ትናንት ቅዳሜ መስከረም ፬/፪፼፮ ከቀትር በኋላ እዚህ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስርቤት ከታሰሩ በኋላ ተፈተው የወጡት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ማለትም ማርቲን ሺቢ እና ዩዋን ፐርሹን እንዲሁም ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተወካዮች፡ ጋዜጠኞችና በስዊድን የሚኖሩ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ስዊድናውያን ሲሆኑ ጥያቄያቸውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ለኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደሚላክ ለማወቅ ተችሏል። ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፉትን የእስር ህይወት የሚዘግበውን እና በቅርቡ ለህትመት የበቃውን 438ቱ ቀናት የሚለውን መጽሃፋቸው ይፋ የሆነው በዚህ ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞችን ለማስታወስ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ እንዲሆን በመወሰን የዛሬ ዓመት ከእስር ሲፈቱ እስከዛሬ ድረስ ባልሰሩት ወንጅል በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በከፍተኛ ስቃይ ለሚንገላቱት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች እና ሌሎች የህሊና እሰረኞች የገቡትን ቃል ለማደሰ እንደሆነ በዝግጅቱ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ማርቲን እና ዩዋን መጽሃፋቸው በእንዲህ ዓይነቱ ዝግጅት ላይ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አንዱ የወሰኑበት ምክንያት የእነሱን ከእስር መፈታት ተከትሎ ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተወንጅለው በእስር ላይ የሚገኙ የስራ ባልደረቦቻቸው በዓለም ዓቀፉ ሚዲያ በመንዘጋታቸው እና ይሄንን በመላው ዓለም ዘንድ ትኩረት እያጣ የሚገኘውን ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ የመጣውን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አፈና እንዲቆም እርዳታ ለጋሽ አገሮች፡ አህጉራዊ እና ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች በስልጣን ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ መንግስት ግፊት ላይ በማድረግ በቃሊቲ፡ በቂሊንቶ፡ ዝዋይ እና ሌሎችም እስርቤቶች የሚገኙ ጋዜጠኞች፡የተቃዋሚ ፖርቲዎች መሪዎች እና በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች እንዲፈቱ በማሰብ ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በህይወት ከተለዩ በኋላ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አፈና ይሻሻል ሲባል ጭርሱን ተባብሶ መቀጠሉን በመጠቆም በቅርቡ ከማርቲን እና ዩዋን ጋር በተመሳሳይ ወራት እና ወንጀል ታስራ አሁንም በቃሊቲ እስርቤት ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባት ስላላችው አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ እንደዓብነት አንስተዋል። ርዕዮት በእስር ላይ በምትገኝበት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እየተፈጸመባት ያለውን ኢሰብዓዊና ኢህጋዊ በደሎች ለመቃወም ከመስከረም ፩ ጀምሮ በረሃብ አድማ ላይ መሆኗን በመጠቆም ይህ በገዥው ስርዓት ሎሌዎች በህሊና እስረኞች ላይ የሚካሄደው በደል እና ግፍ ቅጥ እያጣ መሆኑን አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም ውብሸት ታዬ ከእስር እንዲፈታ ያቀረበው የይቅርታ ደብዳቤ በገዥው መንግስት ተቀባይነት ካለማገኝቱም ባሻገር ከአራት ወራት በፊት ከቂሊንጦ ወደ ዝዋይ እስርቤት ሆን ተብሎ በመዛወሩ ልጁ እንዲሁም እድሜያቸው ከሰማኒያ ዓመት በላይ የሆናቸው ወላጆቹ ተመላልሰው ሊጠይቁት እንዳልቻሉ ተገልጿል። እነዚሁ የእስርቤት ባለስልጣናት ውብሸት ታዬ እና ሌሎች የህሊና እስረኞች ከቤተሰቦቻቸውም ሆነ ከሌሎች ጎብኚዎቻቸው በወር ውስጥ ከ100 የኢትዮጵያ ብር በላይ እንዳይቀበሉ እገዳ እንደተደረገባቸው ለመገንዘብ ተችሏል። በዚህ ለሁለት ሰዓታት በተካሄደው ዝግጅት ላይ ማርቲን ሺቢ፡ዩዋን ፐርሹን፡ መስፍን ነጋሽ እንዲሁም በስዊድን የአምንስቲ ኢንተርናሽናል እና የድንበርየለሹ የጋዜጠኞች ማህራት ተወካዮች በኢትዮጵያ እየተካሄደ ሰላለው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እና ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት አፈና ያላቸውን አመለካከት ካቀረቡ በኋላ ከታዳሚዎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች በመመለስ የእለቱ ዝግጅት ተጠናቋል። ABF የተባለው ስዊድናዊ የሲቪክ ተቋም፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ድንበርየለሹ የጋዜጠኞች ማህበር በስዊድን ይህንን መስከረም ፬ ፪፼፮ የተካሄደውን ዝግጅት በጋራ በመሆን አዘጋጅተዋል።
No comments:
Post a Comment