ሰሞኑን ለዚያራ ሻሸመኔ ወደ ሚገኘው ማረሚያ ቤት ጎራ ያሉ የሻሼ ሙስሊሞች በማረሚያ ቤቱ ግቢ ውስጥ የተቀዳደደ ባንዲራ ተሰቅሎ ሲውለበለብ አይተው በመንግስታችን ተግባር እጅጉን አዝነዋል!! መንግስታችንም ለተከበረው ባንዲራችን ክብርን ስላልሰጠው በወያኔ መራሹ መንግስት በጣሙን አፍረዋል!! ከርሱም ብሶ ባንዲራውን የሚያፈቅረውን ሀገር ወዳዱን ሙስሊም ለባንዲራ ክብር የሌላቸው ሲል ለብዙ ቀናት ሲዘልፍ በመቆየቱም በሀይል ተናደዋል!! የመንግስት ተግባርም ጅራፍ እራሱ መቶ እራሱ ይጮሀል!! የሚለውን ተረት እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል!!.... ታዲያ ለዚያራ ከሄዱ ወንድሞቻችን መሀከል አንዱ ወንድማችን ይህን በማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተሰቅሎ የነበረውን የተቀዳደደ ባንዲራን አይቶ እንዲህ በማለት ቀልድ አዘል ቁም ነገርን ተናግሯል፡- “እዚህ ማረሚያ ቤት የገባ ሰው ሁሉ እንደሚጨቆነው ፤ ባንዲራችንም ማረሚያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ገብቶ ተጨቆነ እኮ!!” በማለት አጠገቡ ያሉትን ፈገግ አሰኝቷል፡፡
እንደዚያ ምናከብረው ባንዲራችን በዚህ መልኩ ተቀዳዶ በማየታችን ልባችን አዝኗል ፤ ስለ ክብሩ ሲሉ አባቶቻችን ደማቸውን ያፈሰሱለት እንዲሁም ህይወታቸውንም የለገሱለት ክቡር ባንዲራችን በዚህ መልኩ ለባንዲራው ከብር በሌለው መንግስታችን እንደዚህ ተዋርዶ በማየታችን በጣሙን ተከፍተናል!!... ያ….በህፃንነታችን ለባንዲራችን የምናዜመው ዜማ አሁንም ድረስ ጆሮዬ ላይ ያቃጭልብኛል!!....
ባንዲራችን!!!
አረንጓዴ ፤ ቢጫ ፤ቀይ!!
አርማችን ነው!! መለያችን!!
ለኢትዮጲያ ሀገራችን!!!
ባንዲራችን…..
ድል ፍትህን ለተጠሙ ሙስሊሞች!!
አላሁ አክበር!!
ከአቡኪ
No comments:
Post a Comment