ከማስተዋል ብርሃኑ
‹‹ ከመወለድህ በፊት የነበረውን አለማውቅ ለዘላለም ህፃን ሆኖ መኖር ነው ›› ብሎ የተናገረ የጥንት ሮማዊ ሰው ሲሮስ እንደሚባል ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በመክሸፍ መፅሀፋቸው ላይ ነግረውናል፡፡ ፕሮፌሰርም ሀሳቡንም እንዲህ ሲሉ በመፃህፋቸው ላይ ደግፈውታል ‹‹… እኔ የታሪክ ስሜት የምለው እያንዳንዱ በዛሬው ዘመን ውስጥ የሚኖር ኢትዬጵያዊ ተገንጥሎ ለብቻው የሚኖር ሳይሆን ቀድመው የነበሩ ብዙ ትውልዶች የልፋት፣ የጥረትና የመስዋዕት ውጤት በመሆኑ ከበስተጀርባው የዚህን ትውልድ ቅርስ ሁሉ ተሸክሞ የቆመ መሆኑን እንዲታወቅ ያስፈልጋል፡፡…..››
የታሪክ አጋጣሚ ዛሬ ስልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግ እና ባለስልጣናት ስላለፉት ዘመናት የኢትዬጲያ ታሪክ ያላቸው የተንሸዋረረ እይታ ከላይ ያለውን ሀሳብ እንዳይቀበሉ አድርጓቻዋል፡፡ ስለዚህ ለዘላለም ህፃን ሆኖ መኖርን መረጡ ማለት ነው የሚል ጥያቄ ቢቀርብ እንዲህ ሆኑ ……
እውነት ሞትን ታሸንፋለች፡፡ ሞት ግን እውነትን አታሸንፍም፡፡ መለስ እውነትን አያውቃትም ሰለዚህ ሞት አሸነፈው፡፡ ታሪክ ግን አለው፡፡ ያለፈውን የብዙ ትውልድ ታሪክ እንዳይቀጥል የጀመረው ታሪክን ማጥፋት ስራ ፡፡ እሱ ሲያልፍ የታሪክ ሂደት ሆኖ የታሪክ ማጥፋት ስራውን ኢህአዴግና ባለስልጣናቱ ተያይዘውታል፡፡ ኢህአዴግ
የመለስን ታሪክ ለማስቀጠል በዘረኝነት እና በጥቅመኝነት ብዙዎችን አጥምቀው ‹‹የራዕዩ ስር ቁማርተኞች›› የሚባሉ አይነት ሰዎችን አፈሉ(ፈጠሩ)፡፡የታሪክ አጋጣሚ ዛሬ ስልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግ እና ባለስልጣናት ስላለፉት ዘመናት የኢትዬጲያ ታሪክ ያላቸው የተንሸዋረረ እይታ ከላይ ያለውን ሀሳብ እንዳይቀበሉ አድርጓቻዋል፡፡ ስለዚህ ለዘላለም ህፃን ሆኖ መኖርን መረጡ ማለት ነው የሚል ጥያቄ ቢቀርብ እንዲህ ሆኑ ……
አነዚህም የራዕዩ ስር ቁማርተኞች ስራቸው……..
መሬት የያዘውን የብዙ ዘመን የኢትየጲያ ታሪክን ቦታ ማስለቀቅ ……………/ለህንድ ገበሬዎች መሸጥ መሰለኝ //ሳቅ/
የተከበሩ የታሪክ መዛግብትን እና ቅርሶችን ማጥፋት
የታሪክ አዋቂዎችን ፀሀፊዎችን ማጣጣል ……በቃ ስንቱን ዘርዝሬ እችላለሁ ጠቅለል ላድርገው
የራዕዩ ስር ቁማርተኞች ስራቸው ከመለስ ራዕይ ውጪ ያሉትን የኢትዬጲያ 3ሺ አመት ታሪክ ማወቅ፣ ማንበብ እና ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለው ሙሉ ሰው አያደርግም የሚሉ ናቸው፡፡ እደግመዋለሁ ሙሉ ሰው አያደርግም ! የሚሉ ናቸው ፡፡
ደሞ እዛ ማዶ ያለኸው ራዕዩ ስር ቁማርተኛ ያልከው እኔን ነው በልና ጩኽ አሉ ደሞ……!
No comments:
Post a Comment