Tuesday, September 10, 2013

ህወሀት/ኢህአዴግ፣ ዳግም ሩዋንዳን ለመስራት ያሰናዳውን “የአፍሪካው ልኡል” የተሰኘ መጽሀፍ በራዲዮ ለመተረክ አለማየሁ ታደሰ መስማማቱ አነጋጋሪ ሆንዋል

አለማየሁ ታደሰን ተው በሉት
ህወሀት/ኢህአዴግ፣ ዳግም ሩዋንዳን ለመስራት ያሰናዳውን “የአፍሪካው ልኡል” የተሰኘ መጽሀፍ በራዲዮ ለመተረክ ፣ ጌትነት እንየው ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር፣ አለማየሁ ታደሰ መስማማቱ ተነግሯል። መጽሀፉ ለገበያ ሳይበቃ አስቀድመው የአነበቡት የብአዴን ሰዎች፣ “በኢትዮጵያ ታሪክ እንዲህ አይነት አስቀያሚ መጽሀፍ ተጸፎ አያውቅም” ብለው ነግረውኛል። አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ መጽሀፉ ከፍቅር እስከ መቃብር ይበልጣል ብለው አስተያየት ሰጥተውበታል። በእነ መለስ ዜናዊና በረከት ሴራ ዳንኤል ግዛው የተባለ ሰው The prince of Africa በሚል የጻፈውን መዝሙር ፈንቴ ተርጉሞታል።
መጽሀፉ በይፋ ሳይመረቅ የቀረው መለስ በድንገት በመሞቱ ነው። ይህን ኢትዮጵያን የሚያደማ፣ ለትውልድ ከፍተኛ ጠበሳ ጥሎ የሚያልፈውን መጽሀፍ አለማየሁ ታደሰ ለመተረክ ተስማምቶ ከሆነ የእድሜ ልክ ጸጸቱን እንደሚሸምት እርግጠኛ ነን ። የምታውቁት ሁሉ እባካችሁ ምከሩት።
ይህን የምለው ለአለማየሁ ካለኝ ክብር አንጻር እንጅ በሌላ አይደለም።

Fasil YenEalem

No comments:

Post a Comment