ሌ/ጀኔራል ባጫ ደበሌ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞችን ከሥራ እንዲባረሩ አደረጉ
ሌ/ጀኔራል ባጫ ደበሌ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞችን ከሥራ እንዲባረሩ አደረጉ
ሌ/ጀኔራል ባጫ ደበሌ ‘’እንዴት አላወቃችሁኝም?’’ብለው ሁለት የአዋሽ ባንክ ሰራተኞች ከስራ እንዲባረሩ አደረጉ፡፡ ጅኔራሉ ሰሞኑን ከመኪና ግጭት ጋር በተያያዘ የተላከ ገንዘብ ለመቀበል በተልምዶ በድሉ ሕንጻ እየተባለ ወደሚራው ዋናው አዋሽ ባንክ ይሄዳሉ፡፡እንደደረሱም ገንዘቡ መድረሱን ገንዘብ ከፈዮቹን ይጠይቃሉ፡፡ጄኔራሉ የለበሱት የሲቪል ልብስ ነው፡፡ ሰራተኞቹም እንዳልደረሰ ይናገራሉ፡፡ሰራተኞቹ ይህን መልስ ሲሰጡ ሰውየው ሌ/ጀ ባጫ ደበሌ መሆናቸውን አላወቁም፡፡እንደማንኛውም የባንክ ተገልጋይ ነበር የተመለከቷቸው፡፡ጀኔራሉ በሰራተኞቹ አለመታወቃቸው አበሳጫቸውና በነገር ይጎነትሏቸው፣ ይዝቱባቸውም ጀመር፡፡ ግራ የተጋቡት ሰራተኞች የጀኔራሉን ስም እንደገና ይጠይቋቸዋል፡፡ይህን ያደረጉት ስማቸውን ኮምፒውተር ላይ ለመፈለግ ነበር፡፡ ጀኔራሉም ሰራተኞቹን በማንጓጠጥ መልክ‘’ኤል.ጂ.ባጫ ደበሌ በሉ’’ይሏቸዋል፡፡ሰራተኞቹ አሁንም ግራ ተጋቡ፡፡በዚህ መሃል ጀኔራሉ ዛኛና ስድብ ያወርዳሉ፡-‘’እናንተ ከዚህ ስረ ካለቀቃችሁ እኔ ሞቻለሁ ማለት ነው’’ይሏቸዋል፡፡እየፎከሩ የሰራተኞቹን አለቆች ሊያነጋግሩ ዘለው ወደውስጥ ገቡ፡፡ ትዕዛዙን ከሰጡ በኋላ ገንዘቡን ተቀብለው ወጡ፡፡እንደፎከሩትም ሁለቱም ሰራተኞች ወዲያውኑ ከሰራ ታገዱ፡፡ጄኔራሉ የተናገሩትን ተጨማሪ ጸያፍ ቃልና ፉከራ ለክብራቸው ስል ዘለልኩት፡፡እንዴት ያሳፍራል?Yሚገርመው የባንኩ የስራ ኃላፊዎች ድንጋጤና ፈጣን እርምጃ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment