ልማት በመልካም አስተዳደር ላይ ይመሰረታል፡፡ታሪክ ትክክለኛውን ውሳኔ ያመላክተናል፡፡የሕዝቦቻቸውን ፍላጎት የሚያከብሩ፤በሕዝቦች ፈቃደኝነት የሚያስተዳድሩ በሃይልና በማንአለብኝነት ከሚገዙ የበለጠ ልማታዊ ፤ የበለጠ የረጉ፤እና የበለጠ ስኬታማ ናቸው፡፡ መሪዎች ራሳቸውን ለማሳበጥና በሃብትም ለመክበር ጥረት የሚያደርጉ ከሆኑ፤ ማንኛውም ሃገር ሃብት ሊኖረው አይችልም፡፡ፍትህ የሕግ የበላይነት በሚጨፈለቅበትና በሙስናና በሌብነት በተመሳቀለ ሃገር ውስጥ ለመኖር የሚመኝ ማንም የለም፡፡ ይህ አይነቱ ሁኔታ ያለበት የዴሞክራሲ ሃገር ሳይሆን የግፍ ሃገር ነው፡፡ያንን የመሰለውን አስከፊ ስርአት መገላገያው ደግሞ አሁን ነው… በ21ኛው ክፍለ ዘመን፤ችሎታ ያላቸው፤ታማኝነት ያላቸው፤እና ግልጽነትን የሚቀበሉ ኢኒስቲቲዩሽኖች ለዚህ ስኬት ቁልፍ ናቸው፡፡
—–ጠንካራ ፓርላማ፤ታማኝ የሆነ የፖሊስ ሃይል፤ነጻና ለራሳቸው ሕሊና የሚገዙ የፍትህ ስርአት አባላት፤ነጻና ዴሞክራሲያዊ ፕሬስ፤ ንቁና ልማታዊ የሆነ የግል ዘርፍ፤የሲቪል ማህበረሰብ፡፡ ለዴሞክራሲ ነፍስ የሚዘሩበትና መከታ የሚሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕብረተስቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አስፈላጊው ይሄው በመሆኑ፡፡…. ታሪክም ከነዚህ የአፍሪካ ጀግኖች ጋር ይቆማል እንጂ ራሳቸውን በሥላጣን ለማክረም ግፍ ከሚሰሩትና ለግለሰብ ፍላጎታቸው አመጽ ከሚያስነሱትና ሕገ መንግስቱን እንዳሻቸው ከሚያመሳቅሉት ጋር አይሰለፍም፡፡አፍሪካ ጡንቸኞች አየስፈልጋትም፤የሚያስፈልጋት የፈረጠሙ ዴሞክራሲያዊ ኢንስቲቲዩሽኖች ነው፡፡አፍሪካ የተሻለና ስፋት ያለው እድገት እንደሚኖራት ጥርጥር የለኝም፡፡ከሰብኣዊ
No comments:
Post a Comment