዲመች ለማድረግ ቢጥሩ ከፈላጭ ቆራጭ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለውጡን ማቆም ምኞት እንጂ ተግባራዊ ሊሆንላቸው አይችልም፡፡ አሁን የቀረውና መልስ የሚፈልገው አንድ ጥያቄ ብቻ ነው፡፡ እገሌ እገሌ ተገሌ ሳይባል ሁሉም በገዢው ፓርቲ የተጨቆኑና የግፍ ሰለባ የሆኑ ተቃዋሚ ሃይላት ማሕበራት፤ የሰብአዊ መበት ተሟጋቾች፤ የዴሞክራሲ ናፋቂዎች፤ ሁሉም በአንድነት ከግፍ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት በኢትዮጵያ ለሚደረገው ሂደት ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?ከሕዝቡ ጋር ይቅር ለእግዚአብሔር ተባብሎ እርቅ መመስረት ፤ በ2005 በተካሄደው ምርጫ የተሳተፉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ሁሉም ወደ ሕዝቡ ተመልሰው፤ ባለፈው ተስፋውን፤ ሕልሙን፤መነሳሳቱን ያጨለሙበትን ሕዝብ ይቅርታ በመጠየቅ እርቅ ሊያደርጉ ተገቢ ነው፡፡ ለሕዝቡም ያለምንም ይሉኝታ ‹‹ባለፈው አሳዝነናችኋል፤ በዚያም በምር አዝነናል፤ ከናንተም ያጣነውን አመኔታና ድጋፍ ለማግኘት እንድንችል ጠንክረንና ካለፈው ተምረን እንክሳችኋለን›› ለማለት ብቃቱና ወኔው ሊኖረን የግድ ነው፡፡ ሕዝቡ ከተቃዋሚ መሪዎች ቅጥ ያለው ይቅርታ ይገባዋል፡፡ ይህንንም ቢያደርጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋ፤ ይቅር ባይ፤መሃሪ፤ አዛኝ ነውና ይቅር ይላቸዋል፡፡
ካለፈው ስህተት መማር፤ ካለፈው ስህተታቸው መማር የማይችሉና ፍቃደኝነቱም የሌላቸው ያንኑ ያለፈውን ስህትታቸውን መድገማቸው አይቀሬ ነው፡፡ ባለፈው በተቃዋሚዎች በርካታ ስህተቶችና ወድቀቶች ተከናውነዋል፡፡ እነዚህ ስህተቶች ተነቅሰው ሊወጡ ይገባል፡፡ ከነዚህም ስህተቶች በመነሳት ላይደገሙ ትምህርት ሊወሰድባቸውና ዳግም እንዳይመጡም ሊገቱ ተገቢ ነው፡፡
የተቃዋሚውን ተቃዋሚዎች ማወቅ፤ የተቃዋሚዎች ተቃዋሚዎች ቸል ሊባሉ አይገባም፡፡ ሃይላቸው ከፋፍሎ በመግዛትና በብሔር በማለያየት ድብ ድብ ጨዋታ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ተሰባስበውና ተባብረው አንድ ቢሆኑባቸውና አንድ የጋራ አጀንዳ ቢኖራቸው ገዢዎቹ የተቃዋሚ ተቃዋሚዎች አቅመቢስ ልፍስፍስ ናቸው፡፡
ተጎጂነትን ማቆም፤ ከተቃዋሚዎች ጥቂቶቹ ‹‹የተጎጂነት አስተሳሰብ›› ይዘዋል፡፡ ማንም ሰው የተጎጂነት ስሜት ሲያድርበት ከተግባርና ከሃላፊነት ይርቃል፡፡ ስለታሰሩት ጋዜጠኞች በቅርቡ ለተደረገለት ቃለመጠይቅ በሰጠው ይፋ መግለጫ ላይ ሃይለማርያም መልስ ሰጥቶ ነበር፡፡ ለአሜሪካን ድምጽ በሰጠው ምላሽ ላይ በሃገሪቱ ያሉት የፖለቲካ እስረኞች ‹‹ሽብርተኞች›› ና ከተወገዙ ድርጅቶች ጋር ሁለት ባርሜጣ አድርገው የሚሰሩ ናቸው፡፡ አንደኛው ‹‹ሕጋዊ›› ሌላው ደግሞ ‹‹ሕገወጥ››፡፡ የፖለቲካውን መድረክ ለመክፈትና ለማረጋጋት ስላለው ሃሳብ ምንም አላለም፡፡ ያም ሆነ ይህ ሃይለማርያምም ሆነ ገዢው ፓርቲ ያሻቸውን ይበሉም፤አይበሉም ተቃዋሚዎች ሳይደክሙና ሳያስተጓጉሉ አበክረው ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ መጠየቃቸውን መቀጠል አለባቸው፡፡ ተጠያቂነት ማለትም ይሄው ነው፡፡ ተቃዋሚው ሁል ጊዜ ለትክክለኛው ጉዳይ መቆም አለበት፡፡ የፖለቲካ ሰዎችን ከወህኒ መልቀቅ ትክክል ነው፤ በወህኒ ማጎር ግን ስህተት ነው፡፡
በመንስኤዎችና በጉዳዮች ላይ የጋራ አጀንዳ ማዘጋጀት፤ በሁሉም ተቃዋሚዎች ተቀባይነት ያለው የዴሞክራሲ፤የሰብአዊ መብት፤የሕግ የበላይነት፤የሕዝቦች አንድነት፤የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጥምረት ነው ማዕከሉ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ለማገዝና ለማራመድ የሚሆን አጀንዳ በጋራ መቅረጽ ምን ችግር አለው?
