Wednesday, September 18, 2013

የስድስት ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የአሶሳው የትራፊክ አደጋ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ከአሶሳ ወደ አዲስ አበባ 60 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ኢት 22816 የጎን ቁጥሩ 2970 የሆነ አገር አቋራጭ አውቶብስ ትላንት ተገልብጦ 20 ሜትር ርቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ በመግባቱ ስድስት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በ38 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተሰማ።
 አደጋው የደረሰው ትላንት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ30 ላይ ከአሶሳ ወደ አዲስ አባባ 60 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከአሶሳ ከተማ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በሚገኝ ኩርባ መንገድ ላይ ሲደርስ አቅጣጫውን ስቶ 20 ሜትር በሚደርስ ጉድጓድ ውስጥ በመግባቱ ነው። ከዚህ አስከፊ አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ የቆሰሉት ወደ አሶሳ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ሌሎች 20 ያህል ሰዎች ደግሞ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከአደጋው መትረፋቸው ታውቋል።
አደጋው ከመድረሱ አስቀድሞ አወቶቡስ በከፍተኛ ፍጥነት ይጓዝ እንደነበር የዓይን እማኞች ገልፀዋል። የአውቶቡሱ አሽከርካሪ የ28 ዓመት ወጣት በቁጥጥር ስር ውሏል።

No comments:

Post a Comment