የሙስና ወንጀል ፈጽሟል በሚል የፌደራል የሥነምግባር እና የፀ-ሙስና ኮሚሽን ክስ የመሰረተበትበኢትዮ ቴሌኮም የምዕራብ አሶሳ ሪጅን ዋና ገንዘብ ያዥ የነበረው አቶ ኢዶሳ ረጋሳ በ20 ዓመት ጽኑ እስራትናበ50 ሺህ ብር እንዲቀጣ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነቀምት የሚገኘው የምዕራብ ምድብ ችሎት በቅርቡበዋለው ችሎት ውሳኔ አስተላለፈ።
ከፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው ተከሳሹ በኢትዮቴሌኮም የምዕራብ አሶሳ ሪጅን ዋና ገንዘብ ያዥ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት ከሰኔ እስከ ሐምሌ 2003 ዓ.ም ባለውጊዜ ውስጥ ከሽያጭ ሰራተኞች ከተረከበው ገንዘብ ውስጥ ብር 2 ሚሊየን 859 ሺ 318 ብር ባንክ ያስገባበማስመሰልና የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም አጭበርብሮ ለግል ጥቅሙ አውሏል።
ተከሳሹ በዚህ አድራጎቱ መንግስታዊ ሰነዶችን ወደ ሀሰት መለወጥና መገልገል፣ ከባድ አታላይነትእንዲሁም ዕምነት የማጉደል የሙስና ወንጀሎችን ፈጽሟል በሚል ኮሚሽኑ ክስ የመሰረተበት መሆኑን ለማወቅተችሏል።
ግለሰቡም ኮሚሽኑ የመሰረተበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ በ20 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብርእንዲቀጣ ፍ/ቤቱ የወሰነ ሲሆን በመንግስት ላይ ለደረሰው ኪሳራ በከፊል ማካካሻነት ይሆን ዘንድ ነቀምት ከተማየሚገኘውና በ200 ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈው የተከሳሹ መኖሪያ ቤት እንዲወረስ ኮሚሽኑ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታአቅርቦ ጉዳዩ በሂደት ላይ ይገኛል።
በሰንደቅ ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment