Sunday, September 1, 2013

ጐዳና የወደቀና ሕይወት ፊቷን ያዞረችበት አዛውንቱ ሃበሻ በአሜሪካ ! (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

አዛውንቱ ሃበሻ በአሜሪካ
በዲሲ ዘጠነኛ መንገድ በአንድ ጥግ ኩርምት እንዳለ ነበር ያገኘሁት። ሔኖስ ይባላል፤ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ቴሌ-መድሃኒያለም ሰፈር ነው። ከአገር የወጣው የ18 ዓመት ወጣት እያለ ሲሆን፣ አሜሪካ 42 አመት ኖሯል። አሁን የ60 አመት አዛውንት ነው። በኢንጂነርነት በዲግሪ እንደተመረቀ ይናገራል። ከዚያም፥ « በዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለሁ ከተዋወቅኳት ጀርመናዊት ፍቅረኛዬ ሁለት ልጅ ወልጃለሁ። የመጀመሪያው ልጄ እድሜው 31 ሆኗል።» አለኝና ዝም አለ። አይኖቹ እንባ አቀረሩ። እንደምንም ብሎ ቀጠለ፥ « ልጆቼ ከእናታቸው ጋር በጀርመን- ሽቱትጋርት ይኖራሉ። ከተለያየን በጣም ቆየን። አይጠይቁኝም። ጐዳና የወደቀና ሕይወት ፊቷን ያዞረችበት ሰው ማን ይፈልገዋል!?» ..የእንባ ዘለላዎች ..ግድባቸውን ጥሰው ጉንጩን ያረጥቡት ያዙ። ላረጋጋው ሞከርኩ። እንባውን እየጠራረገ፥ «..በጣም ጥሩ ስራ እና ኑሮ ነበረኝ፤ ምን ዋጋ አለው!?..ነበርን ማውራት ምን ሊጠቅም!?..ትዳሬ ሲፈርስ በልጆቼ ናፍቆት ሰካራም ሆንኩ። ይኸው አሁን ለምታየው የጐዳና ሕይወት ተዳረኩ» አለኝና አነገቱን አቀረቀረ። ከዚህ በላይ ልጠይቀው አልቻልኩም። ..
( ሔኖስ ይኸውላችሁ….)

No comments:

Post a Comment