ከስምምነቱ ሳይርቁ ላለመስማማት መስማማት፤ ይሄን ‹‹ከኔ ሃሳብ ጋር መቶ በመቶ ካልተስማማህ ጠላቴ ነህ›› የሚለውን ጎጂ እምነት የተቃዋሚ አመራሮችና ደጋፊዎቻቸው፤ጨርሰው ማጥፋት አለባቸው፡፡ ከህሊናቸው ጋር ያሉ ሰዎች በሃሳብ ባይስማሙ ምንም ማለት አይደልም ጉዳትም የለውም፡፡ እነዚህ ደግሞ የዴሞክራሲ ባህሪ ናቸው፡፡ ተቃዋሚው በውስጡ የሃሳብ ልዩነትን ሳይቀበል የገዢውን ፓርቲ መቻቻልን አለመቀበል ሊያወግዝ ተገቢ ነው?
ግለሰብተኝነት ተመላኪነትን መከላከል፤ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ሂደት ውስጥ በጣም አስቸጋሪው ጉዳይ የሆነው የግለሰቦች ተመላኪነት ነው፡፡ በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ ተቃዋሚው ጀግኖችን በመፍጠር እነሱን ከምንም በላይ አድርጎ በመመልከትና ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ እያሞካሸና እያሞገሳቸው ከማምለክ ባልተናነሰ መጠን ከበሬታ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህንን ባደረግን ቁጥር ደግሞ የወደፊት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች እያሳደግን መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
ዘወትር በቀናነት መንቀሳቀስ፤ ተቃዋሚዎችም ሆኑ አብረዋቸው የተሰለፉት ሁሉ በቀና መንገድ መጓዝን መልመድ አለባቸው፡፡ ግለሰባዊም ሆነ ድርጅታዊ ግንኙነታቸው በቀናነት የተመሰረተ ሊሆን ይገባል፡፡ የምንለውን መሆንና የምንሆነውን ማለት ይገባናል፡፡ የአንድ ሰው ግለኛ የበላይነት ከማያስፈልግ ደሴት ውስጥ ያስቀምጠናል::
በጥቅሉ እያሰብን፤ተግባራችን ወቅታዊ፤ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የሚደረግ ትግል ምርጫን ማሸነፍ አለያም የስልጣን እርካብን ረግጦ ለሕዝባዊ ቢሮ መብቃት ብቻ አይደለም፡፡ ትግሉ ለታላላቅ ጉዳዮች ነው፡፡ ዘላቂነት ያለው ዴሞክራሲያዊ መሰረት ለመዘርጋት፤በኢትዮጵያ ሰብአዊነትን ማክበርና መጠበቅ እንዲሁም ተጠያቂነትንና የሕግን የበላይነት በአግባቡ አክብሮ ማስከበር፡፡ ይህንን እውነታ አምነን ከተቀበልንም ትግሉ አሁን ላለነው ለኛ ብቻ ሳይሆን፤ለሚመጣው ትውልድም ጭምር ነው፡፡ የምናደርገው ሁሉ ከኛ አልፎ ለተተኪዎቹ ልጅ ልጆቻችን የሚተላለፍ ኢትዮጵያችን ውድና የምትናፈቅ፤ ኖረንባት የማንጠግባት እንድትሆን በማድረግ ነው፡፡
ወጣቱ ትውልድ ለመሪነት እንዲበቃ ዕድሉን መስጠት፤ በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ ያለን የእድሜ ባለጸጎች ብዙዎቻችን ለመቀበል የሚያስቸገረን ጉዳይ አለ፡፡ ያም ችግራችን ቦታውን መልቀቅና ለወጣቱ ማስረከብን መማርና መቀበል አለብን፡፡ ለወጣቱ አመራሩን እንዲይዝ ዕድሉን እንስጠው፡፡ ወደድንም ጠላንም መጪው ዘመን የእነሱ ነው፡፡ ከኛ ስህተቶች እንዲማሩ ብናግዛቸውና ወደበለጠ አስተሳሰብና ዘዴ እንዲዘልቁ ብናደርግ በእጅጉ ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ በዓለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘው ወጣቶችን የሚመለከት አንድ እውነታ ቢኖር፤ ከምንም በላይ ነጻነትን መውደዳቸው ነው፡፡ የመጀመርያዋ የሴት ፖለቲካ መሪ የሆነችው ብርቱካን ሚዴቅሳ ትለው እንደነበረው፤ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት መሪዎቻችን እኛ ተማሪዎቻቸውና ተረካቢዎቻቸው ለምንገነባት ‹‹የወደፊቷ ሃገር ኢትዮጵያ›› እነሱ ውሃውን ያቀብሉን እኛ ከዚያ ባሻገር ያለውን ሁሉ እያደረግን ሃገርን እንገንባ፡፡
ሃሳባችን እንደ ድል አድራጊ እንጂ እንደ ተሸናፊ አይሁን፤ ድል፤ ድል አድራጊዎች እንደሚያስቡት፤ ሽንፈትም ተሸናፊዎች እንደሚያስቡት አይደለም፡፡ በድል ውስጥ ሽንፈት እንዳለ ሁሉ በሽንፈት ውስጥም ድል ይገኛል፡፡ በ99.6 ምርጫውን ድል ያደረጉት በገጽታቸው ላይ የአሸናፊነት ምስል ይታይባቸዋል፡፡ የተገኘው ድል ግን በተንኮልና በቅሚያ፤ በእፍርታምነት የተገኘ መሆኑን አስረግጠን እናውቃለን፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን ተቃዋሚዎች እንደ አሸናፊ ስብስብ ወይም ተሸናፊ መመልከቱ ላይ ነው፡፡ አሸናፊዎች እንደአሸናፊ ያስባሉ ተሸናፊዎችም በተቃራኒው፡፡
የተቃዋሚው ጎራ እራሱን እንደገና መፍጠር አለበት፤ ገዢው ፓርቲ ምንም እንኳን የለውጥ ፍንጣቂም ባያሳይ ደጋግሞ ግን በየሕዝባዊ ንግግሩ፤እራሴን እንደገና እያደስኩ ነው ይላል፡፡ ያም ሆኖ ግን ‹‹ምንም የሚለወጥ የለም›› ማለታቸውን ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጊዜ ካለው ሁኔታ አሁን ምንም ለውጥ አይኖርም ነው የሚሉት:: ተቃዋሚዎችም ቢሆኑ እራሳቸውን እንደገና መፍጠር አለባቸው፡፡ ለውጣቸውም እራሳቸውን ለዴሞክራሲያዊ እውነታ በማሰገዛት፤ሕዝቡንም በጠራ አመለካከት ላይ በማሰለፍ ሕብረትና አንድነት፤ መግባባትና መተሳሰብ ጠቀሜታው ታላቅ እንደሆነ ተገንዝቦ በማስገንዘብ፤ ድርጅታዊ ሃላፊነቱም በሕዝቡ ፈቃደኛነት ላይ የተገነባ መሆኑን በማረጋገጥና ሁል ጊዜም ዓላማቸው ለትክክለኛው ሁኔታ በመቆም በሃይል የሚደረገውንና አድራጊውንም ለመዋጋት መቆማቸውን በማረጋገጥ ላይ ሊሆን ይገባል፡፡
ተቃዋሚው ጨርሶ ተስፋ መቁረጥ አይገባውም፤ ሰር ዊንሰተን ቸርችል ‹‹ፈጽሞ እጃችሁን አትስጡ:: ፈጽሞ ፈጽሞ ፈጽሞ በምንም መልኩ ቢሆን:: በትልቅም ይሁን ትንሽ ፈጽሞ ፈጽሞ እጃችሁን አትስጡ!! ለክብርና ለመልካም ስሜት በታማኘነት ካልሆነ በስተቀር ፈጽሞ ፈጽሞ!! ሃይል አለኝ ለሚለው አትንበርከኩ:: ከአፍ እስከ ገደፉ ለታጠቀው ጠላትና አብረውት ሽር ጉድ ለሚሉት ሾካኮች ፈጽሞ እጅ አትስጡ!!›› የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ይህን ስልት ነው መከተል ያለባቸው እንጂ ለገዢው ፓርቲ አካኪ ዘራፍና የግፍ አፈና ሊሸነፉ አይገባም፡፡ ፈጽሞ ፈጽሞ ፈጽሞ!! ድል አድራጊዎች መንገዳቸው ይሄ ብቻ ነው፡፡
ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment