የአሸባብ ክፍፍልና የአባላቱ መገደል
መሃመድ ኡመር እንደሚለው በአልሸባብ መካከል ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ክፍፍል ተፈጥረዋል በክፍፍሉ ሳቢያ የጥቃት ኢላማ ከሆኑት መካከል አል አሜሪኪ ኣንዱ ሲሆኑ በጥቃቱ የኣህመድ መዶቤ እጅ እንዳለበት ግን በስፋት ይነገራል። አህመድ መዶቤ ከሶማሊ ላንድ እንዲያውም መሐመድ ኦመር እንደሚለው የኢትዮፕያ አካል ከሆነው የኦጋዴን አካባቢ የወጡ ናቸዉ።
የአሸባብ ታጣቂዎች
የአሸባብ ክፍፍልና የአባላቱ መገደል
የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የአሸባብ መሪዎችና ታጣቂዎች ተከፋፍለዉ እርስ በርስ መገደደላቸዉ ተዘገበ።የተለያዩ የዜና ምንጮች እንደዘገቡት የቡድኑ ታጣቂዎች እርስ በርስ በገጠሙት ዉጊያ የዉጪ ዜግነት ካላቸዉ የቡድኑ ተዋጊዎች እና መሪዎች ቢያንስ ሰወስቱ ተገድለዋል። ከተገደሉት አንዱ የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያለዉ እና አል አሜሪኪይ በሚል ቅፅል የሚታወቀዉ የቡድኑ የተዋጊዎች መሪ ይገኝበታል።ዩናይትድ ስቴትስ አሸባብ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚያደርገዉን ፕሮፓንጋንዳ ይመራ የነበረዉ አል-አሜሪኪን ለያዘ፥ ለገደለ ወይም ያለበትን ለጠቆመ አምስት ሚሊዮን ዶላር እንደምትሸልም ከዚሕ ቀደም አስታዉቃ ነበር።ከአል-አሜሪኪ ሌላ አንድ የብሪታንያ ዜግነት ያለዉ የፓኪስታን ተወላጅና ዜግነቱ ያልተጠቀሰ ሌላ ተዋጊ መገደሉም ተዘግቧል።ጀዓፈር ዓሊ አጭር ዘገባ አጠናቅሯል።
በአሜሪካ አላባማ ክ/ሀገር የተወለደው ኦመር ሀማሚ አል አሜሪኪ በሚል የግሃድ ስሙ ይበልጥ ይታወቃል የ29 ዓመቱ አል አሜሪኪ ወደ ሶማልያ ኣቅንቶ ኣልሸባብን የተቀላቀለው እ ጎ ኣ በ2006 ዓ ም ሲሆን በሶማሊያ አልሸባብን ተቀላቅለው ከሚንቀሳቀሱት እና ይበልጥ ከሚታወቁት መካካልም ነበር
ሓማሚ በእንግሊዝናው ዜማ እና የቪዲዮ ቅንብር እያዘጋገ የሶማሊያን መንግስት ለመጣል ወጣቱን በስፋት ከመቀስቀስ ኣንስቶ በጸረ አሜሪካ እንቅስቃሴ ውስጥም በስፋት ይጠቀሳል ከዚሁ የተነሳ አሜሪካ እሱን ላስያዘ ወይም ላስገደለ የ 5 ሚሊየን ዶላር ጉርሻ እንደምትሰጥአስታውቃም ነበር
ትላንት የተገደለው ግን በራሱ በአልሸባብ አንጃዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግችት መሆኑ ታውቀዋል
ትላንት የተገደለው ግን በራሱ በአልሸባብ አንጃዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግችት መሆኑ ታውቀዋል

No comments:
Post a Comment