Monday, September 9, 2013

ሪያድ አንዲት የ24 አመት ኢትዮጵያዊት ጵግሜ 2 ቀን 2005 ከቀኑ 5 ኮንቴነር ውስጥ ሞታ ተገኘች !

ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ከአንድ ወር በፊት በኤንባሲው ጠያቂ ነት ከሳውዲ እስርቤት ወደ ኮሚኒቲ ጊዘያዊ መጠለያ ኮቴነር እንደተጣለች የሚነገርላት የ24 አመቷ ወጣት ዘይነብ መሃመድ እረፍት ዜና አያሌ ኢትዮጵያውያንን አስደንግጦል ። ወጣት ዘይነብ መሃመድ ወደ ኮሚኒትው መጠለያው ስትገባ በጣም ደክማ እንደነበር የሚገልጹት የአይን ምስክሮች ወጣቷ በወቅቱ የቅርብ ክትትል እና ህክምና ያስፈልጋት እንደ ነበር የሳውዲ ፖሊሶች ዘይነብን ለኤንባሲው በሃላፊነት ሲያስረክቡ መግለጻቸውን ይናገራሉ ።የ24 አመቷ ወጣት ዘይነብ መሃመድ ያለምንም የህክምና እርዳታ ለአንድ ወር ያህል መንሰኤው በማይታወቅ ህመም ስትሰቃይ ከርማ ፡ በሪያ የኮሚኒው መጠለያ ኮኒቴነር ውስጥ ሞታ ተገኝታለች ። የወጣቷ ህይወት ካለፈ በሃላ ሬሳውን ከቦታው ለማንስታ ኤንባሲውን ወክሎ በወጣቷ አሞሞት ዙሪያ ለሳውዲ ፖሊሶች ቃል የሚሰጥ ዲፕሎማት በመጥፋቱ ዛሬ ከቀኑ 5 አካባቢ ህይወቷ ያለፈው ወጣት ለሰአታት ሬሳዋ መጉላቱን ያዩ የኮሚኒቲው ማህበረሰብ እንባ እይተናነቃቸው ገልጸዋል ። ወጣቷ ወደ ኮሚኒቲው ግዜያዊ መጠላይ ስትመጣ በጣም ስለደከመች እንቀበላለን ይልቁን ኤንባሲው በሃላፊነት ወጣቷን ሆስፒታል እንዲያስገባ ጥረት ማድረግ እንዳለበት በወቅቱ ግፊት ቢያደርም ሲሚ አለማግኘታቸውን ጠቅሰው ዛሬ ለወጣቷ ህልፍተ ህይወት ግባር ቀደም ተጠያቂው ዲፕሎማቱ መሆናቸውን አበክረው ገልጸዋል። በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ጌዜ ያዊ መጠለያ ኮኔንቴነር ውስጥ፡ ከሚገኙ ወገኖቻችን መሃከል እስካሁን 4 እህቶቻችን መሞታቸው ይታወቃል ።
ከ Ethiopian Hagere ከሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ

No comments:

Post a Comment