ማክሰኞ ጳጉሜ 5/2005
ሀምሌ 2003 ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ቀላል አመት አልነበረም፡፡ መንግስት በግላጭ እስልምና ውስጥ እጁን ጣልቃ ማስገባቱን ያለአንዳች እፍረት ማወጅ የጀመረበት ጊዜ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን እንዲያገለግል የተቋቋመውን መጅሊስ መንግስት በሚሾማቸው የፖለቲካ ሹመኞች ተቆጣጥሮ መቆየቱ በሁሉም ዘንድ የታወቀ እውነታ የነበረ ቢሆንም በይፋ ያሻውን ሰሪ ለመሆን ጣልቃ ይገባል ብሎ ግን ከነጭራሹ የገመተ አልነበረም፡፡
መንግስት በሐምሌ 2003 በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው የሀይማኖት ስልጠና ነበር ‹‹አህባሽ›› የተሰኘው አንጃ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ያስመጣው አዲስ አስተሳሰብ መሆኑን ያስታወቀው፡፡ ብዙ ሳይቆይም በሀረማያው ስብሰባ ‹‹ሃይማኖታዊ›› ትምህርት ለመስጠት ሲዳዳቸው የነበሩት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው በግዮን ሆቴል በጋዜጠኞች ፊት በሰጡት መግለጫ የአዲሱን አንጃ መምጣት ይበልጥ ግልጽ አወጡት፤ ለሂደቱም በገንዘብ ያገዟቸውን ባለሀብቶች አመሰገኑ፡፡
ዜናው ብዙዎችን አስደነገጠ፡፡ ‹‹መንግስት በሃይማኖት፣ ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም›› ሲል የሚደነግግ ህገ መንግስት ባለበት አገር እንዲህ አይን ያወጣ ተግባር ሲፈጽሙ መገኘታቸው ህዝበ ሙስሊሙን አስቆጣ፡፡ እዚህም እዚያም ጉርምርምታ ተፈጠረ፡፡ ይህ ህዝባዊ ቁጣ ብዙም ሳይቆይ ወደሰላማዊ ትግልነት ተቀይሮ ዛሬ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በር እያንኳኳ ይገኛል፡፡ ‹‹የመብት ጥያቄያችን እስኪመለስ ይቀጥላል!›› አብሮን የቆየ ጥብቅ መፈክራችን ነው - ኢንሻአላሁ ተአላ!
ለዛሬ ጥቂት ጥያቄዎችን እስቲ እንጠይቅ! እስልምናን ከ1400 አመታት በፊት ለምታውቀው ውድ አገራችን ኢትዮጵያ የሊባኖሱ ‹‹አህባሽ›› ለምን አስፈለጋት? የትኛውስ ችግር ተፈጥሮ ይሆን በግጭት ስትታመስ ከኖረችው ሊባኖስ እስልምና ሊያስተምሩ አህባሾች ወደአገራችን የሚመጡት? የሀይማኖት ደሃ አለመሆናችን ጠፍቷቸው ይሆን? በወቅታችን እኒህን ጥያቄዎች ለመጠየቅ ተገደዋል - ኢትየጵያውያን ሙስሊሞች!
መንግስት አዲሱን አንጃ አምጥቶ ከመጫኑ በፊት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እያዳበረ የመጣው የተንሸዋረረ አመለካከት ዛሬ ሃገሪቱን ልትወጣው እሱም ሊወጣው ካልቻለው ጉድጓድ ውስጥ ከትቶታል፡፡ የመንግስት ካድሬዎች ያለአንዳች በቂ እውቀት በድፍረት ብቻ በሚሞነጫጭሯቸው ጥናት ተብዬ ወረቀቶች ሲያራምዷቸው የነበሩ የተሳሳቱ አመለካከቶች አገሪቱን የሀይማኖት ጭቆና ተምሳሌት እያደረጓት ይገኛሉ፡፡ ‹‹ይህ ሁሉ ለምን?›› ብለን ከጠየቅን መንግስት አህባሽን ለማምጣት በመንደርደር ላይ ሳለ ካድሬዎቹን ለማሰልጠን ያዘጋጀውና አፈትልኮ የወጣው ድብቅ መመሪያ መልሱን ይሰጠናል፡፡ ይህ ከወርሀ መጋቢት 2003 ቀደም ብሎ የተለቀቀ እቅድ ‹‹የሃይማኖት አክራሪነትንና የጎሣ ግጭቶችን የምንፈታበት አገራዊ ዕቅድ መነሻዎችና አቅጣጫዎች›› የሚል ርእስ ያለው ሲሆን ባለ 42 ገጽ ዶኩመንት ነው፡፡ ይህ ሰነድ አስገራሚ ነጥቦችን ይዟል፡፡ ከዚህ ሰነድ የተወሰኑትን በቀጣይ ይዘን እንቀርባለን፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment