ኢትዮጵያ በተለያዩ ፀሃፍት ዘንድ በተለያየ አጠራርና ስም ስትጠራ ኖራለች:: በዋናነት በኦሪት ላይ "ኩሽ" ትባል ነበር::
እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው 70 ሊቃውንት በጋራ ሆነው ብሉይን ከእብራይስጥ ወደ ፅርዕ/ግሪክ/ ሲተረጉሙ "ኩሽ" የሚለውን ቃል ከግብፅ በስተደቡብ ያለውን አገር ሁሉ ለመጠቆም ይጠቀሙበት የነበረውን የነገድ አባት ስም("አይቶ ፒያ") ወይም "Aithio-Pia" ብለው ተረጎሙት::
ይህን ወደ ግዕዝ ሲተረጉሙትም ቃሉን ብቻ እንደወረደ "ኢትዮጵያ" ብለው አሰፈሩት:: ከግዕዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎምም እንደገና ያለ ፍቺ ሆሄውን ብቻ "ኢትዮጵያ" አሉት:: ህዝቡን ደግሞ "ኢትዮጵያዊ" ::
የቃሉ ስር መሰረት የት ነው ? ሲባል ግሪክ ሆነ::ትርጓሜውስ ? ተብለው ሲጠየቁ "በፀሐይ የጠቆረ፣ በፀሃይ የተቃጠለ ፊት ያላቸው.." ብለው ነገሯቸው/ዋሹዋቸው::
እንግዲህ ብሉይ ከሂብሩ ወደ ፅርዕ በተተረጎመበት ዘመን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት በ282 ላይ ነበር:: እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው 70 ሊቃውንት በጋራ ሆነው ብሉይን ከእብራይስጥ ወደ ፅርዕ/ግሪክ/ ሲተረጉሙ "ኩሽ" የሚለውን ቃል ከግብፅ በስተደቡብ ያለውን አገር ሁሉ ለመጠቆም ይጠቀሙበት የነበረውን የነገድ አባት ስም("አይቶ ፒያ") ወይም "Aithio-Pia" ብለው ተረጎሙት::
ይህን ወደ ግዕዝ ሲተረጉሙትም ቃሉን ብቻ እንደወረደ "ኢትዮጵያ" ብለው አሰፈሩት:: ከግዕዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎምም እንደገና ያለ ፍቺ ሆሄውን ብቻ "ኢትዮጵያ" አሉት:: ህዝቡን ደግሞ "ኢትዮጵያዊ" ::
የቃሉ ስር መሰረት የት ነው ? ሲባል ግሪክ ሆነ::ትርጓሜውስ ? ተብለው ሲጠየቁ "በፀሐይ የጠቆረ፣ በፀሃይ የተቃጠለ ፊት ያላቸው.." ብለው ነገሯቸው/ዋሹዋቸው::
Aithio - Pia የሚሉት እነዚህ ሁለቱ ቃላቶች "አይቶ" ጥቁር፣አደረገ፣አቃጠለ፣ የሚል ትርጉም ሲሰጥ "ኦፕያ" ወይም "ኦጵስ" ፊት የሚል ትርጉም ይይዝና ነዋሪዎች ፊታቸውን ፀሃይ ያቃጠለው በሚል ፀና:: አንዳንዶችም ሲራሩልን "ጠይም" ለማለት ነው ይሉናል::
እንዴት ግሪካዊያን ኢትዮጵያ ማለት "በፀሃይ የጠቆረ" ማለት ነው እንዳሉን እና እንዳታለሉን/እንደዋሹን ይህን ያህል ካየን ይህን ቀልማዳነት ደግሞ እንዲህ እናፈርሰዋለን::
+++
"ኢትዮጲስ 1ኛ" እና "ኢትዮጲስ 2ኛ" የሚለው ስም ግሪክ ከመታወቋ ሺ አመት ቀድሞ እዚህ(ኢትዮጵያ) የነገስታት መጠሪያ ስም የነበረ ነው::
"ኢትዮጲስ" በአማርኛም፣በግዕዝም፣በሱባም፣ በእንግሊዘኛም፣ በምንም ቢለዋወጥ ያው "ኢትዮፒስ" ነው::
የአገሪቱ ስም ከግሪክ ብቻ ከተገኘ ንጉስ ኢትዮጲስ ከግሪክ የወሰደው ስም ነውን ?
የግዕዝ ቋንቋ በአጋዝያን ዘመን ነበረ:: ኢትዮጵያም ቋሚ ስም፣ ትርጉም ያለው ስም ነበራት:: ምንጩም ፍንጩም ግሪክ አይደለም!!!
ኢትዮጵያ ማለት በትክክለኛው፣ ፍጹም በጠራው አገላለጽ ባሁኑ "ኢት-ዮጵ":
የአማርኛ አባት በሆነው በግዕዝ = "ኢትኦጵግዮን"
የግዕዝ አባት በተባለው በሳባ = "እንቅዮጳዝዮን"
ቋንቋ ከመከፋፈሉ በፊት በኖኅና በቤተሰቦቹ ዘመን ኩሽቲክ ሴሚቲክ ተብሎ ከመከፋፈሉ በፊት የነበራት ስያሜ "እንቅዮጳዝዮን" የተባለች አገር ናት::
ስለዚህ በአማርኛ ኢትዮጵያ እያልነው ያለነው በዘመን ብዛት ተወራርሶ እዚህ ደረሰ እንጂ በጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አንድ አይነትና ተመሳሳይ፣ቢገለባበጥ ይዘቱንን የማይለቅ፣በራሱ በፈጣሪ የተሰየመ፣ከነወንዙ የተሰጠ ስያሜ ነው::
የምድር ሁሉ ቋንቋ፣ፈጣሪ ከፍጡሮቹ በተነጋገረበት ቋንቋ "እንቅዮጳዝዮን" ስትባል ቆየችና ቀስ በቀስ "ኢትዮጵግዮን" መባል ጀመረችና በመሐል ቤት ተሰረቀች:: ከዚያ በኋላ ለሌላ ግልጋሎት ሲጠቀሙበት ኖረው ብንፈልግ፣ብንፈልግ፣ብንዳብስ፣ብንዳብስ አጣነው:: በመጨረሻ "ኢትዮጵ" ሆኖ አገኘነው::
"ኢት" = ስጦታ
"ዮጵ" = ብጫ ወርቅ ወይም እንቁ
"ግዮን" = ፈሣሽ ወንዝ
በጥቅል "ኢትኦጵግዮን" = "የግዮን ወርቅ ስጦታ"
ከዚያ በፊት ማን ትባል ነበር ? "እንቅዮጳዝዮን"
እውነቱ ይሄ እና ይሄ ብቻ ነው!
ሙሉው ምንጭ የተገኘው: "የኢትዮጵያ የ5ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግ " ከሚለው መጽሐፍ በጋዜጠኛ ፍስሐ ያዜ ካሣ የተጻፈ!
መጽሐፉ በሚያስደስት መልኩ ሃተታውን እያተተ እና ድምዳሜውን እየደመደመ ይሄዳል::
No comments:
Post a Comment